Posts

Ethiopia's Ethnic Federalism And The Right To Self-Determination

Image
Ethiopia's Ethnic Federalism And The Right To Self-Determination The Experience Of Sidama People By Kinkino Kia The Ethiopian state that emerged as result of the 19th c. successive expansion and centralizing measures under monarchical and dictatorial Derg rules miserably failed to reflect and accommodate the existing diversity on the ground. After the military Derg regime was ousted by the joint military assault of the different ethno-national groups, the new TPLF/EPRDF elites who came to control a political power restructured the country according to their ideology and promised the right to self-determination including secession, devolving political, administrative and economic power to ethnically defined regional states, which however, required a real reckoning. This book provides a relatively comprehensive empirical account as to how this hallowed right to self-determination is played out in reality in a local context, with a special focus on the experience of Si

ሃዋሳ እና ኣከባቢዋ በተጋዦች ኣይን

Image
Heading for Hawassa AUGUST 13, 2014   /  MICHAEL STRAUSS   /  COMMENTS OFF Leaving Yabello , I had been warned that the road all the way up to Hawassa was under construction , so I was up early to get a good start . I rode to the fuel station next to the motel , they were out , then across the road to join the ever growing queue for petrol , there must have been over 100 plastic containers lined up and around 20 tuk- tuks and motorcycles  in front of me , so I joined the line . The pump was only to open after 8 , being a faranji has its advantages , more so a faranji on a scooter , we made many friends who took it apon themselves to take me to the front of the queue , so as the pump came to an unconvincing life , Vic and I filled  tank and container and headed out . The road works started in town as did  our nine hour journey to cover the 300 kilometres up to Hawassa . The price of progress the inconvenience and road trauma . Those who take this route in years to come will

ኢትዮጵያ ወደ ውጪ ከምትልከው ቡና የምታገኘው ገቢ በ25 በመቶ እንደሚያድግ እየተነገረ ነው፤ 1/3ኛውን የቡና ምርት ኣቅራቢ የሆኑትን የሲዳማ ቡና ኣምራቾችን ተጠቃሚ ለማድረግ ምን ታስቧል?

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 15፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) ኢትዮጵያ በ2014/15 ወደ ውጪ ከምትልከው የቡና ምርት ከ900 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ልታገኝ እንደምትችል ተገለጸ። ይህም ቀደም ሲል ከነበረው ገቢ የ25 በመቶ እድገት ያሳየ ነው ተብሏል። የኢትዮጵያ ቡና ላኪዎች ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አለምሰገድ አሰፋ እንደተናገሩት፥ በያዝነው አመት የብራዚል ቡና በድርቅ በመመታቱ የቡና ዋጋ መሻሻል አሳይቷል። በዚህም አሁን በገበያ ላይ ያለው የቡና ዋጋ ባለበት ሊቀጥል እንደሚችል ነው አቶ አለምሰገድ የጠቆሙት። ዋነኛዋ ቡና አምራች ሀገር ብራዚል ባስተናገደችው ድርቅ የተነሳ አቅርቦቷ መቀነሱን ተከትሎ፥ ኒውዮርክ እስከ ጥር ወር ድረስ 70 በመቶ የቡና ፍላጎትን ከኢትዮጵያ በመግዛት ስትሸፍን መቆየቷም ተዘግቧል። በአፍሪካ ቀዳሚዋ ቡና አምራች ሀገር ኢትዮጵያ፥ ባለፉት 12 ወራት ወደ ውጪ ከላከችው ቡና 719 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ያገኘች ሲሆን ፥ ይህም ካለፈው አመት ጋር ሲነፃፃር በ3 ነጥብ 7 በመቶ ዝቅ ያለ ነው። ሀገሪቱ በዚህ አመትም ከ500 ሺህ ቶን በላይ ቡና ታመርታለች ተብሎ ይጠበቃል ያሉት ስራ አስኪያጁ፥ ከአጠቃላይ ምርቱ ግማሽ ያህሉም ለውጭ ገበያ እንደሚቀርብ ተናግረዋል። የቡና አምራች አካባቢዎች መስፋፋት ለምርቱ ማደግ አስተዋፅኦ ያደርጋልም ነው ያሉት። በሼክ ሙሃመድ አላሙዲ የሚተዳደረው የሆራይዘን ፕላንቴሽን፥ 10 ሺህ ሄክታር  በበበቃ እንዲሁም 12 ሺህ 114 ሄክታር የቡና እርሻ መሬት መግዛቱን አስታውሶ የዘገበው ብሉምበርግ ነው። ኤፍ.ቢ.ሲ

