Posts

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን የማዘጋጀት አቅም እንዳላት ተገለጸ

Image
አዲስ አበባ መስከረም 2/2007 ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን የማዘጋጀት አቅሙ እንዳላትና የትኛውንም አይነት መሰል ኃላፊነት ቢሰጣት ለመወጣት ዝግጁ መሆኗን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተናገሩ። የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌደሬሽን /ካፍ/ ፕሬዝዳንት ኢሳ ሃያቱ በበኩላቸው አስፈላጊን ቅደመ ሁኔታ ካሟላች ካፍ የአፍሪካ ዋንጫን የማዘጋጀት ኃላፊነት ለኢትዮጵያ ለመስጠት ፈቃደኛ መሆኑን ገልጸዋል። በካፍ ፕሬዝዳንት ሚስተር ኢሳ ሃያቱ የተመራ የልኡካን ቡድን ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝና ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ተወያይቷል። በኢትዮጵያ እያደገ የመጣውን የስፖርት ኢንዱስትሪ ለማገዝና ለማጠናከር ከኮንፌደሬሽኑ ጋር ያለውን ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይም ተነጋግረዋል። ከውይይቱ በኋላ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን ለማዘጋጀት እንቅስቃሴዎች ጀምራለች። ኢትዮጵያ በእግር ኳስ ስፖርት ትልቅ ታሪክ ያላት አገር ብትሆንም ይህ ለረጅም ጊዜ ተቀዛቅዞ ቆይቷል ያሉት አቶ ደመቀ አሁን እየታየ ያለው መነቃቃት የሚያበረታታ ነው ብለዋል። ኮንፌደሬሽኑ ይህንን ተነሳሽነትና መነቃቃት በሚደገፍባቸው ሁኔታዎች እንዲሁም አገሪቱ በተለያዩ መድረኮች ያላትን ውክልና በማስፋት ዙሪያም ተወያይተዋል። አቶ ደመቀ እንደገለጹት "በውይይቱ ኮንፌደሬሽኑ በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች ያለውን የስልጠና ማእከልና ብሄራዊ የእግር ኳስ ቡድኑን ለማጠናከር ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጿል"። የካፍ ፕሬዝዳንት ሚስተር ኢሳ ሃያቱ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን የማዘጋጀት ፍላጎት እስካላትና ቅድመ ሁኔታዎችን እስካሟላች ድረስ ካፍ ሃላፊነቱን ቢሰጣት ደስተኛ እንደሆኑ ነው የተናገሩት።

አዲሱን ዓመት በአዲስ መንፈስ እንቀበለው

Image
በአዲስ ዓመት አዲስ መንፈስ ያስፈልጋል፡፡ እንኳን ከዘመን ወደ ዘመን አሸጋገራችሁ ሲባል የመልካም ምኞት መግለጫው ራሱ የመታደስ ስሜት ይፈጥራል፡፡ አሮጌው ዘመን አልፎ አዲሱ ሲተካ ሁሉም ነገራችን አዲስ የመሆንና የመታደስ ስሜት ይፈልጋል፡፡ አዲሱን ዓመት በአዲስ መንፈስ እንቀበለው ስንል በዓሉ ከሚፈጥረው ድባብ በላይ ዘለቄታዊው ብሔራዊ ጉዳይ ይቅደም ማለታችን ነው፡፡ ሁሌም አዲስ ዓመት አዲስ መንፈስ ይፈልጋልና፡፡ ስለዚህ አዲሱን ዓመት ስንቀበል የሚከተሉትን አምስት ዋና ዋና ነጥቦች ልብ ልንላቸው ይገባል፡፡ 1.የመልካም አስተዳደር ጉዳይ ይታሰብበት እንደሚታወቀው የአንድን አገር ኢኮኖሚያዊ ዕድገትም ሆነ ዲሞክራሲያዊ ጉዞ ከሚፈታተኑ ችግሮች መካከል የመልካም አስተዳደር እጦት አንደኛው ነው፡፡ መልካም አስተዳደር በሌለበት ልማት የለም፣ ዕድገት የለም፣ ዲሞክራሲ የለም፣ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ አይታሰብም፡፡ የመልካም አስተዳደር እጦት ዜጎችን ለመከራና ለስቃይ ከመዳረጉም በላይ የሕግ የበላይነትን ይጋፋል፡፡ በአዲሱ ዓመት የሕዝባችንን ችግሮች ከሚያባብሱት መካከል በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሰው የመልካም አስተዳደር እጦት ይወገድ ዘንድ መንግሥት በከፍተኛ የኃላፊነት መንፈስ መሥራት ይኖርበታል፡፡ የመልካም አስተዳደር ዕጦት የሰላም፣ የልማትና የዲሞክራሲ ፀር በመሆኑ በአዲሱ ዓመት ከፍተኛ ትኩረት ማግኘት አለበት፡፡ ሕዝብ በፍትሕ እጦት፣ በአገልግሎት መስተጓጎልና ጨርሶውኑ አለመገኘት፣ በሕገወጥ ተግባራትና በመሳሰሉት ችግሮች ሲሰቃይ ችላ መባል የለበትም፡፡ የሕግ የበላይነትን የሚጋፉና ዜጎችን ለእንግልት የሚዳርጉ አስከፊ ተግባራት መቆም ይኖርባቸዋል፡፡ ግብር ከፋዩ ሕዝብ የአገልጋይነት መንፈስ ባለው ቢሮክራሲ መስተናገድ አለበት፡፡ የሕዝብን ችግር ከመጤፍ ሳይ

