ወራዊው ኣጠቃላይ ኣገራዊ የዋጋ ግሽበት በኣማካይ ጥማሪ ኣሳይቷል ተባለ
ሰሞኑን ማዕከላዊ ስታቲሰቲክስ ኤጀንሲ የወጣው መረጃ እንደምያሳየው፤ የነሐሴ ወር አጠቃላይ አገራዊ የዋጋ ግሽበት በአማካይ 7 ነጥብ 2 በመቶ ደርሷል ። እንደኤጄንሲው ከሆነ፤ የሐምሌ ወር የዋጋ ግሽበት 6 ነጥብ 9 በመቶ የ ነበ ረ ሲሆን የነሐሴ ወር 2006 ዓ . ም አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ከሐምሌ ወር ጋር ሲነፃፀር የ 0 ነጥብ 3 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። የዋጋ ግሽበቱ ልጨምሪ የቻለው በዋናነት ምግብ ነክ ባል ሆኑ ሸቀጦች ላይ በታየው ጭማሪ ነው ተብሏል ። እንደ ሬድዮ ፋና ዘጋባ ከሆነ፤ በሐምሌ ወር 5 ነጥብ 7 በመቶ የነበረው የምግብ ነክ ሸቀጦች ዋጋ የመጨመር አዝማሚያ በተጠናቀቀው የነሐሴ ወር ወደ 5 ነጥብ 2 በመቶ ዝቅ ብሏል። በአንጻሩ ምግብ ነክ ያልሆኑ ሸቀጦች ዋጋ የመጨመር አዝማሚያ በሐምሌ ወር ከነበረው 8 ነጥብ 2 በመቶ በነሐሴ ወር ወደ 9 ነጥብ 4 በመቶ ከፍ ብሏል። በዚህም መሰረት የነሐሴ ወር 2006 ዓ . ም አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት በአማካይ 7 ነጥብ 2 በመቶ ሆኖ ተመዝግቧል። አገራዊ የዋጋ ግሽበት ላስፐርስ በተባለ ዓለም አቀፍ ቀመር የሚለካ ሲሆን፥ ሲዳማን ጨምሮ በመላ አገሪቱ ባሉ 25 የኤጀንሲው ቅርንጫፎች አማካይነት ከ 119 የገበያ ቦታዎች የዕቃዎችን ዋጋ በማሰባሰብና ወደ ዋናው ቅርንጫፍ በማምጣት በባለሙያዎች ተተንትኖ በየወሩ ይፋ እንደምያደርግ ከሮይተርስ እና ፋና ብሮ ድ ካስት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።