እ.ኤ.አ. በ2012 መጨረሻ አቅራቢያ፣ ሊበርታድ የተባለችውና ንብረትነቷ የአርጀንቲና ባሕር ኃይል የሆነችው ወታደራዊ ማሠልጠኛ መርከብ በዓለም አቀፍ የሕግ አስከባሪ አካል በቁጥጥር ሥር የዋለችው፣ በጋና ቴማ ወደብ አቅራቢያ ሲሆን በዚያ ለሁለት ወራት ከሁለት ሳምንት እንድትቆይ ተገዳለች፡፡ ከዚህች መርከብ ባሻገር ንብርትነቱ የአርጀንቲና የሆነው ፕሬዚዳንታዊ አውሮፕላንም ሲበር ከነበረበት አገር ተይዞ በቁጥጥር ሥር ለመዋል በቅቷል፡፡ በዚህ አላበቃም፡፡ በአሜሪካው ፌዴራል ሪዘርቮ ባንክ የሚከማቸው የአርንቲና ማዕከላዊ ባንክ ተቀማጭ እንዳይንቀሳቀስ ከመደረጉ በላይ እንዲወረስ መደረጉ የሚታወስ የቅርብ ጊዜ ክስተት ነው፡፡ አርጀንቲናውያን ከጥቂት ሰዎች በተበደሩት ገንዘብ ሳቢያ ዕዳ አለባቸው እንበል፡፡ እውነታው ይሄው ነው፡፡ መሠረቱ በአሜሪካ ሆነ መቀመጫውን ኬመን ደሴት ያደረገውና ከአሜሪካ ውጭ በመንቀሳቀስ፣ የተለያዩ ፈንዶችን በማስተዳደር ከሚታወቀው ኤንኤምኤል ካፒታል ከተባለው ኮርፖሬሽን ጋር በተፈጠረ ቅራኔ ሳቢያ ነበር ንብረቶቹ የታገዱት፡፡ የኒውዮርክ ፍርድ ቤት በፍትሐብሔር ክስን ባስቻለበት ወቅት፣ ኤንኤምኤል ኮርፖሬሽን በአርጀንቲና ያለኝ ከ800 ሚሊዮን ዶላር በላይ ዕዳ ይከፈለኝ ሲል ጠይቋል፡፡ አርጀንቲና እ.ኤ.አ በ2001 በነበረባት የ82 ቢሊዮን ዶላር የብድር ቃልኪዳን ሰንድ (ሶቨሪን ቦንድ) ዕዳ በወቅቱ ለመክፈል አልቻለችም ነበር፡፡ እ.ኤ.አ. ከ1989 እስከ 2000 ድረስ በዘለቀውና አርጀንቲናን በመታው የፋይናንስ ቀውስ ሳቢያ፣ አገሪቱ ያለባትን የብድር ዕዳ ለመክፈል ሳትችል መቅረቷ፣ የአገሪቱን የቦንድ ሰርቲፊኬት የገዙ የውጭ ኢንቨስተሮችን ድንጋጤ ውስጥ የከተተ ክስተት ነበር፡፡ አርጀንቲና ዕዳዋን ለመክፈል አለመቻሏ ብቸኛ አገ