Posts

ሐዋሳን እንዳየኋት

Image
ሐዋሳን እንዳየኋት በአገራችን ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ በማደግ ላይ ካሉ ከተሞች ውስጥ አንዷ ሐዋሳ ናት፡፡ የኢንዱስትሪ ዞን ከተማ ከሆኑትም አንዷ ናት፡፡ የውጭ አገርና የአገር ውስጥ ጎብኝዎች በስፋት የሚስተናገዱባት በሆነችነችው ሐዋሳ ከተማን በጎበኘሁ ጊዜ  የሚከተሉትን ችግሮች መመልከት ችያለሁ፡  ይኸውም እንዲሰጣቸው የሚፈልጉትን የገንዘብ መጠን ወስነው ካልሰጣችሁኝ የሚሉ ለማኞች እንዲሁም የቆሙ መኪናዎች ዕቃ ሥርቆት እየተስተዋለ ይገኛል፡፡ ይህ ድርጊት በጊዜ ቁጥጥር ሥር ካልዋለ፣ ለከተማዋ ዕድገትና መሻሻል እንዲሁም የተሻለ ገቢ ለማግኘት መሰናክል ስለሚሆን የተከማው አስተዳደር እነዚህን ችግሮች ትኩረት ሰጥቶ ፈጣን መፍትሔ  መስጠት ወይም ዕርምጃ መውሰድ ይገባዋል እላለሁ፡፡ (አማን ኑሪ፣ ከአዲስ አበባ) ቤቶች ኤጀንሲ ለሹማምንት ቤት የሚሰጠው ከማን ወስዶ ነው? ‹‹የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ ለተሿሚዎች ቤት እንዲያቀርብ ታዘዘ፤ የሚያቀርበው ቤት ባለመኖሩ ደንበኞች ላይ ትኩረት ተደርጓል፡፡›› በማለት የሪፖርተር የእሑድ መስከረም 25 ቀን 2007 ዓ.ም. ዕትም፣  የውስጥ ዜና አስነብቧል፡፡ ይህንን ዜና ተንተርሼ ከፍትሕ አካላት ራሱን ነጥሎ ኢፍትሐዊ የሆነ ዕርምጃን በመውሰድ የሚታወቅን ተቋም ይባስ ብሎ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ በራሱ አስፈጻሚዎች ነዋሪውን ከቤቱ እንዲያስወጣ ሥልጣን ስለተሰጠው የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ የማውቃቸውን እውነታዎችና እንደዚህ ዓይነቶቹ ኢፍትሐዊ አካሄዶች በዜጎችና በመንግሥት ላይ የሚያሳድሩት ጥሩ ያልሆኑ ተፅዕኖዎችን ለማሳየት ግድ ብሎኛል፡፡ የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ ከከተማ ትርፍ መሬትና ቤት አዋጅ ጋር በተገናኘ የተወረሱ ቤቶችን ማለትም ኪራያቸው ከመቶ ብር በላይ የሆኑትን ቤቶች እንዲቆጣጠርና የቤት አቅር

በፖሊስ ለሚፈጸሙ የመብት ጥሰቶች ምላሽ የሚሰጥ ሥርዓት አለን?