የወንዶ ገነት ግብርና ምርምር ማእከል: ለምግብ መድሀኒትና ነዳጅ ዘይት በሚያገለግሉ እጽዋቶች ላይ ምርምር እያካሄደ ነው

ሻሸመኔ ጳጉሜ 5/2006 ኢትዮጵያ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ የምታስገባውን መድሃኒት፣ምግብ ማቀነባበሪያ፣የኮስሞቲክስና ነዳጅ ዘይት ወጪ በሂደት ለማስቀረት ምርምር እያካሄደ መሆኑን የወንዶ ገነት ግብርና ምርምር ማእከል አስታወቀ። በማእከሉ የመአዛማ፣መድሃኒትና ነዳጅ ዘይት እጽዋቶች አስተባባሪና ተመራማሪ አቶ በእምነት መንገሻ ሰሞኑን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ባለፉት አምስት ዓመታት ማእከሉ ምርምር ካካሄደባቸው 30 እጽዋቶች መካከል 20ዎቹ ለምግብ፣ለመጠጥ ማቀነባበሪያ፣ ለስኳር ፣ ለመድሃኒትና ነዳጅ ዘይት የሚያገለግሉ መሆናቸው በሙከራ ተረጋግጧል። ከውጪና ከሐገር ውስጥ አሰባስቦ ምርምር ያካሄደባቸውን እጽዋቶች በልማቱ ለሚሳተፉ አርሶ አደሮችና ባለሃብቶች ማሰራጨቱን ገልጸዋል። ማእከሉ ከንግድ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ባካሄደው የገበያ ጥናት መሰረት ሐገሪቱ ከውጭ ለምታስገባቸው የምግብ ማቀነባበሪያ፣መድሀኒትና ነዳጅ ዘይት ውጤቶች በየአመቱ ከሁለት ነጥብ አምስት ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር እንደምታወጣ መረጋገጡን አስታውቀዋል። ከጃትሮፋ ተክል ነዳጅ፣ከመአዛማ እጸዋቶች ኮስሞቲክስ፣የጸጉርና ገላ የውበትና ጤንነት መጠበቂያ፣ለመድሀኒት ቅመማ  የሚያገለግሉ እጽዋቶች በምርምር ማግኘቱን ገልጸዋል። ማእከሉ ሐገሪቱ የምታወጣውን የውጭ ምንዛሪ ለማስቀረትና ምርቱን በማስተዋወቅ ለአለም አቀፍ ገበያ ለማቅረብ ለጀመረው ኢንዱስትሪ መር ስትራቴጂ እቅድ ነድፎ እየሰራ መሆኑንም አስታውቀዋል። የሚያፈልቃቸውን የምርምር ውጤቶች ለአርሶ አደሩና ባለሃብቱ በማስተዋወቅና በማሰራጨት ተጠቃሚው ህብረተሰብ ዘንድ እንዲደረስ ትኩረት መሰጠቱን ገልጸዋል። በሰው ሰራሽና በተለያየየ ምክንያት የተራቆተውን መሬት በማእዛማ እጽዋቶች ሸፍኖ የአፈር ለምነት

