Posts

OMN: Amharic Interview with Sidama activist Bekele Wayu (part one) Novem...

Image

Algeria record fifth straight win v Ethiopia

Image
Algeria made it five wins from five in their 2015 African Cup of Nations qualifying campaign with their 3-1 victory over Ethiopia at the Stade Mustapha Tchaker in Blida on Saturday evening. Goals from Sofiane Feghouli, Riyad Mahrez and Yacine Brahimi moved Algeria up to 15 points, the only team to have won all their games thus far. Algeria head coach Christian Gourcuff made two changes to the side that beat Malawi last time out, with Med Lamine Zemmamouche and Saphir Taider replacing Rais M’Bolhi and Nabil Bentaleb respectively, while Bidvest Wits and Ethiopia striker Getaneh Kebede missed the game through suspension. The hosts put Ethiopia under immense pressure in the opening 10 minutes of the encounter, with Rafik Halliche notably heading just wide. It was Ethiopia, though, who opened the scoring completely against the run of play in the 22nd minute through Omod Okwory, who picked up the ball near the halfway line before bursting forward and hitting a right-footed effort

አቶ አስፋው ዴንጋሞን የኢትዮጵያ ፔትሮሊየም ልማት ድርጅትን በዋና ዳይሬክተርነት እንዲመሩ ተሾሙ

Image
 አቶ አስፋው ዴንጋሞን የኢትዮጵያ ፔትሮሊየም ልማት ድርጅትን በዋና ዳይሬክተርነት እንዲመሩ ሾመዋቸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ፔትሮሊየም ልማት ድርጅት አዲስ የተቋቋመ የመንግሥት የልማት ድርጅት ነው፡፡ ድርጅቱ በኢትዮጵያ የተፈጥሮ ጋዝና ዘይት ልማት ሥራ ውስጥ እንዲሳተፍ ታቅዶ የተመሠረተ መንግሥታዊ ድርጅት ነው፡፡  አቶ አስፋው ዴንጋሞ የውኃ ሀብት ሚኒስትር ሆነው ማገልገላቸው ይታወሳል፡፡ በመቀጠልም በኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን የዋና ዳይሬክተሩ አማካሪ ሆነው አገልግለዋል፡፡ Read more at: www.ethiopianreporter.com

የፖለቲካ ፓርቲዎች የሕዝብ ትዝብት ውስጥ እንዳይወድቁ

Image
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጽሕፈት ቤት በመጪው ግንቦት ወር የሚካሄደውን አምስተኛ ዙር አገር አቀፍ የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ይፋ አድርጓል፡፡ ቦርዱ የፊታችን ግንቦት የሚካሄደውን አገር አቀፍ ምርጫ ለማካናወን የሚያስፈልጉ ቅድመ ዝግጅቶች በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡ በዚህ መሠረት የፖለቲካ ፓርቲዎች ቅስቀሳ የሚያደርጉበት፣ መራጮች የሚመዘገቡበት፣ ምርጫው የሚካሄድበትና ውጤቱ ይፋ የሚደረግበት የጊዜ ሰሌዳ ታውቋል፡፡  ምርጫው ሊካሄድ ሰባት ወራት የቀሩት ሲሆን፣ በአገሪቱ ያሉት የፖለቲካ ፓርቲዎች በዚህ ምርጫ ለመሳተፍ፣ የቻሉትን ለማሸነፍ እንቅስቃሴ የሚያደርጉበት ወቅት ነው፡፡ በመሆኑም ፓርቲዎች ዕጩዎቻቸውን የሚያዘጋጁበት፣ የምረጡኝ ቅስቀሳ ለመጀመር የቤት ሥራቸውን የሚያጠናቅቁበትና ሌሎች አስፈላጊ ነገሮችን የሚያሟሉበት ጊዜ ነው፡፡ ወቅቱ የምርጫ በመሆኑ የአገሪቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሕዝብ ትዝብት ውስጥ እንዳይወድቁ ሊጠነቀቁ ይገባል፡፡  እስካሁን አራት አገር አቀፍ ምርጫዎች በአገሪቱ የተካሄዱ ቢሆንም፣ ምርጫ 97 በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ጥሎት ያለፈው ትዝታ ግን የሚረሳ አይደለም፡፡ በአገሪቱ ያለው የዴሞክራሲ ሥርዓት ታዳጊ የሚባል ቢሆንም፣ በምርጫ 97 ታይቶ የነበረው የተስፋ ጭላንጭል የዴሞክራሲ ሥርዓቱን ዕድገት ያፋጥነዋል ተብሎ ይታመን ነበር፡፡ ያለመታደል ሆኖ በወቅቱ የነበረው የሕዝብ እንቅስቃሴ በቀጣዩ የ2002 ዓ.ም. ምርጫ ሳይታይ ቀረ፡፡ ሳይሟሟቅና ግለቱ ሳይሰማን አለፈ፡፡ ለዚህ ደግሞ በአገሪቱ ውስጥ የነበሩት ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ተጠያቂዎች ናቸው፡፡  በቅርቡ እንደሰማነው ዘጠኝ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ትብብር መሥርተዋል፡፡ ትብብሩን የመሠረቱት የተቃዋሚ ፓርቲዎች የትብብሩ ዓላማ ነፃ፣ ፍትኃዊና ተዓማኒ ምርጫ ለማ

