Posts

የMekane Yesus Church ኣመጣጥ በሲዳማ

Image
ሲዳማን በተመለከተ በተለያዩ ቋንቋዎች ከተጻፉ መጽሐፊት መካከል በዚህ ሳምንት እንድያነቡት የወደድነው በ Tolo እና Arne (Uppsala University, Humanistisk-samhällsvetenskapliga vetenskapsområdet, Faculty of Theology, Department of Theology) ለዶክተሬት ዲግሪ ሟሟያነት  Sidama and Ethiopian: The emergence of the Mekane Yesus Church in Sidama በሚል ርዕስ የተጻፈውን የምርምር ስራ ይሆናል። መልካም እሁድ እና ንባብ ይሁንላችሁ! Abstract (en)  : The present work belongs to local African church history and international mission history.The author shows why and how the Sidama people in south Ethiopia became part of theevangelical movement. During the last hundred years this group has experienced a lot ofchanges, incorporated in the greater Ethiopia, being influenced by the internationalmissionary movement, occupied by an European power and becoming a part of themodernising movement. As a result of all the changes and impulses the people faced, the Sidama to a great extendturned away from their traditional worldview and practices including their religion andacc

ከዶ/ር አንበሴ ተፈራ የምርምር ስራዎች መካከል...

Image
የኢትዮጵያ ብሔረሰቦችና ቋንቋዎቻቸው አጭር ቅኝት ( የዚህ አጭር ጽሁፍ አዘጋጅ ዶ/ር አንበሳ ተፈሪ ሲዳማ ውስጥ ይርባ በምትባል ቦታ በ1962 ተወለዱ።በ1984 ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፡ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን፡ በ1987 ደግሞ ሁለተኛቸውን፡ በቋንቋ ጥናት ተቀበሉ።ከ1984 ጀምሮም፡ ወደ እስራኤል እስከተሰደዱበት 1990 ድረስ፡በተማሩበት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ውስጥ በመምህርነት አገልግለዋል።ከ1990 ጀምሮ ደግሞ በእስራኤል በተለያየ ቦታ በሚገኙ፡ ዩኒቨርስቲዎች፡እንዲሁም)የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ጭምር አማርኛንና የቋንቋ ጥናትን አስተምረዋል።መልካም ንባብ!) ኢትዮጵያ በተለምዶ 3 ሺ ዘመን ታሪክ ያላት ሲሆን በአንዳንድ ታሪካዊና የአርኪኦሎጂያዊ ቁፋሮ መረጃዎች ግን ይህ ታሪካዊ ዕድሜ እስከ 5 ሺ ዓመት ሊደርስ ይችላል። ይህቺ ረጅም ታሪክ ያላት አገር በአሁኑ ጊዜ በኦፊሲዬላዊነት 73 “በሕይወት ያሉ” ቋንቋዎች አሏት። የኢትዮጵያ 73 ቋንቋዎች የሚመደቡት በ2 የቋንቋ ቤተሰቦች ውስጥ ነው።እነዚህም አፍሮ-እስያዊ እና ኒሎ-ሰሐራዊ (ዓባይ-ሰሐራዊ) ናቸው። አፍሮ እስያዊ ቋንቋዎች በሰሜን አፍሪቃና በደቡብ ምዕራብ እስያ የሚነገሩ ሲሆን 6 ንዑሳውያን ቤተሰቦች አሉት። እነዚህም ጥንታዊ ግብጽ፣ በርበር፣ ቻዳዊ፣ ኩሻዊ (ሐማዊ)፣ ኦሞአዊና ሴማዊ ቋንቋዎች ናቸው። ከእነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ውስጥ 3ቱ ማለትም ጥንታዊ ግብጽ፣ በርበር እና ቻዳዊ በኢትዮጵያ የማይነገሩ ሲሆን የተቀሩት 3ቱ ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ ይነገራሉ። እነዚህም ኩሻዊ (ሐማዊ)፣ ኦሞአዊና ሴማዊ ቋንቋዎች ናቸው። በዕድሜ ረገድ ኩሻዊና ኦሞአዊ ጥንታዊ ቋንቋዎች ሲሆኑ ሴማዊ ቋንቋዎች ከእነሱ ቀጥለው ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ናቸው። ሴማዊ ቋንቋዎች የሚባሉት ግዕዝ

መንግሥትና የአውሮፓ ኅብረት በሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ላይ ሳይስማሙ ተለያዩ

