Posts

የጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የአዙሳ ዩኒቨርሲቲ የክብር ስነ-ስርዓት መሰረዝና ያስከተለው ውዝግብ

Image
ነሐሴ 6 2006ዓም የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ የአማርኛዉ ቋንቋ አገልግሎት በኢትዮጵያ መንግሥትና በውጭ ሀገር የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን (ዳያስፖራ) መካከል ያለዉን ግንኙነት የገመገመ ዝግጅት ማቅረቡ ይታወሳል። በዝግጅቱ ዉስጥ ከተካተቱት በርካታ ርእሶች መካከል የካሊፎርኒያው አዙሳ ፓሲፊክ ዩኒቨርሲቲ ለጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ ሊሰጥ አቅዶ የነበረዉ የክብር ስነስርዓት የሰረዘበት ምክንያት አንዱ ነበር። ርዕሰ ጉዳዩን አስመልክቶ የተጠናከረ ዘገባ በአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ መሰራጨቱን ተከትሎ፤ አንዳንድ የአሜሪካ ድምጽ ጋዜጠኞች “ሆን ብለዉ እዉነትን አዛብተዋል።” የኢትዮጵያ ሕዝብ “የዳያስፖራዉን ድምጽ እንዳይሰማ አፍነዋል” የሚሉና በተለይም አዙሳ ዩኒቬርሲቲ ሽልማቱን እንዲሰርዝ ዘመቻ ካደረጉት አንዱ ጋዜጠኛና የፖለቲካ አክቲቪስት አቶ አበበ ገላዉ ቪኦኤ ላይ ያቀረባቸዉ ክሶች በራሱ ድረ ገጽ አዲስ ድምጽ፣ በኢሳትና በሌሎች የዳይስፓራ መገናኛ ብዙሃን ሲሰራጭ ሰንብቷል። ከአቶ አበበ ገላዉና የዋሽንግተን ዲሲ ኢትዮጵያ ማህበረሰብ ጣምራ ግብረ-ሃይል ከተባለው የዳያስፖራ ቡድን ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ አስተዳደር የተቃዉሞ ደብዳቤዎች ደርሰዋል። የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮም በዝግጅቶቹ ላይ ከማንኛውም ወገን የሚቀርቡ ተቃውሞዎችንና ትችቶችን ትኩረት ሰጥቶ ያጣራል። በዚህም መሰረት የጣቢያው ሃላፊዎች የፕሮግራሞችን ይዘት የሚገመግም ገለልተኛ አጣሪ ቡድን መድበው፤ የፕሮግራሙን ይዘት አስመርምረዉ ለአቶ አበበ ገላዉ ኦፊሴል ምላሽ ሰጥተዋል። ቀጥለን በምናቀርበዉ ዝግጅት የነሐሴ 6ቱን ዘገባ ዋና ዓላማና የተጠናቀረበትን ሁኔታ፣ የገለልተኛውን አጣሪ ቢሮ ድምዳሜዎች፣ እንዲሁም ከፕሮግራሙ ሰፊ ክፍል በአንድ ነጥብ ላይ የተፈጠረዉን ዉዥንብር ግልጽ ካደረግን በኋላ፤ አሻሚ የሆኑ

