Posts

ኣንድባል የምጋሩ የሲዳማ ሴቶች የመሬት ባለቤትነት ወይም የመጠቀም መብት እስከምን ደረጃ ነው?

Image
በሲዳማ የሴቶች የመሬት ባለቤትነት በተለይ ኣንድ ባል የሚጋሩ ምስቶች ( ባለቤቶቻቸው ከኣንድ በላይ ምስቶች ያሏቸው ከሆነ ) የመሬት ባለቤትነት ወይም የመጠቀም መብት እስከምን ደረጃ ነው ? Impacts of Polygamous Marriage on Women's Land Rights in Ethiopia: Its Impacts on Women's Rural Land Rights in Sidama Zone,Southern Nations, Nationalities and Peoples Regional State በምል ርዕስ በቴሬዛ ጴጥሮስ የተዘጋጀው መጽሐፍ በዚህ ጉዳይ ላይ የተሰራውን ጥናት ይዞ ቀርቧል። መጽሐፉ ከኣንድ በላይ ጋብቻ በሴቶች የመሬት ባለቤትነት እና ተጠቃሚነት ላይ ያለውን ተጽዕኖ ከሲዳማ ሴቶች ኣንጻር የምተነትን ሲሆን ያለውን ኣሉታዊ ገጽታን ያብራራል። መጽሐፉ ሴቶችን በኢኮኖሚ ብሎም በሌሎች ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ መስኮች ራሳቸውን ለማስቻል በመንግስት እና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ለምደረገው ስራ ኣጋዥ የሆነ መረጃ ይዟል። በኣጠቃላይ ከኣንድ በላይ ጋብቻ በሲዳማ ሴቶች ላይ ያለውን ኣሉታዊ ገጽታ በኣግባቡ ለመረዳት መጽሐፉ ጠቃሚ መረጃ ይስጣል። ለተጨማሪ መረጃ ከታች ይጫኑ፦  http://www.amazon.com/Impacts-Polygamous-Marriage-Womens-Ethiopia/dp/3659197424/ref=sr_1_4/186-0184352-4930450?s=books&ie=UTF8&qid=1409839362&sr=1-4&keywords=Sidama

Giant American Clothing Company to take its investment to Hawassa or Dire Dawa

Image
The government wants this company to take its investment to Dire Dawa or  Hawassa , but the company has its eyes on the Bole Lemi Industrial ... The company, Phillips-Van Heusen (PVH) Corporation, generated a revenue of 8.2 billion dollars in 2013 PVH has 700 outlets all over the world which sell Tommy Hilfiger, Calvin Klein and Heritage brands it sourced from factories in Bangladesh, Sri Lanka, China, Honduras, Hong Kong, Indonesia, Philippines, Malaysia, Mongolia, Singapore, Thailand and Taiwan. Phillips-Van Heusen (PVH) Corporation – a giant American clothing company and owner of the Tommy Hilfiger, Calvin Klein and Heritage brands – has set 10 investment preconditions to the Government of Ethiopia (GoE). Officials of the company made a visit to Ethiopia, along with 27 textile and garment factories from different countries, last week, for the third time in two months. The second round visit was made by 40 companies led by Mark Green, vice president of the com

