Posts

ISS and Hawassa University have signed a Memorandum of Understanding in order to achieve cooperation in academic education and research

Image
ISS and Hawassa University have signed a Memorandum of Understanding in order to achieve cooperation in academic education and research. In the photo Dr Yosef Mamo (r), President of Hawassa University and professor Leo de Haan (l), Rector of ISS. Photo from ISS Facebook Timeline ISS and Hawassa University have signed a Memorandum of Understanding in order to achieve cooperation in academic... http:// fb.me/7jOsi4bRV  

BGI’s Hawassa Plant to Boost Beer Capital Production to 1.44m hl

Image
BGI Ethiopia, Ethiopia’s giant brewery, received eight large fermentation tanks for the expansion of its Hawassa plant on Thursday January 15, 2014 with an investment of 30 million euros. The eight large fermentation tanks will increase the production capacity of the Hawassa plant by nearly double, said Essayas Hadera, marketing manager of BGI Ethiopia. Each having a capacity of 2,200hl, two of the tanks are Bright Beer Tank (BBT), used for fermentation process and the remaining six tod tanks used for processing the beer. Ziemann International GmbH, a Germany based Company supplied beer tanks for many countries, including Russia, Mexico, and Belgium, manufactures the fermentation tanks. The tanks were purchased two months ago, all of which arrived at the Hawassa plant last Thursday. St George beer entered the Ethiopia market in 1922 by Belgian owners. Later it had German owners, before it was nationalized by the military regime. It is currently owned by BGI, which also has a

ፌዴሬሽኑ በተጨዋቾች ዝውውር ላይ መመሪያ አወጣ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በክለቦች ላይ የሚታየውን የተጨዋቾች የዝውውር ስርዓት ወደ ዘመናዊ አሰራር ለመቀየር የሚያስችል ሰነድ ይፋ አደረገ። የፌዴሬሽኑ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ወንድምኩን አላዩ ሰነዱ አለም የሚከተለውን አሰራር ለመተግበር የሚረዳው ይሆናል ብለዋል።በተጨዋቾች ዝውውር ጊዜ የኪራይ ሰብሳቢዎች፣ ያልታወቁ ደላሎችና አጭበርባሪዎችን ለመከላከል  የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል። ሰነዱ የተጨዋቾች ዝውውር በፌዴሬሽኑ እውቅና ሊኖረው እንደሚገባና የዝውውር ጊዜውም ፌዴሬሽኑ ባስቀመጠው ቀን ብቻ ሊወሰን እንደሚገባ ይገልጻል። እንደ ሰነዱ ከሆነ ክለቦች ከሶስት የማይበልጡ የውጭ አገራት ፕሮፌሽናል ተጨዋቾችን ብቻ ያስፈርማሉ። ሰነዱ ከጥር 25 ቀን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆንም ፌዴሬሽኑ ወስኗል። የወሬው ምንጭ ኢቲቪ ነው

የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ ድህነት ቢቀንስም ወደባሰ ድህነት የገቡ እንዳሉ ይፋ አደረገ

Image
- መንግሥት የመረጃና የጥናት ሥልት ችግሮች አሉ ይላል የዓለም ባንክ ይፋ ያደረገው የኢትዮጵያ የድህነት ጥናት ባለፉት አሥር ዓመታት ድህነት መቀነሱን ቢያሳይም፣ በአስከፊ ድህነት ውስጥ ይገኙ የነበሩ ሰዎች ወደ ተባባሰ የድህነት አረንቋ ማምራታቸውን አመለከተ፡፡ የዓለም ባንክ ጥር 12 ቀን 2007 ዓ.ም. ይፋ ያደረገው ጥናት እንዳሳየው፣ በዓለም አቀፍ የድህነት መስመር መለኪያ መሠረት (በቀን 1.25 ዶላር ገቢ ሥሌት) በአገሪቱ እ.ኤ.አ. ከ2000 እስከ 2011 ባሉት ዓመታት የድህነት መጠን ከነበረበት 55 በመቶ ወደ 30 በመቶ ቀንሷል፡፡ በዚህም በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ በአስከፊ ድህነት ውስጥ የሚገኘው ሕዝብ ቁጥር 25 ሚሊዮን መሆኑን፣ በባንኩ የአፍሪካ ቀጣና የድህነት ቅነሳና የኢኮኖሚ ማኔጅመንት ከፍተኛ የኢኮኖሚ ባለሙያዋ ሩት ቫርጋስ ሒል ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡  ሩት እንዳብራሩት ከሆነ እ.ኤ.አ. በ2005 ከነበሩት ድሆች ይልቅ እ.ኤ.አ. በ2011 የነበሩት ድሆች የበለጠ ደህይተዋል፡፡ ‹‹እጅግ ዝቅተኛ በሆነ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ደሃ ቤተሰቦች እ.ኤ.አ. ከ2005 ጀምሮ የኑሮ መሻሻል አላሳዩም፣ እንዲያውም አንዳንዶቹ በፊት ከነበሩበት በባሰ ድህነት ውስጥ ይገኛሉ፤›› በማለት የገለጹት ሩት፣ ከዓለም ድህነት መስመር ውጪ ያሉት 12 በመቶ ተጋላጮችም መልሰው ወደ ድህነት አዘቅት ውስጥ የመግባት ዕድላቸው ሰፊ መሆኑን አሳስበዋል፡፡  በጥናቱ መሠረት እ.ኤ.አ. በ2005 የነበሩት የአገሪቱ ድሆች መጠን እ.ኤ.አ. በ2011 ከነበሩት ድሆች ገቢ መጠን ጋር ሲነፃፀር፣ በ2011 የነበሩት ድሆች በ2005 ከነበሩት ያነሰ የገቢ መጠን እንደነበራቸው መታየቱን ሩት ይፋ አድርገዋል፡፡ በመሆኑም እስከ 2011 በነበሩት ስድስት ዓመታት ውስጥ ድሆች የነ

