የሲዳማ ማክሮ ፋይናንስ ባለፉት 15 ኣመታት ተቀማጭ ካፒታሉን ከ200ሺ ብር ወደ ሁለት ሚሊዮን ዶላር ማሳደግ ብችልም፤ በዞኑ የማክሮ ፋይናንስ ገበያ ያለው ተወዳዳሪነት እየቀነሰ ነው
እንደፈረንዶቹ ዘመን ኣቆጣጠር በ 1998 ኣመተምህረት ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ነገር ግን ሰርተው መለወጥ የምችሉ፤ በገጠር እና ከተማ ነዋሪ የሆነው እና ኣማራጭ የገንዘብ ተቋማት በኣቅራቢያቸው የሌሏቸው ዜጎች ለመረዳት ተብሎ በ 200 ሺ ብር ካፒታል የተቋቋመው የሲዳማ ማክሮ ፋይናንስ ባለፉት 15 ኣመታት ተቀማጭ ካፒታሉን ወደ ሁለት ሚሊዮን ዶላር ማሳደግ ብችልም፤ በዞኑ የማክሮ ፋይናንስ ገበያ ያለው ተወዳዳሪነት እየቀነሰ ነው። የማክሮ ፋይናሱ ኣሴት ( Assets) ባለፉት ኣስርተ ኣመታት ከ 2 ነጥብ 3 ሚሊዮን ዶላር ወደ 1 ነጥብ 9 ሚሊዮን ዶላር ወርዷል፤ የማክሮ ፋይናንሱ ኤኪቲይ ( Equity) ደግሞ ከ 1 ነጥብ 9 ሚሊዮን ዶላር ወደ 619 ሺ 085 ከ 06 ሳንቲም ወርዷል፤ ግሮስ ሎን ፖርትፎልዮ ( Gross Loan Portfolio) ደግሞ ከ 657 ሺ 678 ከ 99 ሳንቲም ወደ 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ኣድጓል፤ ቀድሞ የሲዳማ ልማት ፕሮግራም በኃላ ላይ ደግሞ የሲዳማ ልማት ኮፕሬሽን እህት ኩባንያ ሆኖ በፍቃድ በቁጥር 40/1996 በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ቁጥጥር ስር ሆኖ የተመዘጋበው የሲዳማ ማክሮ ፋይናንስ በሲዳማ ዞን ውስጥ ባሉ የገጠር እና ከተማ ቀበሌያች የብድር ኣገልግሎት በመስጠት ላይ ሲሆን ወደ 50 ሺ የሚጠጉ የኣገልግሎቱ ተጠቃሚዎች እንዳሉት ታውቋል። ከኤም ኤፍ ኣይ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ማክሮ ፋይናንሱ እኣኣ በ 2012 ኣም 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ግሮስ ሎን ፖርትፎሊዮ ሲኖረው፤ በኣማካይ 51 ነጥብ 8 ዶላር ማለትም ወደ ኣንድ ሺ ብር ለየኣንዳንዱ ተበዳር ኣበድሯል። የማክሮ ፋይናንሱ ከ 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ዶላር በላይ ተቀማጭ ገንዘብ ኣለው። ለ