Posts

የኢትዮጵያ ዋንጫ ፡ ሲዳማ ቡና እና አርባምንጭ ከነማ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፉ

Image
የ2007 ዓ.ም የኢትዮጵያ ዋንጫ (ጥሎ ማለፍ) ትላንት በተደረጉ የመጀመርያ ዙር ጨዋታዎች ተጀምሯል፡፡ በ8፡00 አርባምንጭ ከነማ ከ ሙገር ባደረጉት ጨዋታ አርባምንጭ ከነማ በመለያ ምቶች በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፏል፡፡ ሙገር ሲሚንቶ ኤፍሬም ቀሬ በ17ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ግብ 1-0 ሲመራ ቢቆይም ታገል አበበ በ65ኛው ደቂቃ ግብ አስቆጥሮ አርባምንጭ ከነማን አቻ አድርጓል፡፡ የጨዋታው መደበኛ ክፍለ ጊዜም 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይቷል፡፡ አሸናፊውን ለመለየት በተሰጡት የመለያ ምቶች አርባምንጭ ከነማ 4-3 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፉን አረጋግጧል፡፡ በ10፡00 ሲዳማ ቡና ወልድያን በቀላሉ 3-0 አሸንፎ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፏል፡፡ አንዱአለም ንጉሴ ደምቆ በዋለበት ጨዋታ በ36ኛው ፣ በ73ኛው እና 81ኛው ደቂቃ ላይ 3 ግቦችን አስቆጥሮ ሐት-ትሪክ ሰርቶ ወጥቷል፡፡ አንዱአለም ንጉሴ በዙህ የውድድር ዘመን ወልድያ ላይ ሐት-ትሪክ የሰራ ተጫዋች ሆኗል፡፡ ከአንድ ሳምንት በፊት በሊጉ ቢንያም አሰፋ ወልድያ ላይ 3 ግቦች ማስቆጠሩ ይታወሳል፡፡ ምንጭ፦ ሶኬር ኢትዮጵያ

Arba Minch University has formally handed over 3.6 hectares of land to the Hawassa-based Yirgalem Construction Plc

Image
AMU Hospital construction: University hands over land to contractor Arba Minch University has formally handed over 3.6 hectares of land to the Hawassa-based Yirgalem Construction Plc on January 20, 2015, for the construction of 300-bedded teaching-cum-referral hospital. The stated land is situated opposite Madhanalem Church at Secha, Arba Minch. The construction process is likely to commence after three weeks. Academic Affairs Vice President, Dr Agena Anjulo, heading the AMU team for handing over the construction site to the above contractor, said, ‘‘Today, we are handing over the land to the contractor with some existing structures which would be dismantled; and soon they would start hospital construction.’’ Hospital Project Consultant, Mr Teklemariam Rad, said, ‘‘Today, we are handing over 3.6 hectares of land which presently has a garage, store, some houses, utility, sanitary, electric, telephone, water supply lines, surface water, and some additional constructions as a refer

በጥሎ ማለፉ ውድድር ሲዳማ ቡና ወልዲያ ከነማን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት ረታ

Image
በጥሎ ማለፉ ሙገር ስሚንቶ እና አርባ ምንጭ ከነማ ድል ቀናቸው ዛሬ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄዱ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ሙገር ስሚንቶ እና አርባ ምንጭ ከነማ ድል ቀናቸው። በ8 ሰዓት ላይ ሙገር ሲሚንቶ ከአርባ ምንጭ ከነማ ተገናኝተው 1 ለ 1 በመለያየታቸው፥ በተሰጡ መለያ ምቶች አርባ ምንጭ ከነማ 5ለ 4 አሸንፏል። ሲዳማ ቡና በበኩሉ ወልዲያ ከነማን 3 ለ0 በሆነ ውጤት ረቷል። ኢትዮጵያ ቡና ከመብራት ሃይል ነገ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም የፕሪሚየር ሊግ ቀሪ ጨዋታውን ሲያካሂድ ፥ ወላይታ ዲቻ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ ሀዋሳ ከነማ ከደደቢት አንድዚሁ ቀሪ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል። በሌላ በኩል 23ተኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ይቀጥላል። የሊጉ መሪ ቼልሲ ከተከታዩ ማንችስተር ሲቲ ዛሬ ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ላይ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው። ነገ  አርሰናል በኤሜሬትስ አስቶን ቪላን 10 ሰዓት ከ30 ላይ ያስተናግዳል።

