Posts

Sidama Bunna flying high

Image
12ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ታላቁን የቡና ደርቢ በይርጋለም ዛሬ አስተናግዶ ሲዳማ ቡና ኢትዮጵያ ቡናን 1ለ0 በመርታት በሊጉ አናት ላይ የሚያቆየውን ውጤት አስመዝግቧል። ሲዳማ ቡና በሜዳው እና በደጋፊው ፊት ያደረገውን ጨዋታ በበላይነት መወጣቱ በ5 የነጥብ ብልጫ የሊጉ መሪ እንዲሆን አስችሎታል። ሁለቱ ቡድኖች የመጀመሪያውን የጨዋታ ጊዜ ያለምንም ጎል ቢያጠናቅቁም ከእረፍት መልስ ሲዳማ ቡና ወሳኟን ጎል አስቆጥሯል። ጎሏም የሲዳማ ቡናን ጠንካራ ግስጋሴ ያስቀጠለች ሆናለች። ሲዳማ ቡና በ12 ጨዋታዎች 26 ነጥብ ይዟል። ኢትዮጵያ ቡና በአንጻሩ ነጥብ በመጣሉ ሊጉን ለመምራት የሚያደርገውን ጉዞ አስቸጋሪ አድርጎበታል። ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ወልድያ ተጉዞ ወልድያ ከነማን 3ለ0 በመርታት ወደ ሊጉ አናት ተጠግቷል። ጊዮርጊስ በመጀመሪያው ግማሽ አንድ እንዲሁም በሁለተኛው ግማሽ ሁለት ጎሎችን ከመረብ በማሳረፍ ነጥቡን በ11 ጨዋታዎች ወደ 21 በማሳደግ ሲዳማን በቅርብ ሩቅ ይከተላል። ተጋጣሚው ወልድያ ከነማ ደግሞ በወራጅ ቀጠናው መሰንበቱን አረጋግጧል። በሜዳው ሙገር ሲሚንቶን 1ለ0 ያሸነፈው ወላይታ ድቻ 20 ነጥብ በመያዝ በሊጉ ሶስተኛ ደረጃን መያዝ ችሏል። አዳማ ላይ የጎንደሩን ዳሽን ቢራ በተመሳሳይ 1ለ0 የረታው አዳማ ከነማ ወደ ሊጉ መሪዎች የሚያስጠጋውን ውጤት አስመዝግቧል። በወራጅ ቀጠናው የሚገኘውን እና አሰልጣኙን ያሰናበተው ሀዋሳ ከነማ ደግሞ ኤሌክትሪክን 2ለ1 በማሸነፍ የዓመቱን ሁለተኛ ድል አስመዝግቧል። ትናንት በተካሄዱ ሁለት የአበበ ብቂላ ስታዲዮም ጨዋታዎች ደግሞ መከላከያ ከንግድ ባንክ እንዲሁም ደደቢት ከአርባምንጭ በተመሳሳይ 1ለ1 በሆነ ውጤት ተጠናቋል። ምንጭ፦  www.ertagov.com