የዘጠኝ ፓርቲዎች ትብብር ሕዝቡ የምርጫ ካርዱን በጊዜ እንዲወስድ ጥሪ አቀረበ

የዘጠኙ ፓርቲዎች ትብብር በመጪው ግንቦት በሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ሕዝቡ በነቂስ ወጥቶ በመሳተፍ ከጐኑ መቆም ያስችለው ዘንድ፣ የምርጫ ካርድ በመውሰድ ዝግጅቱን እንዲጀምር ጥሪ አስተላለፈ፡፡   ትብብሩ ይህን ያሳወቀው ጥር 12 ቀን 2007 ዓ.ም. ‹‹በነፃነት ለፍትሐዊ ምርጫ የጀመርነው ነፃነታችንን የማስመለስ ትግል ይቀጥላል›› በሚል ርዕስ በሰማያዊ ፓርቲ ጽሕፈት ቤት በሰጠው መግለጫ ሲሆን፣ መግለጫውን የሰጡት ደግሞ የትብብሩ ሰብሳቢ ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት፣ ምክትል ሰብሳቢው አቶ ኤርጫፎ ኤርዴሎና ዋና ጸሐፊው አቶ ግርማ በቀለ ናቸው፡፡  ‹‹የትግሉ ቀዳሚና ዋነኛ ባለቤት የሆንከው መራጩ ሕዝብ ነፃነትና ክብርህን ለማስመለስ በምናደርገው ትግል በንቃት እንድትሳተፍ ዛሬውኑ በመመዝገብ፣ የሥልጣን ባለቤትነትህን የምታረጋግጥበትንና ይህን አምባገነናዊ ሥርዓት የምትቀጣበትን ትጥቅ ‹‹የምርጫ ካርድህን›› በእጅህ እንድታስገባ ጥሪያችንን እናቀርባለን፤›› በማለት ሕዝቡ የምርጫ ካርዱን በጊዜ ወስዶ እንዲጠባበቅ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡ በመጀመርያ ዙር በጋራ የትብብሩ እንቅስቃሴዎች የትግሉን አስፈላጊነት፣ ወቅታዊነት፣ የዓላማና የትግል ሥልት ትክክለኛነት በተግባር ማረጋገጡን ትብብሩ የገለጸ ሲሆን፣ በቀጣይም ትብብሩ ያስገኛቸውን ውጤቶች በመመዝገብ በሁለተኛ ዙር ላስቀመጠው ዕቅድ እንቅስቃሴ መጀመሩን አስታውቋል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ በመጀመሪያው ዙር የተመዘገቡት ውጤቶች ምን ምን እንደሆኑ ሪፖርተር ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን፣ የትብብሩ ኃላፊዎችም ምላሽ ሰጥተውበታል፡፡  ባለፈው የመጀመሪያ ዙር እንቅስቃሴ ከፍተኛ ድል እንዳስመዘገቡ የገለጹት የትብብሩ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ኤርጫፎ፣ ‹‹ሰላማዊ ሠልፍ ለማድረግ ተነስቶ በነበረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ገዥው ፓርቲ በወሰ