የዋሊያዎቹ ዕጣ ፈንታ ዛሬ በአልጀሪያ ይወስናል

Image
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወሳኙን የማጣሪያ ጨዋታውን ከአልጀሪያ ጋር ለማድረግ 20 ተጨዋቾችን በመያዝ ወደ ስፍራው አቅንቷል፡፡ ዋሊያዎቹ በጨዋታው ሙሉ ሶስት ነጥብ ይዘው መመለስ ካልቻሉ አስተናጋጁ ሀገር ያልታወቀውን የአፍሪካ ዋንጫ ለመሳተፍ ዕድሉ አይኖራቸውም፡፡ ዋሊያዎቹ አልጀሪያን ማሸነፍ ከቻሉና ማላዊ ማሊን ነጥብ ማሳጣል ከቻለች ለዋሊያዎቹ  መልካም ዜና ይሆናል፡፡ አሰልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ በአልጀርስ ድል ካልቀናቸው ግን የዋሊያዎቹ የ2015 የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ ከማጣሪያ ጨዋታ ያልዘለለ ይሆናል፡፡ ከምድቡ 12 ነጥብ በመሰብሰብ አስቀድማ ማለፏን ያረጋገጠችው አልጀሪያ ጨዋታውን ለመርሃ ግብር ስትል ታደርጋለች፡፡ አልጀሪያ ባለፈው መስከረም አዲስ አበባ ላይ ዋሊያዎቹን 2ለ1 ማሸነፏ ይታወሳል፡፡ ዋሊያዎቹ ባለፈው አልጀሪያን ከገጠመው ቡድን የ8 ተጨዋቾች ለውጥ አድርገዋል፡፡ ከእነዚህ መካከል የፊት መስመር አጥቂዎቹ ሳልሃዲን ሰኢድ በጉዳት እንዲሁም  ጌታነህ ከበደ በቅጣት እና በአሰልጣኙ ዕይታ ብቁ ያልሆነው አማካኙ አዳነ ግርማ ይገኙበታል፡፡ አሰልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ ባለፈው ሳምንት በኡጋንዳ 3ለ0 ከተሸነፉ በኋላ 5 ተጨዋቾችን ቀንሰዋል፡፡ ዴቪድ በሻህ፣ ሄኖክ ካሳሁን፣ ፉዋድ ኢብራሂም፣ ምንተስኖት አዳነ፣ ኤፍሬም አሻሞ እና እንዳለ ከበደ     የተቀነሱ ተጨዋቾች ናቸው፡፡ የቅዱስ ጊዮርጊሱ ፋሲካ አስፋው ዋሊያዎቹን የተቀላቀለ አዲስ አባል ሆኗል፡፡ በጨዋታው ኡመድ ኡክሪ በጉዳትና በቅጣት የሳሳውን የፊት መስመር በበላይነት እንደሚመራው ይጠበቃል፡፡ ጨዋታው ዛሬ ምሽት በሱፐር ስፖርት 3 በቀጥታ ይተላለፋል፡፡ ምንጭ፦ ኢብኮ