ብሔራዊ ባንክ ለፋይናንስ ተቋማት አዲስ መመርያ አዘጋጀ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በአገሪቱ የሚገኙ የፋይናንስ ተቋማት የሚመሩበት አዲስ መመርያ ለማውጣት ከባለድርሻ አካላት ጋር መወያየቱን፣ የተዘጋጀውንም ረቂቅ መመርያ ተግባራዊ ለማድረግ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡ የአገሪቱን የፋይናንስ ተቋማት በበላይነት የሚቆጣጠረው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጀው አዲሱ መመርያ ባንኮች፣ የኢንሹራንስ ኩባንያዎችና የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት የሚገዙበት ይሆናል ተብሏል፡፡ የሪፖርተር ምንጮች እንደገለጹት፣ ብሔራዊ ባንክ ይህንን ረቂቅ ሕግ ካዘጋጀና ጉዳዩ የሚመለከታቸው የፋይናንስ ተቋማት አስተያየት እንዲሰጡበት ካደረገ በኋላ ባለፈው ሳምንት ከባንኩ ቦርድ አባላት ጋር መክሮበታል፡፡ በ15 ገጾች የተዘጋጀው አዲሱ መመርያ አሥር ዋና ዋና አንቀጾች ሲኖሩት፣ አራት ዝርዝር ማብራሪያዎችን በማካተት ተቋማቱ ተፈጻሚ ማድረግ ያለባቸውን የአሠራር ደንቦችንና የብቃት መለኪያ መሥፈርቶችን ይዟል፡፡ አዲሱ የኮርፖሬት ገቨርናንስ መመርያ በዋነኝነት ትኩረት ያደረገው፣ በፋይናንስ ተቋማቱ ባለአክሲዮኖች፣ በቦርድ ዳይሬክተሮችና በተቋማቱ ከፍተኛ የአመራር አባላት ላይ ሲሆን የሁሉንም የኃላፊነት ድርሻና የተጠያቂነት አሠራር ያጠቃለለ ነው፡፡ በተለይ በፋይናንስ ተቋማት የሚፈቀዱ የገንዘብ ዝውውሮች፣ የተቋማቱን ፖሊሲና የብሔራዊ ባንክ መመርያ የጣሰ መሆን እንደሌለባቸው አዲሱ መመርያ ይደነግጋል፡፡ በሌላ በኩል ከብሔራዊ ባንኩ መመርያ ውጪ ባለአክሲዮኖችም ሆኑ የቦርድ ዳይሬክተሮች ብድር መውሰድ እንዳይችሉ ይደነግጋል፡፡ ዳይሬክተሮችና ባለአክሲዮኖች በማንኛውም በሌላ የፋይናንስ ተቋማት ውስጥ ኢንቨስት ማድረግ የማይችሉበት አንቀጽም በአዲሱ ረቂቅ መመርያ ላይ ተካትቷል፡፡ በዋና ሥራ አስፈጻሚውና በከፍተኛ የአመራር ኦፊሰሮች የተ