ኣዲሱን ኣመት ምክንያት በማድረግ የደቡብ ክልል ብሎም የሲዳማ ዞን መንግስት ለሕግ ታራሚዎች ይቅርታ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፤ ኢትዮጵያ በእስረኞች ቁጥር በኣፍሪካ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች
ሰሞኑን ከኣገሪቱ መገናኛ ብዙሃን የተለያዩ ወንጀሎችን በመፈጸማቸው የእስራት ቅጣት ውሳኔ ተላልፎባቸው ሁለት ሦስተኛውን የቅጣት ጊዜያቸውን በእስራት ያሳለፉና በማረሚያ ቤት ቆይታቸው መልካም ሥነ ምግባር የነበራቸው፣ ከ 900 በላይ ታራሚዎች ኣዲሱን ኣመት ምክንያት በማድረግ በይቅርታ እንደሚፈቱ ገልጸዋል፡፡ Photo from http://mereja.com/forum/viewtopic.php?t=70171&p=427589 እንደሪፖርተር ጋዜጣ ዘገባ ከሆነ ታራሚዎቹ ስለይቅርታ አጠያየቅ በይቅርታ ቦርድ ጽሕፈት ቤት በተዘጋጀው ቅጽ መሠረት ሞልተው የሚያቀርቡትን የይቅርታ ጥያቄ፣ ቦርዱ ተቀብሎና ከማረሚያ ቤቶቹ አጣርቶ ለፍትሕ ሚኒስቴር ካቀረበ በኋላ፣ ሚኒስቴሩ ለአገሪቱ ፕሬዚዳንት በማቅረብ ፕሬዚዳንቱ ይቅርታ እንደሚያደርጉ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ፕሬዚዳንት ዶ / ር ሙላቱ ተሾመ በይቅርታ ቦርድ ጽሕፈት ቤት በኩል ተጣርቶ የቀረቡላቸውን ከ 900 በላይ ታራሚዎች፣ ከእስር እንዲለቀቁ ጳጉሜን 5 ቀን 2006 ዓ . ም . ይፋ እንደሚያደርጉ ተገልጿል፡፡ እነዚሁ ታራሚዎች በኣዲሱ ኣመት ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንድቀላቀሉ ለማድረግ መታሰቡ ይበል የሚያሰኘ ኣካሄድ ቢሆንም በኣገሪቱ ውስጥ በእስር ላይ ከምገኙ በርካታ ቁጥር ካላቸው ታራሚዎች ኣንጻር በይቅርታ የምፈቱት ታራሚዎች ቁጥር በጣም ኣነስተኛ ነው። ከተለያዩ ምንጮች የተገኙ መረጃዎች እንደምያሳዩት በኢትዮጵያ ሶስት ፌደራል ፤ ከ 117 በላይ የክልል እና በርካታ ቁጥር ያላቸው ያልታወቁ እስር ቤቶች እንዳሉ የተገለጸ ሲሆን፤ ኣለምኣቀፍ የእስረኞች ጥናት ማዕከል ( InternationalCentre for Prison Studies – ICPS) ከኣንድ ኣመት በፊት ባሳተመው World Prison Populatio