Image
ጎሮ ሰፈራ አካባቢ ለወትሮው በሚታጠፍበት ቦታ ላይ ሲደርስ ከፊት ለፊቱ ያሉ ተሽከርካሪዎች ሲፈተሹ ያያል፡፡ ስለዚህ ትራፊክ ፖሊሶቹ የሦስተኛ ወገን ኢንሹራንስ ጨምሮ ስለመሟላታቸው ለሚቀርቡላቸው ጥያቄ አሽከርካሪዎች ሲመልሱ ተራው ደርሶት በሒደቱ ውስጥ ለማለፍ መጠባበቅ ጀመረ፡፡ መጠባበቁ ከምክንያታዊ ጊዜ ሲያልፍ ወጣቱ ትራፊክ ፖሊሶቹ እንዲያስተናግዱት መጣራት ጀመረ፡፡ ሰሚ አጥቻለሁ ብሎ በማሰቡ ታጥፎ ለመንቀሳቀስ መንገድ ጀመረ፡፡  ድንገት ግን ‹‹ነውር አይደለም እንዴ?›› የሚል ጥያቄ ድምፁን ከፍ አድርጎ ከኋላ ከሚከተል የትራፊክ ፖሊስ ሰማ፡፡ ወጣቱም ተሽከርካሪውን ካቆመ በኋላ ‹‹ነውሬ ምንድን ነው?›› ሲል አጠገቡ የቆመውን ትራፊክ ፖሊስ ጠየቀው፡፡ ለጥያቄው ምላሽ መስጠቱን ወደ ጎን በማድረግ የሚፈልጋቸውን ሰነዶችና ጥያቄዎች አከታትሎ መጠየቅ ጀመረ፡፡ ወጣቱ የተጠየቀውን ሁሉ ካሟላ በኋላ በድጋሚ የሠራው ነውር ምን እንደሆነ ለማወቅ እንደሚፈልግ ገለጸ፡፡ መንጃ ፈቃዱን ጨምሮ ሌሎች መረጃዎችን ለትራፊኩ ሰጥቶ የነበረው ወጣት ሳያስበው ፊቱ ላይ ተወረወሩበት፡፡ የሁለት ዓመት ሕፃን ልጁና ባለቤቱን ይዞ የነበረው ወጣት በፍጥነት ከተሽከርካሪው በመውጣት ትራፊክ ፖሊሱን ተከትሎ ‹‹ለምን እንዲህ ታደርጋለህ?›› ሲል ጠየቀ፡፡ አሁንም ያልጠበቀው ምላሽ ገጠመው፡፡ ትራፊክ ፖሊሱ በቦክስ መታው፡፡  ይህ ሁሉ ድርጊት ሲፈጸም የሚመለከቱት የአካባቢው ሰዎች ብቻ ሳይሆኑ ሌሎች የትራፊክ ፖሊስ ባልደረባዎችም ጭምር ነበሩ፡፡ ወጣቱ ትራፊክ ፖሊሱን ለመክሰስ እንደሚፈልግ በመግለጽ አሁንም መከተሉን አላቆመም፡፡ በአካባቢው የተሰባሰቡት አራት ተጨማሪ የትራፊክ ፖሊሶች ምን እንደተከሰተ እንኳን ለማጣራት ሳይሞክሩ ወጣቱን ይበልጥ በማዋከብና በመገፈታተር መንገዱን እንዲቀጥ

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

Image
የመንግሥት ስልጠና የምርጫ ቅስቀሳ አካል ነው ብሏል  የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ለምን ወጣ መባሉ ተገቢ አይደለም - ምርጫ ቦርድ ምርጫ ቦርድ ከኢህአዴግ ተፅዕኖ ሙሉ ለሙሉ ነፃ መሆኑ ሳይረጋገጥና የምርጫ አፈፃፀም ችግሮች ሳይወገዱ የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ለማወጅ መዘጋጀቱ ተገቢ አይደለም ሲል ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ የሚመሩት ኢማዴ-ደህአፓ ተቃወመ፡፡ መንግስት፤ የዩኒቨርሲቲ መምህራንና ተማሪዎችን ጨምሮ ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየሰጠ ያለው ስልጠና የምርጫ ቅስቀሳ አካል ነው ሲልም ፓርቲው ኮንኗል፡፡  የኢትዮጵያ ማህበረ ዴሞክራሲ ደቡብ ህዝቦች አንድነት ፓርቲ ሰሞኑን ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ባስገባው ግልፅ ደብዳቤ፤ ያለፉት አገር አቀፍና የአካባቢ ምርጫዎች ከመካሄዳቸው በፊት በምርጫ ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው ዙሪያ ኢህአዴግ ከተቃዋሚዎች ጋር የሚወያይበት መድረክ እንዲዘጋጅ በተደጋጋሚ ብንጠይቅም እስካሁን ከቦርዱ የተሰጠ ተግባራዊ ምላሽ የለም ብሏል፡፡  ሃገሪቱ “በአንድ አውራ ፓርቲ” ብቸኛ ቁጥጥር ስር መውደቋ አደገኛና አሳሳቢ ነው ያለው ፓርቲው፤ የመድብለ ፓርቲ ስርአት የመገንባት ተስፋችን ጨርሶ እንዳይከስም ቦርዱ ሃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት አሳስቧል፡፡ ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ የሚካሄድበትን ሁኔታ ለመፍጠር ገዥው ፓርቲና ሃቀኛ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚወያዩበት መድረክ እንዲያመቻች በህግ ስልጣን የተሰጠው ምርጫ ቦርድ የገባውን ቃል በማጠፍ መድረኩን ሳያመቻች የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማዘጋጀቱ ፋይዳ የለውም ብሏል - ፓርቲው፡፡  ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ በተሻሻለው የምርጫ ህግ፣ ለቦርዱ የተሰጠውን የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ መድረክ የማስተባበር ስልጣን ለመቀማት ታማኝ ፓርቲዎችን በተቃዋሚ ስም አሰባስቦ “የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ መድረክ” በመፍጠር የምርጫ ውድድር አሯሯጭ አሰልፏል ሲ

