Posts

ጠንካራዎቹ የደቡብ ክልል ክለቦች

Image
በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከሚወዳደሩ 14 ክለቦች መካከል የደቡብ ክልል አራት ክለቦችን በማሳተፍ ከክልሎች ቀዳሚው ነው። ክልሉ ከሚወከልባቸው አራት ክለቦች መካከል ሶስቱ ከመሪዎቹ መካከል የሚመደቡ ናቸው። ሃዋሳ ከነማም ቢሆን ለጊዜው በደረጃው ግርጌ አካባቢ መሰንበቻውን ያደረገ ቢሆንም ካለው የቡድን ስብስብና የቆየ ታሪክ በመነሳት በቅርቡ ወደ መሪዎቹ የመመለስ እድል እንዳለው በርካቶች ግምታቸውን ይሰጣሉ። የክልሉ ክለቦች ከሰበሰቡት ነጥብ በተጨማሪ በፕሪሚየር ሊጉ ትልቅ ልምድና ውጤት ያላቸውን ለቦች ሳይቀር ማሸነፍ ችለዋል። ለአብነት ያህል የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና መከላከያን፣ ደደቢትንና ኢትዮጵያ ቡናን ሲያሸንፍ አርባ ምንጭ ከነማ በበኩሉ በሜዳው ቅዱስ ጊዮርጊስንና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን አሸንፎ ከሜዳው ውጭ ደግሞ ከደደቢትና መከላከያ ጋር ነጥብ ተጋርቶ ተመልሷል። ወላይታ ድቻም ተመሳሳይ ገድል አለው።   ተጨማሪ ለማንበብ

የስምጥ ሸለቆ ሐይቆች ተፋሰስ ባለስልጣን ችግሮቹን ቀርፎ ወደ ተግባር በመሸጋገር አገራዊ ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ተባለ

Image
የስምጥ ሸለቆ ሐይቆች ተፋሰስ ባለስልጣን በአጭር ጊዜ ወደ ስራ በመግባት የተጣለበትን አገራዊ ኃላፊነት ሊወጣ እንደሚገባ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሳሰበ። ምክር ቤቱ ማሳሰቢያውን የሰጠው በምክር ቤቱ የተፈጥሮ ሀብት ልማትና አካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የስምጥ ሸለቆ ሐይቆች ተፋሰስና የአዋሽ ተፋሰስ ባለስልጣናት የ6 ወራት የዕቅድ አፈፃፀማቸውን ዛሬ በገመገመበት ወቅት ነው። የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ዶክተር ገመዳ ብነግዴ የባለስልን መስሪያ ቤቱን አስመልክተው በሰጡት ማሳሰቢያ መስሪያ ቤቱ  ከተቋቋመ አንድ  ዓመት ቢሞላውም አስካሁን ድረስ ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ አለመግባቱና በአጭር ጊዜ ወደ ስራ  በመግባት የተጣለበትን አገራዊ ኃላፊነት ሊወጣ ይገባል። እነዚህ ተፋሰሶች አሳሳቢ በሚባል ደረጃ ላይ እንደሚገኙና ባለስልጣኑ ከሌሎች የተፋሰስ ልማት ስራዎች ልምድ በመቀመር ፈጥኖ ተፋሰሶቹ ከአደጋው ሊታደጋቸው እንደሚገባ ጠይቀዋል። የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴርም በተፋሰስ ልማት ላይ የተሰማሩ መስሪያ ቤቶች አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል ማድረግ እንዳለበት ነው ቋሚ ኮሚቴው ያሳሰበው። የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ከበደ ከንቹላ መስሪያ ቤቱ በተሟላ መልኩ ወደ ተግባር አለመሸጋገሩን በሚመለከት ለቋሚ ኮሚቴው በሰጡት ምላሽ ለዘርፉ የሚመጥኑ ባለሙያዎች ባለማግኘቱ የተሟላ የሰው ኃይል ባለመኖሩ መሆኑን አስረድቷል። በተመሳሳይ ቋሚ ኮሚቴው የአዋሽ ተፋሰስ ባለስልጣን የ6 ወራት የዕቅድ አፈፃፀም ላይ ግምገማ አድርጓል። ባለስልጣኑ በረጅም ዓመታት ያካበተውን የተፋሰስ ልማት ልምድ አዳዲስ ለሚቋቋሙ የተፋሰስ ልማት ስራዎች ሞዴል በመሆን ልምዱን ሊያካፍል ይገባል ብሏል። ባለስልጣኑ በውሃ አስተዳደር የመረጃ ቋት በማደራጀትያከናወናቸው ስራዎች ቋሚ ኮ