የተሻሻለው የመኖሪያ ቤት ኅብረት ሥራ ማኅበራት መመርያ ተቃውሞ ገጠመው

ሰሞኑን ተሻሽሎ በቀረበው የመኖሪያ ቤት ኅብረት ሥራ ማኅበራት መመርያ ላይ ከአስተዳደሩ ከፍተኛ ባለሥልጣን ጋር የተወያዩት ቤት ፈላጊዎች ተቃውሞአቸውን ገለጹ፡፡  የማኅበራቱ ተወካዮች ቅሬታቸውን የገለጹት፣ ከአንድ ዓመት መጉላላት በኋላ ተሻሽሎ የቀረበው መመርያ ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትልና የተሻረው መመርያ የሰጠውን ጥቅም የሚያስቀር ነው በሚል ነው፡፡  ጥቅምት 6 ቀን 2007 ዓ.ም. በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰለሞን ኃይሌ፣ የከንቲባ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሰግድ ጌታቸውና የንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሺሰማ ገብረ ሥላሴ ከማኅበራቱ ተወካዮች ጋር በከተማው ምክር ቤት አዳራሽ ለግማሽ ቀን ውይይት አድርገዋል፡፡  በተካሄደው ድንገተኛና ያልተጠበቀ ስብሰባ የማኅበራቱ ተወካዮች ከባለሥልጣናቱ ጋር ባካሄዱት ስብሰባ ስምምነት ላይ መድረስ ሳይችሉ ቀርተዋል፡፡ የማኅበራቱ ተወካዮች ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ አዲሱ መመርያ ቀደም ሲል ተስፋ ጥለው የተደራጁበትን  የሚሸረሽር ነው፡፡  አዲሱ መመርያ ቀደም ሲል ወጥቶ ከነበረው መመርያ ጋር በመሠረታዊ ሐሳቦች ላይ ልዩነት አምጥቷል፡፡ ቀደም ሲል የነበረው መመርያ ለፕሮግራሙ የሚቀርበው መሬት ከሊዝ ነፃ እንደሆነ ይገልጻል፡፡ ነገር ግን በመልሶ ማልማት ቦታዎች ነዋሪዎች የሚነሱ ከሆነ ማኅበራቱ ካሳ እንሚከፍሉ ተገልጾ ነበር፡፡ ነገር ግን ይህ አሠራር ቀርቶ መሬት በሊዝ እንደሚሰጥ በመጥቀሱ አዲሱ መመርያ የሐሳብ ለውጥ አምጥቷል፡፡  ሌላኛው ለውጥ መኖሪያ ቤቶቹ የሚገነቡት በሁለት አግባብ ነው፡፡ የመጀመሪያው በማስፋፊያ ቦታዎች ‹‹ታውን ሐውስ›› የተሰኘ የመኖሪያ ቤት ዓይነት እንደሚገነባ፣ በመልሶ ማልማት ቦታዎች ደግሞ ባለአምስት ፎቅ አፓርታማ እንደሚገነባ ነበር፡፡ ነ

ሲዳማን ጨምሮ በደቡብ ክልል የማጅራት ገትር በሽታ መከላከያ ክትባት እየተሰጠ ነው

Image
Photo: Wikipedia   በደቡብ ክልል የማጅራት ገትር በሽታ መከላከያ ክትባት እየተሰጠ ነው ሀዋሳ ጥቅምት 8/2007 በደቡብ ክልል ከ11 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ተደራሽ የሚያደርግ የማጅራት ገትር በሽታ መከላከያ ክትባት የመስጠት ዘመቻ ዛሬ መጀመሩን የክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ ገለጸ፡፡ በቢሮው ጤናና ጤና ነክ ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ዋና የስራ ሂደት ባለቤት አቶ ጀማል ሀሰን እንደገለጹት ክትባቱ በዘመቻ የሚሰጠው ከዛሬ ጀምሮ ለሚቀጥሉት ለአስር ቀናት ነው፡፡ በዚህ በክልሉ 11 ዞኖችና አራት ልዩ ወረዳዎች ዕድሜያቸው ከ1 እስከ 29 ዓመት የሆናቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ክትባቱ እንዲያገኙ ይደረጋል፡፡ አቶ ጀማል እንዳስረዱት  ሞቃታማ ፣ደረቅና ነፋሻማ የሆነውን የአየር ንብረት ተከትሎ በወረርሽኝ መልክ ሊከሰት የሚችለውን የማጅራት ገትር በሽታ አስቀድሞ ለመከላከል ክትባቱ ይሰጣል ፡፡ ከሁለት አመት በፊት በክልሉ ቤንች ማጂ ፣ ሸካ ደቡብ ኦሞና ካፋ ዞኖች የመጀመሪያ ዙር የመከላከያ ክትባት መሰጠቱን አመልክተዋል፡፡ ሁለተኛው ዙር የማጅራት ገትር በሽታ መከላከያ ክትባት ደግሞ በቀሪዎቹ የክልሉ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች በዘመቻ መጀመሩን ተናግረዋል፡፡ ዘመቻውን ለማሳካትም  በክትባቱ ለሚሳተፉ በየደረጃው ለሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ስልጠና መሰጠቱም ተመልከቷል፡፡ ክትባቱ በተመረጡ ትምህርት ቤቶች በጤና ተቋማትና ህዝብ በብዛት በሚገኝባቸው አካባቢዎች ማዕከላት እንደሚሰጥና ለክትባቱ አስፈላጊ የሆኑ መድሀኒቶችና ሌሎች ተጓዳኝ ቁሳቁሶች መሰራጨታቸውም  የስራ ሂደት ባለቤት ገልጸዋል፡፡ ህብረተሰቡም ይህንን አውቁ በየአካባቢው ባሉ የክትባት ማዕከላት በመገኘት ልጆቹን ማስከተብ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ በዚህ ዘመቻም በክልሉ የሚ