Hawassa University (HU) and Wondo Genet Collage of Forestry & Natural Resources are to Receive Equipments

Image
Ethiopian Universities is to receive donation of equipments worth two million Birr, including laboratory equipment, machines, printers and projectors. Horn of Africa Regional Environment Center & Network (HoA-RECN), which leads the Ethiopian consortium of sustainable tourism based on natural resource management with balance towards women (STRONGBOW) project, and the Center for International Cooperation at University of Amsterdam (CIS-VU) will hand over these equipment to selected higher learning institutions in Ethiopia on September 9, 2014 at HoA-RECN headquarters inside Gullele Botanic Garden, Addis Abeba. The Handover ceremony will take place in the presence of Araya Asfaw (PhD), executive director of HoA-RECN, Denyse Snelder (PhD), STRONGBOW Project director, Henk van den Heuvel, senior advisor for higher education management & Organization for CIS-VU, Rawda Seman, STRONGBOW project coordinator for HoA-RECN and representatives of different higher learning institu

ኣዲሱን ኣመት ምክንያት በማድረግ የደቡብ ክልል ብሎም የሲዳማ ዞን መንግስት ለሕግ ታራሚዎች ይቅርታ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፤ ኢትዮጵያ በእስረኞች ቁጥር በኣፍሪካ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች

Image
ሰሞኑን ከኣገሪቱ መገናኛ ብዙሃን የተለያዩ ወንጀሎችን በመፈጸማቸው የእስራት ቅጣት ውሳኔ ተላልፎባቸው ሁለት ሦስተኛውን የቅጣት ጊዜያቸውን በእስራት ያሳለፉና በማረሚያ ቤት ቆይታቸው መልካም ሥነ ምግባር የነበራቸው፣ ከ 900 በላይ ታራሚዎች ኣዲሱን ኣመት ምክንያት በማድረግ በይቅርታ እንደሚፈቱ ገልጸዋል፡፡ Photo from http://mereja.com/forum/viewtopic.php?t=70171&p=427589 እንደሪፖርተር ጋዜጣ ዘገባ ከሆነ ታራሚዎቹ ስለይቅርታ አጠያየቅ በይቅርታ ቦርድ ጽሕፈት ቤት በተዘጋጀው ቅጽ መሠረት ሞልተው የሚያቀርቡትን የይቅርታ ጥያቄ፣ ቦርዱ ተቀብሎና ከማረሚያ ቤቶቹ አጣርቶ ለፍትሕ ሚኒስቴር ካቀረበ በኋላ፣ ሚኒስቴሩ ለአገሪቱ ፕሬዚዳንት በማቅረብ ፕሬዚዳንቱ ይቅርታ እንደሚያደርጉ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ፕሬዚዳንት ዶ / ር ሙላቱ ተሾመ በይቅርታ ቦርድ ጽሕፈት ቤት በኩል ተጣርቶ የቀረቡላቸውን ከ 900 በላይ ታራሚዎች፣ ከእስር እንዲለቀቁ ጳጉሜን 5 ቀን 2006 ዓ . ም . ይፋ እንደሚያደርጉ ተገልጿል፡፡ እነዚሁ ታራሚዎች በኣዲሱ ኣመት ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንድቀላቀሉ ለማድረግ መታሰቡ ይበል የሚያሰኘ ኣካሄድ ቢሆንም በኣገሪቱ ውስጥ በእስር ላይ ከምገኙ በርካታ ቁጥር ካላቸው ታራሚዎች ኣንጻር በይቅርታ የምፈቱት ታራሚዎች ቁጥር በጣም ኣነስተኛ ነው። ከተለያዩ ምንጮች የተገኙ መረጃዎች እንደምያሳዩት በኢትዮጵያ ሶስት ፌደራል ፤ ከ 117 በላይ የክልል እና በርካታ ቁጥር ያላቸው ያልታወቁ እስር ቤቶች እንዳሉ የተገለጸ ሲሆን፤ ኣለምኣቀፍ የእስረኞች ጥናት ማዕከል ( InternationalCentre for Prison Studies – ICPS) ከኣንድ ኣመት በፊት ባሳተመው World Prison Populatio