Posts

የሁለቱ ምክር ቤቶት 4ኛው ዙር የመጨረሻው የስራ ዘመን የጋራ መክፈቻ ስነ ስርዓት ነገ ይካሄዳል

Image
አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) የህዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የ4ኛው ዙር የመጨረሻው የስራ ዘመን  የጋራ መክፈቻ ስነ ስርዓት ነገ ይካሄዳል። በመክፈቻ ስነሰርዓቱ ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ ንግግር ያደርጋሉ። በፕሬዚዳንቱ ንግግርም የ2007 ዓ.ም ዋና ዋና የመንግሰት የትኩረት አቅጣጫዎች ይዳሰሳሉ ተብሏል። ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክው፥ በመክፈቻ ስነስርአቱ ላይ የሁለቱ ምክር ቤቶች አባላትና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይታደማሉ። ስነ ስርአቱ በቴሌዥንና በሬድዮ በቀጥታ ይተላለፋል።

ግራ ያጋባው የኢትዮጵያ የአዘጋጅነት ጥያቄ

Image
ከሰሞኑ የአብዛኛው የስፖርት ቤተሰብ መነጋገሪያ የሆነው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የአፍሪካ ዋንጫን ማዘጋጀት አለመቻል እንደ አንድ አገራዊ አጀንዳ እያነጋገረ ይገኛል፡፡ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) አዲስ አበባ ላይ ጠቅላላ ጉባኤውን ማሰናዳቱን ተከትሎ አብዛኛው የስፖርት አፍቃሪ ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. የ2017 የአፍሪካ ዋንጫ የአስተናጋጅነቱ ዕድል እንዲሰጣት ለካፍ ያቀረበችው ጥያቄ እንድትጠቀምበት ይረዳታል ተብሎ ቢጠበቅም፣ የኋላ ኋላ ግን ‹‹አቅም የለንም›› በሚል ምክንያት ፍላጐቷን ወደ ጎን ማድረጓ ከፌዴሬሽኑ ተሰምቷል፡፡ ‹‹ሲጀመር ምን ያህል አቅም ኖሮን ነበር?›› ሲል የሚጠይቀው የእግር ኳስ ቤተሰብ አገሪቱ የ2017ቱን የአፍሪካ ዋንጫ ለማዘጋጀት ዕድሉ እንዲሰጣቸው ከጠየቁ አገሮች አንዷ ሆና መቅረቧ አስገራሚና በዕቅድ ያለመመራት አሠራር መኖሩን በግልጽ እንደሚያመለክት ያወሳሉ፡፡ ካፍ ባለፉት ሳምንታት በአዲስ አበባ ባደረገው ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ከተመለከታቸው አጀንዳዎች የ2019 የአፍሪካ ዋንጫ ለካሜሮን፣ የ2021 ለአይቨሪኮስት፣ የ2023 ለጊኒ የአስተናጋጅነቱን ዕድል የሰጠበት ይጠቀሳል፡፡ የ2017ቱን ቀደም ሲል የአስተናጋጅነቱን ዕድል ለሊቢያ የተሰጠ መሆኑ ቢታመንም፣ ወደ ኋላ ላይ ግን በአገሪቱ በተፈጠረው አለመግባባት ምክንያት ካፍ ዕድሉን ለሌሎች አገሮች አሳልፎ እንደሚሰጥ ይፋ ማድረጉን ተከትሎ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ አልጄሪያና ዚምባቡዌ የ‹‹እናዘጋጃለን›› ጥያቄያቸውን ለካፍ አስገብተዋል፡፡ የመጨረሻው ቀን ገደብም መስከረም 30 ቀን መሆኑም ይታወቃል፡፡ ፌዴሬሽኑ ኢትዮጵያ ቀደም ሲል ሦስት የአፍሪካ ዋንጫዎች ማስተናገዷን በመጥቀስ፣ በአህጉር ደረጃ ከፍተኛ ግምት የሚሰጠውን የ2017ቱን የአፍሪካ ዋንጫ ለማስተናገድ በ

