Posts

African Human Rights Need More Commitment

AFRICA has to make stronger commitments to human rights issues if the continent is to make economic and democratic advances and benefit from its positive spin-offs, says the President of the African Court for Human and Peoples' Rights (AfCHPR), Justice Augustino Ramadhani. In his opening remarks at the national sensitisation seminar on the promotion of the African Court of Human and Peoples' Rights in Addis Ababa, Ethiopia on Saturday, AfCHPR President added that the success of Africa's Agenda 2063 would depend largely on the importance given to the promotion, protection and enjoyment of human and peoples' rights on the continent. "History teaches us that respect for human rights, the promotion of human development and the consolidation of peace, coupled with good political and economic governance are conditions sine qua non for any meaningful development," he told over 100 delegates drawn from various governments, Ambassadors, non-government organizatio

ሙስናን በክልሎች ለመከላከል መንግሥት የፖለቲካ ውሳኔ መስጠት አለበት ተባለ

Image
‹‹በፌዴራል ሥርዓት ውስጥ ጣልቃ መግባት ሕገ መንግሥቱን መጣስ ነው›› አቶ አስመላሽ ወልደ ሥላሴ በክልሎች፣ ብልሹ አሠራርና ሙስናን ለመከላከል፣ የክልል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽኖች በአመራሮች ተፅዕኖ በአግባቡ መሥራት ባለመቻላቸው የፌዴራል መንግሥት ፖለቲካዊ ውሳኔ እንደሚያስፈልግ የፌዴራል የሥነ ምግባር የፀረ ሙስና ኮሚሽን አሳሰበ፡፡ ኮሚሽኑ የአገር አቀፍ የፀረ ሙስና ጥምረት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አሥረኛ መደበኛ ስብሰባውን ኅዳር 11 ቀን 2007 ዓ.ም. በሸራተን አዲስ ለግማሽ ቀን ባካሄደት ወቅት እንደገለጸው፣ በየክልሉ ያሉ የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ተቋማት በነፃነት እንዳይሠሩ የክልሎቹ አመራሮች ተፅዕኖ እያደረሱባቸው መሆኑን አስታውቋል፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሕግና አስተዳደር ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ በአቶ አስመላሽ ወልደሥላሴ ሰብሳቢነት በተካሄደው አሥረኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ የተወሰኑ ባለድርሻ አካላት ብቻ ተገኝተዋል፡፡ የአገር አቀፍ የፀረ ሙስና ጥምረትና የፌዴራልና የክልል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽኖች የ2006 በጀት ዓመት ሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ካቀረቡ በኋላ፣ በተገኙት ጥቂት ባለድርሻ አካላት የተለያዩ ጥያቄዎች ተነስተዋል፡፡ በተለይ በአፋር፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝና በሶማሌ ክልሎች የፀረ ሙስና ተቋማት በነፃነት እየሠሩ እንዳልሆነና ያላቸውን ከፍተኛ ሀብት እንደ አገር መጠቀም አለመቻሉን ተሳታፊዎቹ ተናግረዋል፡፡ በክልል የሚገኙ አመራሮች እነሱ እንዲከሰስ የፈለጉትን የኮሚሽኑ ኃላፊዎች ካልከሰሱ ወይም መከሰስ የሌለባቸውን ከሰው ከተገኙ፣ ከኃላፊነታቸው እንደሚያነሷቸውና በፈለጉት ቦታ እንደሚመድቧቸው ጠቁመዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ የአፋር ክልል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙና ኮሚሽን ኃላፊ እንደሌለው የጠቆሙት የስብ

በኢትዮጵያ የዲፕሎማሲያዊ አገልግሎት ምደባ ወደ ፖለቲከኞች እያዘነበለ ነውን?

Image
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ሁሴን ኦባማ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለትችት ከዳረጓቸው ጉዳዮች መካከል የአሜሪካ የውጭ ዲፕሎማሲ ሥራ ላይ የሚመድቧቸው ሰዎች ማንነት አንዱ ነው፡፡ ፕሬዚዳንት ኦባማ እ.ኤ.አ. በ2012 ለድጋሚ ፕሬዚዳንትነት በተወዳደሩበት ወቅት ለቅስቀሳ ከፍተኛ ገንዘብ ሲያሰባስቡ የነበሩ ግለሰቦች ፕሬዚዳንት ኦባማ በድጋሚ ወንበራቸውን ካገኙ በኋላ የተወሰኑት በተለያዩ አገሮች በአምባሳደርነትና በዲፕሎማትነት ተመድበዋል፡፡  ለምሳሌ በቅርቡ በአምባሳደርነት የተመደበው ማቲው ባርዙን ለፕሬዚዳንቱ የምርጫ ቅስቀሳ ወጪ ከተሰበሰበው 700 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ 2.3 ሚሊዮን ዶላር የሚሆነውን በግሉ አሰባስቧል፡፡  በተመሳሳይ ጆን ፊሊፕስ ለኦባማ የምርጫ ዘመቻ 500 ሺሕ ዶላር ከሰበሰበ በኋላ በጣሊያን ሮም የአሜሪካ ዲፕሎማት ሆኖ ተመድቧል፡፡ ጆን ኤመርሰን 1.5 ሚሊዮን ዶላር ያሰባሰበ ሲሆን፣ የተመደበው ጀርመን በሚገኘው ኤምባሲ ነው፡፡ ጄን ስቴትሰን 2.4 ሚሊዮን ዶላር አሰባስቦ፣ የተመደበው በፈረንሳይ ፓሪስ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡  የአሜሪካ ፕሮፌሽናል ዲፕሎማቶች ማኅበርና ጡረታ የወጡ የአገሪቱ አምባሳደሮች የፕሬዚዳንት ኦባማን ድርጊት ከመውቀስ አልፈው ‹‹የመንግሥት ቢሮን የመሸጥ ያህል ነው›› በማለት ድርጊቱን ተችተዋል፡፡ ይህ ዓይነቱ የፈጠጠ የጥቅም ግንኙነት ያለበት የውጭ ዲፕሎማቶች አመዳደብ በኢትዮጵያ ባይስተዋልም የግለሰቦችን ነፃነት የሚጋፋ አካሄድና በሕግ የማይመራ አመዳደብ ለበርካታ ዓመታት ሥር ሰዶ የከረመ እንደነበር የተወሰኑ ዲፕሎማቶች ይናገራሉ፡፡  በተለይ በ1997 ዓ.ም. በተካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ ፈተና ውስጥ ገብቶ የነበረ መሆኑን የተገነዘበው ገዥው ፓርቲ ከገባበት አጣብቂኝ ከወጣ በኋላ የአባላቱን ቁጥር ለማ