በርካታ የሲዳማ ባላሃብቶችን በሽርክና የያዘው ደቡብ ግሎባል ባንክ ኣዲስ ፕሬዚዳንት ልሾምለት ነው

Image
የአቢሲኒያ ባንክ ፕሬዚዳንት ቀጣይ ማረፊያ ደቡብ ግሎባል ባንክ እንደሆነ ተጠቆመ - ባንኩ ገንዘብና ወርቅ ሸልሞ ሸኛቸው    -    የደቡብ ግሎባል ባንክ ፕሬዚዳንት ከኃላፊነታቸው ለቀቁ በዳዊት ታዬ  ከአቢሲኒያ ባንክ ፕሬዚዳንትነታቸው በፈቃዳቸው መልቀቃቸውን ያሳወቁት አቶ አዲሱ ሃባ፣ ቀጣይ ማረፊያቸው ደቡብ ግሎባል ባንክ እንደሆነ ተጠቆመ፡፡ የደቡብ ግሎባል ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ ወርቁ ለማ ደግሞ ኃላፊነታቸውን ለቀዋል፡ ፡ አቢሲኒያ ባንክ ለአምስት ዓመት የመሩት አቶ አዲሱ፣ በባንኩ ታሪክ የመጀመሪያ ነው በተባለው የሽኝት ፕሮግራም ላይ፣ በባንኩ ቦርድ ውሳኔ መሠረት የግማሽ ሚሊዮን ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡  ከገንዘብ ሽልማቱ በተጨማሪ ለእርሳቸውና ለባለቤታቸው በነፍስ ወከፍ ሃያ ግራም ወርቅ የተበረከተላቸው ሲሆን፣ በቆይታቸው ለባንኩ ያበረከቱት አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደነበር የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር አቶ መሐሪ ዓለማየሁ በሽኝት ፕሮግራሙ ላይ ተናግረዋል፡፡  ቅዳሜ ነሐሴ 24 ቀን 2006 ዓ.ም. በሒልተን ሆቴል በተደረገው የሽኝት ፕሮግራም ላይ አቶ መሐሪ የአቶ አዲሱ መልቀቅ ድንገተኛና ያልተጠበቀ መሆኑን የገለጹት፣ ‹‹አቶ አዲሱ በራሳቸው ምክንያት ባንካችንን ለመልቀቅ ስለጠየቁ ቦርዱም ጥያቄው ድንገተኛ ሆኖ ደስተኛ ባይሆንም ጥያቄውን ተቀብሎታል፤›› በሚል ነው፡፡ አያይዘውም ከአቶ አዲሱ ጋር ወደፊትም መልካም ግንኙነቱ እንደሚቀጥል ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል፡፡ አቶ አዲሱ በአምስት ዓመት ቆይታቸው አበርክተዋል ያሉዋቸውን ዋና ዋና ተግባራት ያስታወሱት የቦርድ ሊቀመንበሩ፣ ‹‹አቶ አዲሱ ለአቢሲኒያ ባንክ የተቻላቸውን ሁሉ አድርገዋል ብዬ አምናለሁ፤›› ብለዋል፡፡ የደቡብ ግሎባል ባንክ ፕሬዚዳንትነታቸውን ያስረከቡት አ

ተቃዋሚ ፓርቲዎች ምን እየሆኑ ነው?

Image
ምርጫ 2007 ዘጠኝ ወራት ያህል እየቀሩት ነው፡፡ ይህ ወቅት ደግሞ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዕጩዎችን የሚያዘጋጁበት፣ የምረጡኝ ቅስቀሳ ለመጀመር የቤት ሥራቸውን የሚያጠናቅቁበትና ምርጫው ምርጫ እንዲመስል የራሳቸውን ድርሻ የሚወጡበት ነው፡፡ አሁን እያየን ያለነው ግን ይህንን ምሥል ሳይሆን ተቃራኒውን ነው፡፡ የምርጫ ሸብ ረብ ሳይሆን በትንሽ በትልቁ እርስ በርስ መናቆር ነው፡፡ በሰላማዊ ትግሉ ውስጥ አለን የሚሉት ስማቸው ጎላ ብሎ የሚታይ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሽኩቻ ውስጥ ናቸው፡፡ ከገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ ጋር ለዓመታት የከረሙበት መናቆር እንዳለ ሆኖ፣ አሁን ደግሞ ወደ ውስጥ ግብግብ ገብተዋል፡፡ የተቃዋሚ ፓርቲዎች መጠናከር ሳይሆን መፍረክረክ እየታየ ነው፡፡ ምርጫ ዋዜማ ላይ ሆኖ ይህንን ትርምስ የሚታዘቡ ደጋፊዎችም ሆኑ አባላት ተስፋ እየቆረጡ ይመስላል፡፡ የፖለቲካ ትግሉንም ሊሸሹ ይችላሉ፡፡ ይህ ደግሞ ለፖለቲካ ፓርቲዎች ህልውና አይበጅም፡፡ ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ በሚደረግ ሰላማዊ ትግል የፖለቲካ ፓርቲዎች ህልውና አስፈላጊ ነው፡፡ የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት የሚያብበው መራጩ ሕዝብ የተለያዩ አማራጮች ያሉዋቸውን ፓርቲዎች ማግኘት ሲችል ነው፡፡ አማራጭ ሲባል ለይስሙላ የሚነገር በጥናት ላይ ያልተመሠረተ ስንክሳር ሳይሆን በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በተለያዩ ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ የተደራጁ ፕሮግራሞችን ይዞ መቅረብ ነው፡፡ አሁን የምናየው ይህንን አይገልጽም፡፡ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ለእንቅስቃሴዎቻቸው መገደብ ሁለት ዓበይት ምክንያቶች አሉ፡፡ አንደኛው ውጪያዊ ሲሆን፣ ሁለተኛው ውስጣዊ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ውጫዊው ምክንያት በገዥው ፓርቲ ተፅዕኖ የሚገለጽ ነው፡፡ ይህ የፖለቲካ ምኅዳሩን ከማጥበብ አንስቶ በርካታ ምክንያቶች የሚቀርቡበት ተፅዕኖ ብዙ የተባለበት በመሆ

