Posts

ኢቦላ ወደ ሌሎች 15 የአፍሪካ አገራት ሊሰራጭ ይችላል ተባለ

Image
ኢትዮጵያም ተጠቅሳለች           ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ እስካሁን የኢቦላ ቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተባቸው አገራት በተጨማሪ ሌሎች 15 የአፍሪካ አገራት ከእንስሳት ወደ ሰዎች ለሚተላለፍ የኢቦላ ቫይረስ የመጋለጥ እድል እንዳላቸው ሰሞኑን ባወጣው የጥናት ውጤት ማረጋገጡን ዋሽንግተን ፖስት ዘገበ፡፡ ዩኒቨርሲቲው ለበሽታው የመጋለጥ እድል አላቸው ብሎ የጠቀሳቸው የአፍሪካ አገራት:- ናይጀሪያ፣ ካሜሩን፣ መካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ ጋና፣ ላይቤሪያ፣ ሴራሊዮን፣ አንጎላ፣ ቶጎ፣ ታንዛኒያ፣ ኢትዮጵያ፣ ሞዛምቢክ፣ ብሩንዲ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ማዳጋስካር እና ማላዊ ናቸው፡፡ በሽታው መኖሩ ከታወቀበት ጊዜ አንስቶ በአፍሪካ ውስጥ በሚገኙ አገራት 51 የተለያዩ አካባቢዎች በኢቦላ ቫይረስ የተጠቁ እንስሳት መገኘታቸውን ያስታወሰው ዘገባው፤ ከእንስሳቱ መካከልም ዝንጀሮዎችና ፍራፍሬ ተመጋቢ የሌሊት ወፎች እንደሚገኙበትና እነዚህ እንስሳት ቫይረሱን ወደ አገራቱ ያስፋፉታል ተብሎ እንደሚገመት አስታውቋል፡፡ በተያያዘ ዜና የአፍሪካ ህብረት ባለፈው ሰኞ በአዲስ አበባ በጠራው አስቸኳይ ስብሰባ፣ በአህጉሪቱ ምዕራባዊ ክፍል የተከሰተውን የኢቦላ በሽታ ለመግታትና ወደሌሎች አገራት እንዳይዛመት ለማድረግ፣ የተቀናጀ አህጉራዊ ስትራቴጂ ነድፎ መንቀሳቀስ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክሯል፡፡በሽታው በተከሰተባቸው የምዕራብ አፍሪካ አገራት እየደረሰ ካለው ከፍተኛ ሰብዓዊና ማህበራዊ ጥፋት በተጨማሪ በአገራቱ ኢኮኖሚ ላይ የከፋ ጉዳት ማድረሱ በስብሰባው ላይ የተገለጸ ሲሆን የአፍሪካ የኢኮኖሚ ኮሚሽንም በበሽታው ሳቢያ በጊኒ፣ ላይቤሪያና ሴራሊዮን የአገር ውስጥ ጠቅላላ ምርት ላይ ከፍተኛ መቀነስ ሊፈጠር እንደሚችል ግምቱን ሰንዝሯል፡፡ ምንጭ፦ ኣዲስ ኣድማስ

Sidama “Chire”

Image
Not too long ago “Sidamo” (or more properly “Sidama”) coffee was often a less respected, more generic cousin to Yirgacheffe, the most fabled ethiopian coffee of all. The push for full, micro-lot traceability in Ethiopia over recent years has changed the landscape for specialty coffee as this spectacular offering demonstrates. Notes of Hyacinth, Honey, white grape are layered in with exotic spice in a coffee with a hefty, silky mouthfeel. Clean, dense and delicious, Sidama Chire is a standout even compared to the wide range of excellent coffee emanating from Ethiopia over the last two seasons. Highly recommended. Purchase  here.

Ethiopia wants PVH to invest either in Hawassa or Dire Dawa

Image
PVH Group lays down pre-investment conditions for Ethiopia September 11, 2014 (Ethiopia) Phillips-Van Heusen (PVH) Corporation, one of the leading American garment companies, has put forth ten conditions to the Government of Ethiopia, before investing in the garment sector in Ethiopia, Addis Fortune reported. Officials of the company had visited Ethiopia, along with 27 textile and garment factories from different countries, last month. The conditions that were laid down by PVH include consideration of tax incentives, logistics issues, and priorities for power supply, and getting a ready-made industrial park. These prerequisites were discussed in a meeting between the representatives of PVH and the Government of Ethiopia officials, State Ministers for Industry, Sisay Gemechu and Tadesse Hiale, Deputy Commissioner of the Federal Investment Commission (FIC) Likyeleshe Abay and representatives from the Textile Industries Development Institute (TIDI). Ethiopia wants PVH to invest e