በኮንፈረንሱ የኢትዮጵያን ቡና ለማሰተዋወቅ ታስቧል

Image
በሶስተኛው ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ቡና ኮንፈረንስ የአገሪቱን ቡና በስፋት በማስተዋወቅና የጥራት ደረጃውን በሚያሳድጉ ጉዳዮች ላይ ትኩረት እንደሚደረግ የኢትዮጵያ ቡና ላኪዎች ማህበር አስታወቀ። የማህበሩ የሥራ አመራር ቦርድ ፕሬዝዳንት አቶ ሁሴን አድራው እንደተናገሩት ማህበሩ በሚያዘጋጀው ተመሳሳይ ጉባኤ በአለም አቀፍ ደረጃ የትላልቅ ቡና ገዥ ኩባንያዎችንና ከቡናዘርፍ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ዓለም አቀፋዊና አህጉራዊ ድርጅቶችን ትኩረት መሳብ ተችሏል። ከጥቀምት 27 ጀምሮ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ቡና ኮንፈረንስም አገሪቱ በቡናው ዘርፍ ያላትን ሚና በማሳየትም ትልቅ የገጽታ ግንባታ መድረክ ይሆናልም ብለዋል። በኮንፈረንሱም አገሪቱ ወደ ውጭ የምትልከው ቡና ጥራት ደረጃን በመገምገም ደረጃውን ይበልጥ ለማሻሻል በሚያስችሉ ነጥቦች ላይ ትኩረት ይደረጋል። በኮንፈረንሱ ከቻይና፣ ከደቡብ ኮሪያ፣ ከህንድ እና ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ታዳሚዎች ይፈሉበታል ተብሎ እንደሚጠበቅ ኢዜአ ዘግቧል።  

ፓርቲዎች በምርጫ ማስፈጸሚያ የጊዜ ሰሌዳ ላይ ውይይት ጀመሩ

Image
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በ2007 ዓ.ም በሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ አፈጻጸም የጊዜ ሰሌዳ ረቂቅ ላይ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት አካሄደ። ለ5ኛ ጊዜ በመጪው ግንቦት የሚካሄደው አገራዊ ምርጫ አፈጻጸም የጊዜ ሰሌዳ ረቂቅ ላይ ከ23 አገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች ጋር ነው ውይይቱ የተካሄደው። የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መርጋ በቃና እንዳሉት ውይይቱ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ቦርዱ ባዘጋጀው ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት እንዲንቀሳቀሱ የጋራ መግባባት ለመፍጠር ከፍተኛ እገዛ ይኖረዋል።   በምርጫ ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳ የምክክር መድረክ ላይ ከተገኙት የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ ፕሬዝዳንት አቶ ተሻለ ሰብሮ ረቂቁ ሊያሰራ የሚችል ተስማሚ የጊዜ ሰሌዳ መሆኑን ተናግረዋል። የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዝዳንት አቶ አየለ ጫሚሶ በበኩላቸው ረቂቅ የምርጫ ድርጊት መርሃ ግብሩ መካተት ያለባቸው ጉዳዮች የያዘ በመሆኑ ፓርቲያቸው የተወሰኑ መስተካከል ያለባቸው ጉዳዮች እንዳሉ አስታውቀዋል። የኢህአዴግ ተወካይ የሆኑት አቶ ደስታ ተስፋው በበኩላቸው "የ2007 ዓ.ም የምርጫ አፈጻጸም የድርጊት መርሃ ግብር ረቂቅ የሚያሰራ እና በተቀመጠው መሰረት ወደ ስራ የሚያስገባ ረቂቅ ሰነድ ነው" ብለዋል። የአዲስ ትውልድ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ    አስፋው ጌታቸው    ምርጫ ቦርድ እንደዚህ አይነት የውይይት መድረክ ማዘጋጀቱ ለአገሪቱ የዲሞክራሲ ባህል ግንባታ ሂደት ትልቅ ሚና እንዳለው ገልጸው የቀረበውን ረቂቅ እን ደሚቀበሉት ተናግረዋል።   የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መርጋ ከተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች በረቂቁ ላይ በሰጡት አስተያየት የመራጮች ምዝገባ፤ የፓርቲዎች