ሳንሻይን ኮንስትራክሽን የሞሮቾ፧ዲምቱና ቢታና መንግድ ልገነባ ነው

Image
የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ሙሉ በሙሉ መንግሥት በሚመድበው ወጪ ይገነባሉ የተባሉ የሁለት መንገድ ፕሮጀክቶች ግንባታዎችን ለሁለት አገር በቀል ኮንትራክተሮች ከ2.2 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ዋጋ እንዲገነቡ ሰጠ፡፡  ሁለቱ አገር በቀል ኮንትራክተሮች የሚገነቡዋቸውን የሁለት መንገዶች ፕሮጀክት ኮንትራት ስምምነት ባለፈው ዓርብ ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ጋር ተፈራርመዋል፡፡ በኦሮሚያና በደቡብ ክልሎች የሚገኙትን ሁለት የመንገድ ፕሮጀክቶች ሥራዎችን የተረከቡት ደግሞ ማክሮ ጀኔራል ኮንትራክተር ትሬዲንግና ሰንሻይን ኮንስትራክሽን ናቸው፡፡ ሁለቱም ኮንትራክተሮች በመንገድ ሥራ ዘርፍ ላይ ከዚህ ቀደም የተለያዩ የመንገድ ፕሮጀክቶች ላይ የተሰማሩ ሲሆን፣ በእጃቸው ያለውን ሥራ በአግባቡ ገንብተው በማጠናቀቃቸው ተጨማሪ ሥራ ሊሰጣቸው መቻሉ ተጠቅሷል፡፡ በስምምነቱ ወቅት እንደተገለጸው ማክሮ ኮንስትራክሽን እንዲገነባ የተሰጠው የመንገድ ፕሮጀክት በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞንና የባሌ ዞንን የሚያገናኘውን የአዳባ አንገቱ መቶ ኪሎ ሜትር መንገድ ነው፡፡ ማክሮ ኮንስትራክሽን ይህን መንገድ ለመሥራት የተዋዋለው 1.25 ቢሊዮን ብር ሲሆን፣ ግንባታውም በሦስት ዓመታት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ሁለተኛውን የመንገድ ፕሮጀክት ኮንትራት የተፈራረመው ደግሞ ሰንሻይን ኮንስትራክሽን ነው፡፡ ሰንሻይን ኮንስትራክሽን የተሰጠው የመንገድ ፕሮጀክት በደቡብ ክልል የሞሮቾ፣ ዲምቱና ቢታና የ60.8 ኪሎ ሜትር መንገድ ነው፡፡ ይህንን መንገድ ለመገንባት ሰንሻይን ኮንስትራክሽን የተዋዋለበት ዋጋ 995.01 ሚሊዮን ብር ሲሆን፣ በኮንትራት ውሉ መሠረት ግንባታው በሁለት ዓመት ከአምስት ወራት የሚጠናቀቅ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ ሰንሻይንና ማክሮ የሚገነቡዋቸው ሁለቱ መንገዶ

