በርካታ የሲዳማ ባላሃብቶችን በሽርክና የያዘው ደቡብ ግሎባል ባንክ ኣዲስ ፕሬዚዳንት ልሾምለት ነው
የአቢሲኒያ ባንክ ፕሬዚዳንት ቀጣይ ማረፊያ ደቡብ ግሎባል ባንክ እንደሆነ ተጠቆመ - ባንኩ ገንዘብና ወርቅ ሸልሞ ሸኛቸው - የደቡብ ግሎባል ባንክ ፕሬዚዳንት ከኃላፊነታቸው ለቀቁ በዳዊት ታዬ ከአቢሲኒያ ባንክ ፕሬዚዳንትነታቸው በፈቃዳቸው መልቀቃቸውን ያሳወቁት አቶ አዲሱ ሃባ፣ ቀጣይ ማረፊያቸው ደቡብ ግሎባል ባንክ እንደሆነ ተጠቆመ፡፡ የደቡብ ግሎባል ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ ወርቁ ለማ ደግሞ ኃላፊነታቸውን ለቀዋል፡ ፡ አቢሲኒያ ባንክ ለአምስት ዓመት የመሩት አቶ አዲሱ፣ በባንኩ ታሪክ የመጀመሪያ ነው በተባለው የሽኝት ፕሮግራም ላይ፣ በባንኩ ቦርድ ውሳኔ መሠረት የግማሽ ሚሊዮን ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡ ከገንዘብ ሽልማቱ በተጨማሪ ለእርሳቸውና ለባለቤታቸው በነፍስ ወከፍ ሃያ ግራም ወርቅ የተበረከተላቸው ሲሆን፣ በቆይታቸው ለባንኩ ያበረከቱት አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደነበር የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር አቶ መሐሪ ዓለማየሁ በሽኝት ፕሮግራሙ ላይ ተናግረዋል፡፡ ቅዳሜ ነሐሴ 24 ቀን 2006 ዓ.ም. በሒልተን ሆቴል በተደረገው የሽኝት ፕሮግራም ላይ አቶ መሐሪ የአቶ አዲሱ መልቀቅ ድንገተኛና ያልተጠበቀ መሆኑን የገለጹት፣ ‹‹አቶ አዲሱ በራሳቸው ምክንያት ባንካችንን ለመልቀቅ ስለጠየቁ ቦርዱም ጥያቄው ድንገተኛ ሆኖ ደስተኛ ባይሆንም ጥያቄውን ተቀብሎታል፤›› በሚል ነው፡፡ አያይዘውም ከአቶ አዲሱ ጋር ወደፊትም መልካም ግንኙነቱ እንደሚቀጥል ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል፡፡ አቶ አዲሱ በአምስት ዓመት ቆይታቸው አበርክተዋል ያሉዋቸውን ዋና ዋና ተግባራት ያስታወሱት የቦርድ ሊቀመንበሩ፣ ‹‹አቶ አዲሱ ለአቢሲኒያ ባንክ የተቻላቸውን ሁሉ አድርገዋል ብዬ አምናለሁ፤›› ብለዋል፡፡ የደቡብ ግሎባል ባንክ ፕሬዚዳንትነታቸውን ያስረከቡት አ