የፀረ ሙስና ኮሚሽን በቡና ወጪ ንግድ ችግሮች ላይ ያካሄደው ጥናት መጠናቀቁ ተሰማ
የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በቡና የወጪ ንግድ ላይ በተፈጠሩ ችግሮች ዙሪያ ሲያካሂድ የቆየውን ጥናት ማጠናቀቁን ምንጮች ገለጹ፡፡ ኮሚሽኑ ሕገወጥ ሥራ ሠርተዋል ባላቸው ላይ ዕርምጃ ለመውሰድ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ጋር እየተነጋገረ መሆኑ ታውቋል፡፡ የፀረ ሙስና ኮሚሽን ረዘም ያለ ጊዜ ወስዶ ሲያካሂድ የቆየው ምርመራዊ ጥናት ተጠያቂ የሚሆኑትን እንደለየ የሚናገሩት ምንጮች፣ በቀጣይነት መወሰድ ባለበት ሕጋዊ ወይም አስተዳደራዊ ዕርምጃ ላይ በከፍተኛ ባለሥልጣናት ደረጃ ውይይት እየተካሄደ መሆኑን ይናገራሉ፡፡ ነገር ግን የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ወዶ አጦ፣ ጥናቱ እየተካሄደ መሆኑን ነገር ግን ገና አለመጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡ የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ምንጮች ግን ኮሚሽኑ በንግድ ሚኒስቴርና በቡና ላኪዎች ላይ ትኩረት አድርጎ ሲያካሂድ የቆየውን ጥናት ማጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡ ጥናቱ ትኩረት ካደረገባቸው ጉዳዮች መካከል ንግድ ሚኒስቴር በቡና ላኪዎች ላይ በቂ ክትትልና ቁጥጥር አለማድረጉ፣ የተሟላ የመረጃ አያያዝ ሥርዓት አለመኖሩ፣ በሁሉም ድርጅቶች ላይ ወቅቱን የጠበቀ የቡና ክምችት ቆጠራ አለመካሄዱ፣ ለውጭ ገበያ የተዘጋጀን ቡና ኤክስፖርት በማያደርጉ ነጋዴዎች ላይ ዕርምጃ አለመወሰዱ፣ በኢትዮጵያ ምርት ገበያ በሚሸጥ የቡና ገለፈት ላይ ተገቢውን ቁጥጥርና ክትትል አለመደረጉ ተጠቃሾች ናቸው፡፡ ከዚህ በላይ ጐልቶ የታየው ችግር ደግሞ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፈቃድ ሳይሰጥ ቡናን ወደ ውጭ አገር ኤክስፖርት ማድረግ ነው፡፡ ብሔራዊ ባንክ ወደ ውጭ ለሚላክ ቡና የሚሰጠው ፈቃድ አለ፡፡ ይህ ፈቃድ ካልተገኘም ቡና ወደ ውጭ መላክ የተከለከለ ነው፡፡ ነገር ግን የተወሰኑ ነጋዴዎች ይህ ፈቃድ ሳይኖራቸው