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሥልጠና ሥጋት የሆነው ርዕዮተ ዓለማዊ ጫና

Image
አንዳንድ የታሪክ ሰነዶችና መጻሕፍት የኢትዮጵያን ፖለቲካ ‘ተማሪ-መራሽ’ ፖለቲካ ይሉታል፡፡ የተደራጀ የፖለቲካ እንቅስቃሴ የፈለቀው በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሲሆን፣ የአፄ ኃይለ ሥላሴና የደርግ መንግሥታትን ከሥልጣን ለማፈናቀል የተማሪዎች ሚና ቁልፍ ነበር፡፡ የወቅቱ የኢሕአዴግ መሪዎች የፖለቲካና የትጥቅ ትግል ለማድረግ የወሰኑት፣ ህልምና ራዕያቸውን የነደፉት በዛሬው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (ያኔ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ተብሎ ይጠራ በነበረው) ነበር፡፡ እነዚህ የኢሕአዴግ መሪዎች ካሳኳቸው ድሎች አንዱ የሆነው የየካቲት 1966 አብዮት 40ኛ ዓመት ከተዘከረ ከጥቂት ወራት በኋላ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ በመላው አገሪቱ የሚገኙ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና መምህራን የመንግሥትን ፖሊሲ፣ ስትራቴጂና ፕሮግራም ለማስተዋወቅ ባለመ ሥልጠና ላይ እየተካፈሉ ይገኛሉ፡፡ ከ40 ዓመት በፊት የተለያዩ አመለካከቶችን ለመጨፍለቅ ሞክሯል ባሉት መንግሥት ላይ ያመፁት ወጣቶች ያመጡት አብዮት በደርግ ተዘርፏል በማለት የትጥቅ ትግል አድርገው ሁለተኛ ለውጥ ቢጎናፀፉም፣ ይህ ሥልጠና በቀድሞዎቹ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በአሁኑ የኢሕአዴግ ከፍተኛ አመራሮች የበላይነት ሲካሄድ ከገዥው ፓርቲ አመለካከት ውጪ ያሉ አማራጭ ሐሳቦችን ይጨፈልቃሉ መባሉ የታሪክ ምፀት ሆኗል፡፡ በመልካም አስተዳደር፣ በዲሞክራሲ ግንባታና በልማት ሥራዎች ላይ ያተኩራል በተባለው ሥልጠና፣ የሥልጠናው አስገዳጅነትና በይዘቱ ርዕዮተ ዓለማዊ አዝማሚያ ላይ ጥያቄዎች ተነስተዋል፡፡ በሥልጠናው ጊዜ፣ ወጪና በኢሕአዴግና በትምህርት ሚኒስቴር ሚናዎች ላይም አስተያየቶች ተሰንዝረዋል፡፡ በገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግና በመንግሥት መካከል ስላለው ልዩነት፣ በመንግሥትና በዩኒቨርሲቲዎች መካከል ስላለው ግንኙነትና የዩኒቨርሲቲዎችን

አንድነት ፓርቲ አቅዶት የነበረው ሠልፍ ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (በአንድነት) መስከረም 25 ቀን 2007 ዓ.ም. ሊያደርገው አቅዶት የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን፣ የፓርቲው ፕሬዚዳንት አቶ ግዛቸው ሽፈራው (ኢንጂነር) ለሪፖርተር አስታወቁ፡፡ ፕሬዚዳንቱ ሠልፉን ለሌላ ጊዜ ማስተላለፍ ያስፈለገበትን ዋነኛ ምክንያት ሲያስረዱ፣ ‹‹እኛ ብቻችንን ከምናደርገው ሠልፉ የሕግ የበላይነትና የህሊና እስረኞችን የሚመለከት በመሆኑ፣ ሌሎች የሚመለከታቸው ፓርቲዎችም አብረን እናደርገዋለን ስላሉ በጋራ እየሠራን በመሆኑ ነው፤›› በማለት አስረድተዋል፡፡ ከዚህ ቀደም ለማድረግ አቅደውት የነበረውን ስብሰባ በተመለከተ፣ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላማዊ ሠልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ቢሮ አስገብተውት የነበረውን ደብዳቤ ከምን እንደደረሰ ከሪፖርተር ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ ‹‹ጥያቄው ምንም መልስ አላገኘም፡፡ እኛም ጉዳዩን አልተከታተልነውም፤›› ብለዋል፡፡ ለዚህም እንደ ምክንያት ያቀረቡት የአቅጣጫ ለውጥ ማድረጋቸውን ሲሆን፣ በዚህም የተነሳ ጉዳዩን በቅርበት አለመከታተላቸውን ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡ ፓርቲው መስከረም 25 ቀን 2007 ዓ.ም. ሊያደርገው አቅዶት የነበረው ሠልፍ ‹‹የአንድነት ንቅናቄ ለሕግ የበላይነትና የህሊና እስረኞችን ለማሰብ›› የሚል መሪ ቃል የነበረው ሲሆን፣ ከዚህም ጋር በተያያዘ የፕሬስ መታፈን፣ የጋዜጠኞችን ስደትና ተያያዥ ጉዳዮችንም እንደሚያነሳ ተገልጾ ነበር፡፡ እንደ ፕሬዚዳንቱ ገለጻ አሁን ግን፣ ፓርቲው የአቅጣጫ ለውጥ በማድረጉ ሠልፉ መቼ እንደሚካሄድ አልተወሰነም፡፡ ‹‹የሠልፉን ቀን አሁን መገመት ያስቸግራል፤›› ብለው፣ በዚሁ ሠልፍ ላይ ከአንድነት ፓርቲ ጋር ምን ያህል ሌሎች ፓርቲዎች እንደሚሳተፉም ገና አለመታወቁን አስረድተዋል፡፡ ‹