መድረክ በሃድያ ዞን ሁለት ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ አካሄደ

Image
  የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ፓርቲ በሃድያ ዞን ሁለት ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ አካሄደ። ፓርቲው ትናንት እና ዛሬ ሰለማዊ ሰልፉን ያካሄደው በሆሳእና ከተማ እና በምስራቅ ባዳዋቾ ሾኔ ከተሞች ነው። የመድረክ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ በሁለቱ ከተሞች በተካሄደው ሰልፍ የፓርቲው አመራሮች፣ አባላት እና ደጋፊዎች ተገኝተዋል። ሊቀመንበሩ ሰልፉ በፀጥታ ኃይሎች ትብብር ያለምንም ችግር መከናወኑን ተናግረዋል። Read more:  ኤፍ.ቢ.ሲ

የምርት ዘመኑን ቡና ወደ ውጭ መላከ እንዳልቻሉ ቡና ላኪዎች ገለጹ

Image
በምርት ዘመኑ የተገኘው አዲስ ቡና ወደ ውጭ እየተላከ እንዳልሆነ ቡና ላኪዎች ገለጹ፡፡ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ ሁለት የቡና ላኪዎች ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ባለፉ ስድስት ወራት የተሸጠው ቡና ከአገር የወጣው በክረምት ወራት ነው፡፡ የሽያጭ ስምምነቱ ባለፈው ዓመት ቢደረግም በዚያው ዓመት መውጣት ባለመቻሉ፣ በዚህ ጊዜ መውጣት ያለበት አዲስ ቡና ግን መውጣት አልቻለም፡፡ ወቅቱ የታጠበ ቡና ወጥቶ አልቆ የደረቀ ቡና የሚላክበት ቢሆንም፣ በተለያዩ ምክንያቶች አፈጻጸሙ ዝቅተኛ መሆኑን ነጋዴዎች አመልክተዋል፡፡ ሽያጩ ሳይፈጸም የቀረው የተቀመጠው የቡና ዋጋ ሊወርድ ይችላል በሚል የቡና ገዥዎች ግብይት ለመፈጸም ባለመፈለጋቸው መሆኑን ሪፖርተር ያነጋገራቸው ነጋዴዎች ገልጸዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም አገር ውስጥ የሚገኙ ቡና አምራቾች የብራዚል ቡና በድርቅ በመመታቱ የዓለም የቡና ዋጋ ከፍ ሊል ስለሚችል፣ የሚያመርቱትን ቡና ለገበያ እያቀረቡ አይደለም በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ አንድ የንግድ ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ አዲሱ ቡና በሚፈለገው ደረጃ መውጣት ያልቻለው ቡና ላኪዎቹ በገለጿቸው ሁለት ምክንያቶች እንደሆነ አረጋግጠዋል፡፡  የመጀመርያ የዓለም ገበያ ከፍተኛ የዋጋ መዋዠቅ ውስጥ በመሆኑ ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ትላልቅ ገዥዎች ግዥ ከመፈጸም ተቆጥበዋል፡፡ በሁለተኛ ደረጃ የብራዚል ቡና በድርቅ በመመታቱና ብራዚል ምን ያህል ቡና ለገበያ እንደምታቀርብ በውል ባለመታወቁ፣ ገዥውም አቅራቢውም ወደ ቡና ግብይት ለመግባት ቁጥብ በመሆናቸው ነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡ በሌላ በኩል ንግድ ሚኒስቴር ባለፉት ስድስት ወራት ከቡና ወጪ ንግድ ከዕቅዱ በላይ ማግኘቱን አስታውቋል፡፡ ሚኒስቴሩ ውጤቱ የተገኘው የከረመ ቡ