ዛምቢያ የመጀመሪያውን ነጭ መሪ ጊዚያዊ ፕሬዝዳንት አድርጋ ሾመች

Image
አዲስ አበባ ጥቅምት 20/2007 ዛምቢያ ፕሬዝዳንቷን በሞት ካጣች በኋላ የአገሪቱ ካቢኔ አዲስ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት መሾሟን ዘ ኒዮርክ ታይምስ ዘገበ። የአገሪቱ ካቢኔ ትናንት ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ  የአገሪቱ  ምክትል ፕሬዝዳንት የነበሩትን ጌይ ስኮትን በጊዜያዊነት ሰይሟል። የእንግሊዙ ዜና ማሰራጫ ቢቢሲ የዛምቢያን መከላከያ ሚኒስትር ኢድጋር ሉንጉን እንደዘገበው ደግሞ የዘር ሃረጋቸው ከስኮትላንድ የሚመዘዙት ሚስተር ስኮት ዛምቢያ ከቅኝ አገዛዝ ነጻ ከወጣች በኋላ የአገሪቱ የመጀመሪያው ነጭ የአገር መሪ ያደርጋቸዋል። ጌይ ስኮት የፕሬዝዳንትነት ምርጫው በ90 ቀን ውስጥ እስከሚካሄድ ድረስ በተጠባባቂነት አገሪታን ይመራሉ። የ70 ዓመቱ አዛውንት ጌይ ስኮት ከዚህ ቀደም አርሶ አደር፣የግብርና ባለሙያና የምጣኔ ሃብት ባለሙያ ሆነው መሰራታቸውን የቢቢሲ ዘገባ አመልክቷል። በተጨማሪም ሚስተር ስኮት በተለያዩ ሃላፊነቶች፣ የሚኒስቴር ቦታዎችና እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር  ከ2011 እስከ 2014 በምክትል ፕሬዝዳንትነት አገልግለዋል። የሚስተር ስኮት እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በ1994 የደቡብ አፍሪካ መሪ የነበሩት ኤፍ ዴ ክለርክ ከስልጣን ከወረዱ በኃላ ከሳሃራ በታች የመጀመሪያው ነጭ መሪ ሆነው መመረጥ በአለም አቀፍ ብዙሃን መገናኛ ተቋማት አዎንታዊና አሉታዊና አስተያዬቶችን እየሰጡ ነው። ዛምቢያን ለ3 አመታት የመሩት የ77 አመቱ ሚካኤል ሳታ ከትናት በስቲያ በሞት መለየታቸው ይታወሳል። ምንጭ፦ ኢዜኣ

በቀርከሃ ተክል ላይ ያተኮረ አለማቀፍ ጉባኤ በቀጣዩ ሳምንት በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

Image
በግብርና ሚኒስቴር የዘላቂ መሬት አያያዝ  ፕሮግራም አማካሪ አቶ መላኩ ታደሰ  እንዳሉት፥ ኢትዮጵያ ለቀርከሀ ምርት ያላት ምቹነት ጉባኤውን እንድታስተናግድ አስመርጧታል። በጉባኤው የግሉ ዘርፍ ለቀርከሃ ልማት በሚኖረው ድርሻ እንዲሁም ቀርከሃ ለተፋሰስ ልማት በሚኖረው ሚና  ዙሪያ ጥናቶች ቀርበው ውይይት ይደረጋል። ቀርከሀ በኢንዱስትሪው ዘርፍ ለኢኮኖሚ እድገትና የህብረተሰቡን የኑሮ ደረጃ  ለመለወጥ የሚኖረው አስተዋጽኦም የጎላ መሆኑን ነው አቶ መላኩ የተናገሩት። ኢትዮጵያ 1 ሚሊዮን ሄክታር ላይ ያረፈ የቀርከሃ ምርት ያላት ሲሆን፥ ከአፍሪካ በአጠቃላይ ካለው ምርት 67 በመቶውን ትሸፍናለች፡፡ ምንጭ፦   ኤፍ.ቢ.ሲ.