ዓለም እንደየኣገራት የህዝብ ቁጥር

Image
The world according to population size This fascinating map depicts countries according to their population and was made using Microsoft Paint You don’t need complicated software to make a fascinating map of the world. Reddit user  TeaDranks  created this using none other than Microsoft Paint. It depicts countries according to their populations, with a single square representing 500,000 people. The map is dominated by China and India, the only two nations in the world with more than one billion residents. Japan, The Philippines and Indonesia have expanded wildly, while sparsely populated countries like Australia and Russia have shrunk beyond recognition. Twenty-nine countries are too small to fit on the map, including Samoa, Saint Lucia, Andorra and - despite its geographical size - Greenland. “The main problem was getting India and China to fit properly,” TeaDranks told i100.co.uk . “I got an outline of the country and gradually filled it into

ሲዳማ ቡና ከወልዲያ ከነማ 10 ሰዓት ላይ በኣበበ ቢቂላ ስታዲየም ይጫወታል

Image
ዛሬ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ሁለት የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ይካሄዳሉ። በ8 ሰዓት ላይ ሙገር ሲሚንቶ ከ አርባ ምንጭ ከነማ ሲገናኙ፥ ሲዳማ ቡና ከወልዲያ ከነማ 10 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ። ኢትዮጵያ ቡና ከመብራት ሃይል ከነገ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም የፕሪሚየር ሊግ ቀሪ ጨዋታውን ሲያካሂድ ፥ ወላይታ ዲቻ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ ሀዋሳ ከነማ ከደደቢት አንድዚሁ ቀሪ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል። በሌላ በኩል 23ተኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ይቀጥላል። የሊጉ መሪ ቼልሲ ከተከታዩ ማንችስተር ሲቲ ዛሬ ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ላይ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው። ሊቨርፑል ከዌስት ሃም፣ ማንችስተር ዩናይትድ ከሌችስተር ሲቲ በተመሳሳይ 12 ሰዓት ነገ ይገናኛሉ። ከነገ አርሰናል በኤሜሬትስ አስቶን ቪላን 10 ሰዓት ከ30 ላይ ያስተናግዳል።

በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ቅናሽ ተደረገ

የንግድ ሚኒስቴር በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ቅናሽ ማድረጉን አስታወቋል ። የዋጋ ቅናሽ ማሰተካከያ የተደረገው የነዳጅ ምርቶች የአለም ገበያ ዋጋ እየቀነሰ መምጣቱን መነሻ በማድረግ መሆኑን ነው ሚኒስቴሩ ለፋና ብሮድካስቲነግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ ያስታወቀው ። በዚህም መሰረት ከነገ ጥር 23 እስከ የካቲት 30፣ ቀን 2007 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ የነደጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋን ይፋ አድርጓል ። በዋጋ ክለሳውም ቤንዚን ኢታኖል ድብልቅ በሊትር 17 ብር ከ20 ሳንቲም ፣ ነጭ ናፍታ 16 ብር ከ10 ሳንቲም ፣ ኬሮሲን 14 ብር ከ42 ሳንቲም ፣ ቀላል ጥቁር ናፍጣ 13 ብር ከ91 ሳንቲም ፣ እንደዚሁም ከባድ ጥቁር ናፍታ 13 ብር ከ23 ሳንቲም ሲሆን፥ የአውሮፕላን ነዳጅ ደግሞ 15 ብር ከ21 ሳንቲም በሊትር የሚሸጥ ይሆናል ። ሚኒስቴሩ የነዳጅ ምርቶቹን ዋጋ በዝርዝር በነገው እለት በጋዜጣ የሚያወጣ መሆኑንና በሁሉም የሃገሪቱ ክፍል ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑንም አስታውቋል ።