Sidama games for kids

home

Hippos Emerging from Lake Hawassa

Image
Photo:  b y   DAVE

ከሬዲዮና ከቴሌቪዥን በተጨማሪ ድረገፆችን ለመቆጣጠር አዲስ ህግ ተዘጋጀ ተባለ

በኢንተርኔት የሚሰራጩ ፅሁፎችን፣ ምስሎችንና ቪዲዮዎችን ለመቆጣጠር ታስቧል  የግል የሬዲዮ ጣቢያዎች ፈርሰው ከመንግስት ቻናል እንዲከራዩ ለማድረግ ታቅዷል      የሬዲዮና የቴሌቪዥን ስርጭቶችን ለመቆጣጠር ከስምንት ዓመት በፊት በታወጀው ህግ ላይ አዳዲስ ቁጥጥሮችን የሚጨምርና እንዲሁም የኢንተርኔት ስርጭቶችንና ድረገፆችን የሚያካትት ህግ ተዘጋጀ፡፡  ከተለያዩ የሚዲያ ተቋማት ጋር ከትናንት በስቲያ ሃሙስ ውይይት የተካሄደበት ረቂቅ ህግ፣ ነባሩ አዋጅ ውስጥ የሰፈሩ የባለቤትነትና የፈቃድ አሰጣጥ ቁጥጥሮችን የሚዘረዝር ሲሆን፤ በኩባንያ መልክ እንጂ በግለሰብ የሬዲዮ ወይም የቴሌቪዥን ድርጅት ማቋቋም እንደማይቻል ይጠቅሳል፡፡ የዝምድና ወይም የጋብቻ ግንኙነት ያላቸው ሰዎች ለብቻቸው ባለአክሲዮን የሆኑበት ኩባንያ ፈቃድ እንደማይገኝም ተደንግጓል፡፡  ምንም እንኳ እስከዛሬ ተግባራዊ ባይሆንም በ1999 ዓ.ም በወጣው ህግ፣ የግል የቴሌቪዥን ጣቢያ ለማቋቋም ፈቃድ እንደሚሰጥ ተገልፆ የነበረ ሲሆን፤ አሁን በተረቀቀው ህግ ግን የቴሌቪዥን ጣቢያ በግል ማቋቋም እንደማይቻል ይደነግጋል፡፡  መንግስት የቴሌቪዥን ማሰራጫ ኔትዎርክ እንደሚዘረጋ የሚገልፀው ይሄው አዲስ አዋጅ፤ የግል ኩባንያዎች ከመንግስት ቻናል እየተከራዩ ለመስራት ማመልከትና ፈቃድ መጠየቅ ይችላሉ ይላል፡፡  የግል ኩባንያዎች ለጊዜው የራሳቸው የሬዲዮ ጣቢያ ለማቋቋም ፈቃድ የሚያገኙበት እድል ሊኖር እንደሚችል አዲሱ ህግ ይጠቁማል፡፡  ወደፊት ግን በግል ባቋቋሙት የማሰራጫ ጣቢያ ሳይሆን ከመንግስት የማሰራጫ ጣቢያ ቻናል እየተከራዩ እንዲሰሩ ይደረጋል ተብሏል፡፡ ለዚህም መመሪያ እንደሚዘጋጅ በረቂቁ ህግ ተጠቅሷል፡፡   በረቂቁ ህግ ከተካተቱ 60 አንቀፆች መካከል አብዛኞች በሬዲዮና በቴሌቭዥን ስርጭት ቁጥጥር ላይ ያተኮሩ ሲሆን፤

የሲዳማ ቡና በብዙ ጀርመኖች ዘንድ እየተወደደ መጥቷል

Image
ቡና ጠጪዎች ከምበዙባቸው የኣውሮፓ ኣገራት መካከል ኣንዷ ጀርመን ናት። ጀርመኖች እንደጣሊያኖቹ ያህል ባይሆንም ቡና የመጠጣት ባህላቸው ጠንካራ ነው። ጀርመኖች በእረፍት ሰዓታቸው ፉት የሚሏትን ቡና ከተለያዩ ኣገራት የምያስገቡ ሲሆን፤ በብዛት የኢትዮጵያን ቡና በመግዛታቸውን ይታወቃሉ። ከ ኢትዮጵያ ከምያስገቡት የቡና ኣይነቶች መካከል ደግሞ ኣሁን ኣሁን የሲዳማ ቡና በብዙ ጀርመኖች ዘንድ እየተወደደ መጥቷል።  የወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ የኣውሮፓ ወክል ዘገባ ከሆነ፤ የሲዳማ ቡና የፕቺ፤ ሮስ፤ ሌሞን እና ሌሎች በርካታ ጣዕሞችን እንዲስጥ ለማድረግ ቀላል ከመሆኑ የተነሳ ቡናን በተለያዩ ጣዕሞች ጋር ኣዋህዶ ለመጠጣት በምሹ ሰዎች ዘንድ ተወዳጅ ሆኗል።  የሲዳማ ቡና በጥሩ ሁኔታ የተለቀመ እና በጸሐይ ኅይል በጥንቃቄ የደረቀ ከመሆኑ በላይ በ2000 ሜትር ከባህር ጠለል በላይ በሆነ መሬት ላይ በቮልካኒክ ሚኔራል በበለጸገ ኣፈር ላይ የበቀለ መሆኑ ተፈላጊነቱን ጨምሯል። ለማንኛውን በጀርመኖች ኣፍ የሲዳማ ቡና ብሎም የቦካሶ ቡና እንደት ይገላጻል፧ ከታች ያንቡ፦    Wenn die Scheune The Barn zum Kaffee-Mekka wird 13. Januar 2015 Hier wird Kaffee zur Wissenschaft, hier wird Kaffee zum absoluten Genuss. Im Berliner Kaffeeshop  The Barn  werden einige der hochwertigsten Kaffeebohnen des Planeten geröstet und serviert. Und die Zubereitung ist eine eigene Wissenschaft, die der Kunde live betrachten kann. The Barn in der Schönhauser Allee