Sidaamu Fidalla

Image
የሲዳማን ቋንቋ ለየት ባለ መልኩ ማቅረብን ኣላማ ያደረገው ይህ መጽሐፊ በውስጡ 33 የሲዳሙኣፎ ፊደላቲን የያዘ ሲሆን፤ ከዚሁ ውስጥ 26 ቱ ነጠላ ኣሃዝ ፊደላቲ ሲሆኑ የተቀሩት 7 ቱ ደግሞ ባለ ሁለት ኣሃዝ ፊደላቲ ናቸው። መጽሐፉ 26 ቱ በላቲን ማለትም በእንግሊዥኛ እና በሌሎች ቋንቋዎች የሚገኙትን ፊደላቲ በቀላሉ ለመማር እንድያመች ዘንድ በፊደላቱ የሚጀምሩትን ቃላት በስዕል ኣስደግፎ ኣቅርቧል። በተጨማሪም የፊደላቱን የያዙ ቃላት በሲዳማ እና በኣፍሪካ ኣፌ ታሪኮች በማዋዛት በማይሰለች መልኩ ይተርካል። የተቀሩት ሰባቱ ለሲዳማ ኣፎ እንድመቹ ተደርገው የተቀረጹት፦ ch, dh, ny, ph, sh, ts እና zh የተባሉ ፊደላቲ በተመሳሳይ የመማሩን ህደት በሚያቀላጥፍ መልኩ ቀርበዋል። የመጽሐፉ የመጨረሻ ክፍል ደግሞ የሲዳማን የቀን፤ ሳምንት እና ወራት ኣቆጣጠርን በተመለከተ በማብራሪያ ኣስደግፎ ኣቅርበዋል። በኣጠቃላይ ይህ በካላ ጋልፋቶ ዎናጎ የተዘጋጀው የሲዳማ ፊደላቲ መጽሐፍ ፤ለሲዳማ ቋንቋ ጀማሪ ተማሪዎች ቋንቋውን በቀላሉ መማሪ እንድችሉ ከፍተኛ እገዛ የሚያድርግ ነው። መጽሐፉ በኣሁኑ ጊዜ በኣማዞን ደረ ገጽ ላይ በሽያጭ ላይ ይገኛል። የሲዳማን ቋንቋ ለመማሪ ለምፈልጉ ወዳጆች በሰጦታ መልክ ለማበርከት ኣልያም ለልጆቻችሁ ማስተማሪያነት መጽሐፉን መግዛት የምትሹ ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን መግዛት የምትችሉ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን። ሲዳሙ ፊዳላ