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን የማዘጋጀት አቅም እንዳላት ተገለጸ

Image
አዲስ አበባ መስከረም 2/2007 ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን የማዘጋጀት አቅሙ እንዳላትና የትኛውንም አይነት መሰል ኃላፊነት ቢሰጣት ለመወጣት ዝግጁ መሆኗን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተናገሩ። የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌደሬሽን /ካፍ/ ፕሬዝዳንት ኢሳ ሃያቱ በበኩላቸው አስፈላጊን ቅደመ ሁኔታ ካሟላች ካፍ የአፍሪካ ዋንጫን የማዘጋጀት ኃላፊነት ለኢትዮጵያ ለመስጠት ፈቃደኛ መሆኑን ገልጸዋል። በካፍ ፕሬዝዳንት ሚስተር ኢሳ ሃያቱ የተመራ የልኡካን ቡድን ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝና ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ተወያይቷል። በኢትዮጵያ እያደገ የመጣውን የስፖርት ኢንዱስትሪ ለማገዝና ለማጠናከር ከኮንፌደሬሽኑ ጋር ያለውን ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይም ተነጋግረዋል። ከውይይቱ በኋላ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን ለማዘጋጀት እንቅስቃሴዎች ጀምራለች። ኢትዮጵያ በእግር ኳስ ስፖርት ትልቅ ታሪክ ያላት አገር ብትሆንም ይህ ለረጅም ጊዜ ተቀዛቅዞ ቆይቷል ያሉት አቶ ደመቀ አሁን እየታየ ያለው መነቃቃት የሚያበረታታ ነው ብለዋል። ኮንፌደሬሽኑ ይህንን ተነሳሽነትና መነቃቃት በሚደገፍባቸው ሁኔታዎች እንዲሁም አገሪቱ በተለያዩ መድረኮች ያላትን ውክልና በማስፋት ዙሪያም ተወያይተዋል። አቶ ደመቀ እንደገለጹት "በውይይቱ ኮንፌደሬሽኑ በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች ያለውን የስልጠና ማእከልና ብሄራዊ የእግር ኳስ ቡድኑን ለማጠናከር ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጿል"። የካፍ ፕሬዝዳንት ሚስተር ኢሳ ሃያቱ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን የማዘጋጀት ፍላጎት እስካላትና ቅድመ ሁኔታዎችን እስካሟላች ድረስ ካፍ ሃላፊነቱን ቢሰጣት ደስተኛ እንደሆኑ ነው የተናገሩት።

አዲሱን ዓመት በአዲስ መንፈስ እንቀበለው

Image
በአዲስ ዓመት አዲስ መንፈስ ያስፈልጋል፡፡ እንኳን ከዘመን ወደ ዘመን አሸጋገራችሁ ሲባል የመልካም ምኞት መግለጫው ራሱ የመታደስ ስሜት ይፈጥራል፡፡ አሮጌው ዘመን አልፎ አዲሱ ሲተካ ሁሉም ነገራችን አዲስ የመሆንና የመታደስ ስሜት ይፈልጋል፡፡ አዲሱን ዓመት በአዲስ መንፈስ እንቀበለው ስንል በዓሉ ከሚፈጥረው ድባብ በላይ ዘለቄታዊው ብሔራዊ ጉዳይ ይቅደም ማለታችን ነው፡፡ ሁሌም አዲስ ዓመት አዲስ መንፈስ ይፈልጋልና፡፡ ስለዚህ አዲሱን ዓመት ስንቀበል የሚከተሉትን አምስት ዋና ዋና ነጥቦች ልብ ልንላቸው ይገባል፡፡ 1.የመልካም አስተዳደር ጉዳይ ይታሰብበት እንደሚታወቀው የአንድን አገር ኢኮኖሚያዊ ዕድገትም ሆነ ዲሞክራሲያዊ ጉዞ ከሚፈታተኑ ችግሮች መካከል የመልካም አስተዳደር እጦት አንደኛው ነው፡፡ መልካም አስተዳደር በሌለበት ልማት የለም፣ ዕድገት የለም፣ ዲሞክራሲ የለም፣ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ አይታሰብም፡፡ የመልካም አስተዳደር እጦት ዜጎችን ለመከራና ለስቃይ ከመዳረጉም በላይ የሕግ የበላይነትን ይጋፋል፡፡ በአዲሱ ዓመት የሕዝባችንን ችግሮች ከሚያባብሱት መካከል በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሰው የመልካም አስተዳደር እጦት ይወገድ ዘንድ መንግሥት በከፍተኛ የኃላፊነት መንፈስ መሥራት ይኖርበታል፡፡ የመልካም አስተዳደር ዕጦት የሰላም፣ የልማትና የዲሞክራሲ ፀር በመሆኑ በአዲሱ ዓመት ከፍተኛ ትኩረት ማግኘት አለበት፡፡ ሕዝብ በፍትሕ እጦት፣ በአገልግሎት መስተጓጎልና ጨርሶውኑ አለመገኘት፣ በሕገወጥ ተግባራትና በመሳሰሉት ችግሮች ሲሰቃይ ችላ መባል የለበትም፡፡ የሕግ የበላይነትን የሚጋፉና ዜጎችን ለእንግልት የሚዳርጉ አስከፊ ተግባራት መቆም ይኖርባቸዋል፡፡ ግብር ከፋዩ ሕዝብ የአገልጋይነት መንፈስ ባለው ቢሮክራሲ መስተናገድ አለበት፡፡ የሕዝብን ችግር ከመጤፍ ሳይ