የገዥው ፓርቲ ከተሞችን የማስፋፋት እቅድ ይፋ ተደረገ
ሃዋሳ ከተማ እኣኣ 2003 ሃዋሳ ከተማ እኣኣ 2014 የኢትዮጵያ ከተሞችን አቅምና ቁጥርን ለማሳደግ የሚያስችል እቅድ ይፋ ተደረገ አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2007 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ከተሞች አቅምና ቁጥርን ለማሳደግ የሚያስችል እቅድ ይፋ ተደረገ ። እቅዱ በከተማ ልማትና ቤቶች ኮንስትራክሽንና በአለም ባንክ የስታስቲክስ ኤጀንሲ በጋራ የተሰራ ነው። በሁለተኛው የእድገትና ትርንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን ከተሞችን ለኗሪዎች ምቹ ለማድረግ የሚያስችሉ ስራዎች በተጠናከረ መልኩ እንደሚሰሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ በመድረ ኩ ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉትም ጥናቱ የሌሎች ሀገራት ምርጥ ተሞክሮዎችን ሀገሪቱ እንድታይ ለማድረግ መሞከሩ የሚመሰገን ነው። አክለውም በተለይ በዚህ ወቅት ሀገሪቱ 2ኛውን የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ እያዘጋጀት ባለችበት ወቅት መሆኑ ደግሞ ያላየቻቸው ነገሮች ካሉ እንድታይ ያግዛታል ያሉት። ኢትዮዽያን እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2025 መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ ለማሰለፍ የሚደረገው ጥረት ከተሞችን በማሳደግና ቁጥራቸውን በማብዛት መደገፍ እንዳለበት ዛሬ የአለም ባንክ ይፋ ያደረገው ጥናት ይናገራል። የበርካታ የሀገራችን ከተሞች ፈተና የሆነው የመሰረተ ልማት ችግር፤ የሃይልና የመብራት እጥረት፤ ዘመናዊ የደረቅና የፈሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ ስርአት መስተካከል እንዳለበት የመኖሪያ ቤትና የስራ እድል ፈጠራው ላይም ሊታሰብበት እንደሚገባ ይጠቁማል። ከዚህ አንጻር የከተሞቹ እድገት ከመምጣቱ በፊትና ከተሞቹን ዝግጁ ከማድረግ አንጻር ምን መሰራት እንዳለበት ጥናቱ የሚጠቁም መሆኑን ነው በአለም ባንክ ከፍተኛ የከተማ ልማት ኤክስፐርት አቶ አበባው አለማየሁ የተናገሩት። ጥናቱ ሀ