በ6ኛው የከተሞች ፎረም ውድድር የሲዳማዋ መዲና ሃዋሳ ከተማ አሸናፊ ሆነች

Image
በ6ኛው የከተሞች ፎረም ውድድር የሲዳማዋ መዲና ሃዋሳ ከተማ አሸናፊ ሆነች። ዝርዝር ወሬውን ከታች ያንቡ፦ ባለፉት አመታት በከተማ ልማት ዘርፍ የተሸለ ስራ መስራቱን የከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚንስቴር ገለፀ፡፡ “ከተሞቻችን የኢንተርፕራይዞች ልማት ማዕከላት በመሆን የኢትዮጵያን ህዳሴ ያሳካሉ” በሚል መሪቃል በድሬዳዋ ሲካሄድ የሰነበተው የከተሞች ፎረም ተጠናቋል፡፡ በመዝጊያው ላይ ንግግር ያደረጉት የከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚንስትሩ አቶ መኩሪያ ሃይሌ እንዳሉት፥ ባላፉት አመታት በከተማ ልማት ዘርፍ የማስፈጸም አቅም በመጠናከሩ የተሸለ ስራ መስራት ተችሏል፡፡ በጥቃቅንና አነስተኛ ለ3 ሚሊዮን ሰዎች የስራ ዕድል ለመፍጠር ታስቦ እየተሰራ መሆኑን የገለፁት ሚኒስትሩ ለማምረቻ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ትኩረት እንደተሰጠ ገልጸዋል፡፡ በጠቅላይ ሚንስትር ማዕረግ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪና የመገናኛ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚንስትር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል በበኩላቸው ከተሞች የሀገሪቱ የዕድገት አውታር መሆናቸውን ጠቁመው፥ ከተሞች በተፋጠነ መልኩ እድገታቸው እንዲቀጥል የከተማ አጀንዳዎችን ከኪራይ ሰብሳቢነት የማጽዳት ስራ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል፡፡ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አሰድ ዚያድ በበኩላቸው፥ ከዝግጅቱ መልካም ልምዶችን እናዳገኙ ተናግረዋል፡፡ ልምዱን ተጠቅመውም የከተማቸወን ዕድገት እንደሚያፋጥኑ ገልፀዋል፡፡ 189 ከተሞችንና ባለድርሻ አካላት በተሳተፉበት መድረክ ለሞዴል ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተፕራይዞች፣ ለሴት ኢንተርፕረነሮች እንዲሁም ወደ ታዳጊና መካከለኛ ለተሸጋገሩ ኢንተርፕራይዞች እውቅና ተስጥቷል፡፡ ከተሞች በፎረሙ ላይ ራሳቸውን ለማስተዋወቅ ባደረጉት ውድድር በምድብ አንድ የ

በጀርመኗ ኮሎን ከተማ በተከፈተው ኣለም ኣቀፍ የፋይን ኣርት ኤግዚብዥን የሲዳማ ባህላዊ ''Barikko'' ባርኮ ለእይታ ቀረበ

Image
የኮሎን ከተማ ለኣለም የጥበብ ሪዕዬ ትይዕንት ሰሞኑን በሯን ክፍት ኣድርጋ ከተለያዩ የኣለም ክፍሎች የምጎርፉትን ጥንታዊ እና ባህላዊ የጥበብ ስራዎች በመቀበል ላይ ትገኛለች። በሪዕዬ ትይእንቱ ላይ ዘመን ጠገብ ቁሳቁሶች ለእይታ የቀረቡ ሲሆን፤ ከቀረቡ ቁሳቁሶች መካከል በ 19 ኛው እና በ 20 ኛው ክፍለ ዘመን የተፈበረኩ እና በህዝብ ዘንድ ተወዳጅነትን ያተረፉ መኪኖች እና የስዕል ስራዎች ይገኙበታል። ለኣብነት ያህል ከቀረቡት የስዕል ስራዎች መካከል በጀመናዊው የኤክፕሬሽን ሰዓል ኣርቲስት ማክስ ፔሄስታይን የተሳሉት ሁለት ስዕሎች በሽያጭ የቀረቡ ሲሆን ዋጋቸውም 1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዬሮ መሆኑ ታውቋል። የወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ ዘጋብ የዩሮ ኒውስን ጠቅሶ እንደዘገባው፤ በኣማካይ 100 የምሆኑ ጋሌሪዎች እና ደላሎች ከኣውሮፓ እና ከተቀረው ኣለም ሃሰባሰቧቸው ማስተርፒስ ስራዎች በተጨማሪ ከኢትዮጵያን እና ኬኒያ የተሰባሰቡ ባህላዊ ቁሳቁሶች ለእይታ የቀረቡ ሲሆን የሲዳማው ባርኮ ከእነዚሁ መካከል ኣንዱ ነው።