‹‹ዲሞክራሲ እንደ ጃኬት ከአውሮፓ ተሰፍቶ አይመጣም›› መንግሥት የአውሮፓ ኅብረትና የኢትዮጵያ መንግሥት በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች እንዲሁም በአካባቢው ሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ ሰሞኑን ሲመክሩ፣ በአገሪቱ የዲሞክራሲና የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ግምገማ ሳይስማሙ ቀርተዋል፡፡  ባለፈው ሐሙስ ነሐሴ 21 ቀን 2006 ዓ.ም. ጠዋት በጽሕፈት ቤታቸው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ እንዳሉት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በተገኙበት የአውሮፓ ኅብረት ተወካዮች ከኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር በኢኮኖሚያዊ ልማት፣ በዕርዳታ፣ በንግድ፣ በኢንቨስትመንትና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ እጅግ ጠቃሚ የሆነ ምክክር አድርገዋል፡፡  የአውሮፓ ኅብረት ለኢትዮጵያ የሚሰጠው የኢኮኖሚ ዕርዳታ ከፍተኛውን መጠን የሚይዝ መሆኑ የተናገሩት አምባሳደር ዲና፣ አገሪቷ ውስጥ ባለው የዲሞክራሲና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ላይ ግን ሳይስማሙ መለያየታቸውን ገልጸዋል፡፡ በእስር ላይ ስለሚገኙት ጦማሪያንና ጋዜጠኞች አስመልክቶ ውይይት ስለመደረጉም ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር፡፡ ከሰብዓዊ መብትና ሐሳብን በነፃነት ከመግለጽ መብት ጋር ተያይዞ የታሳሪዎች ጉዳይ መነሳቱን ገልጸው፣ ‹‹በእስር ላይ ያሉት ጋዜጠኞች የታሰሩት ጋዜጠኞች በመሆናቸው አይደለም፤›› የሚለው የመንግሥት አቋም በአውሮፓ ኅብረት ተቀባይነት አለማግኘቱን አስታውቀዋል፡፡ እንዲሁም ኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው የዲሞክራሲና የሰብዓዊ መብት ችግር በማናቸውም የዲሞክራሲ ሒደት ውስጥ የሚያጋጥም እንጂ፣ ‹‹ሲስተሚክ›› አይደለም የሚለው የመንግሥት አቋም ነው፡፡ የአውሮፓ ኅብረት ግን መንግሥት በተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችና በ

Sidama Traditional Medicinal Plants

Image
McAlvay_Sidama_Plant_Based_Medicine.pdf ምንጭ፦ http://www.surgery.wisc.edu/system/assets/1951/McAlvay_Sidama_Plant_Based_Medicine.pdf?1389376111

በሲዳማ መዲና ሐዋሳ ስለተሰየመችው የኢትዮጵያ ንግድ መርከብ ምን ያውቃሉ?

Image
የኢትዮጵያ ንግድ መርከብ ድርጅት በቅርብ በቻይና ካሰራቸው እና በክልል ከተሞች ስም ከሰየማቸው መከቦች መካከል ኣንዷ የሆነችው ሐዋሳ በኣይነቷ ታንከር ወይም ድፍድፍ ነዳጅ ጫኚ ስትሆን፤ 26ሺ820 ቶኔጅ የመያዝ ኣቅም ኣላት። መርከቧ 187 ነጥብ 8 ሜትር በ 32 ሜትር ሪዝመት ኣላት፤ ክብደቷ ደግሞ  42 ሺ 190 ዴድ ዌይት ነው። የተመረተችው እንደፈረንጆቹ ዘመን ኣቆጣጠር በ 2ሺ 13  ሲሆን በኣሁኑ ሰዓት በ13 ነጥብ 3 ኬኤን በ328ድግሪ ፊጥነት 27 ነጥብ 77716 ድግሪ ላቲቱድ እና 50 ነጥብ 63666ድግሪ ሎንግቱድ በፐሪሺያ ወሽመጥ በመቅዘፍ ላይ ትገኛለች። ለተጨማሪ መረጃ ከታች  ይመልከቱ፦ IMO:  9617454 MMSI:  624018000 Call Sign:  ETHW Flag:  Ethiopia (ET) AIS Type:  Tanker Gross Tonnage:  26820 DeadWeight:  42190 Length x Breadth:  187.8m × 32m Year Built:  2013 Status:  Active Last Position Received In Range Info Received: 3 min ago (2014-08-29 15:27) Area:   Persian Gulf Latitude / Longitude: 27.79563° / 50.62411° Status: Underway using Engine Speed/Course:   13.2kn / 329° AIS Source:   1947 Itineraries History Latest Positions Nearby Vessels Show on live map    Wind:  11 knots Wind direction:  SE (150 o ) Tempe