ኢትዮጵያ በናንጂንግ ኦሎምፒክ ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆነች

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 19፣ 2006 ፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ በቻይና ናንጂንግ እየተካሄደ ባለው የታዳጊ ወጣቶች የኦሎምፒክ ጨዋታ ቅዳሜና ትናንት በተደረጉ የአትሌቲክስ የፍጻሜ ውድድሮች ከአፍሪካ አንደኛ ከአለም የ21ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። በሴቶች ኮከብ ተስፋዬ በ1 ሺህ 500 ሜትር 4 ደቂቃ ከ15 ሰኮንድ ከ38 ማይክሮ ሰከንድ ውድድሩን በአንደኝነት በማጠናቀቅ የወርቅ ሜዳሊያ አስመዝግባለች። በ8 መቶ ሜትር ሴቶች የፍጻሜ ውድድርደግሞ ሀዊ አለሙ በ2 ሰዓት ከ6 ደቂቃ ከ01 ማይክሮ ሰከንድ ሁለተኛ ሆና ስትጨርስ፥ በሴቶች የ3 ሺህ ሜትር ብርሃን ደምሴ ውድድሩን በሶስተኝነት አጠናቃለች። በወንዶች ዮሚፍ ከጀልቻ በ3 ሺህ ሜትር ፍጻሜ በ7 ደቂቃ ከ56 ሰከንድ ከ20 ማይክሮ ሰከንድ ውድድሩን በአንደኝነት በማጠናቀቅ የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝቷል። በወንዶች 1 ሺህ 500 ሜትር ደግሞ ሙሉጌታ አሰፋ በሁለተኝነት ማጠናቀቅ ችሏል። ውድድሩ በመጪው ረቡዕ ፍጻሜውን የሚያገኝ ሲሆን፥ ኢትዮጵያውያን ወጣት ታዳጊ ስፖርተኞች ጥሩ ፉክክር እያደረጉ ይገኛሉ። ዛሬ ከሰዓት በኋላ የ2 ሺህ ሜትር መሰናክል በሁለቱም ጾታና በ800 ሜትር ወንዶች ኢትዮጵያውያን በርቀቱ ተካፋይ ይሆናሉ ። ምንጭ፦  ኤፍ/ቢ/ሲ

በሐዋሳ ከተማ ህዝባዊ ስብሰባዎችን ማድረግ ለተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ኣስቸጋሪ እንደሆነ ቀጥሏል

-ኢራፓ በሐዋሳ ሊያደርገው የነበረው ስብሰባ እንዳይካሄድ መከልከሉን ገለጸ - በወጣው መግለጫ የፓርቲው መሪዎች አልተግባቡም የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ (ኢራፓ) ነሐሴ 11 ቀን 2006 ዓ.ም. እና በተለዋጭ በተያዘ ፕሮግራም ነሐሴ 18 ቀን 2006 ዓ.ም. በደቡብ ክልል ርዕሰ ከተማ በሐዋሳ ሊያደርገው የነበረው ሕዝባዊ ስብሰባ፣ በኢሕአዴግ ተፅዕኖ ፈጣሪነት ተገቢ ባልሆነ ምክንያትና ቢሮክራሲ መከልከሉን አስታወቀ፡፡ በፓርቲው የተሰጠው መግለጫ ስብሰባ እንዳናካሂድ ተከልክለናል ቢልም፣ የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ተሾመ ወልደ ሰማያት ግን መግለጫው የወጣው ‹‹የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ ሳይወያይበት›› ነው በማለት ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ምክትል ፕሬዚዳንቱ፣ ‹‹ኢራፓ የፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባል ስለሆነ ጉዳዩን ወደዚያ መውሰድ እንጂ መግለጫ ለማውጣት መቸኮሉ አስፈላጊ አይደለም፤›› በማለት ገልጸዋል፡፡   የፓርቲው ፕሬዚዳንት አቶ ተሻለ ሰብሮ በበኩላቸው፣ ‹‹›እያንዳንዱ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ አይወያይም፤›› ብለው፣ መግለጫውን በፓርቲው ማሕተም ማውጣታቸውን ገልጸዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ‹‹በሁሉም ጉዳዮች ላይ መግለጫ ለመስጠት የግድ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መሰብሰብ አይኖርበትም፤›› በማለት የወጣው መግለጫ የፓርቲው አቋም ነው በማለት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ፓርቲው በሐዋሳ ሊያደርገው የነበረው ሕዝባዊ ስብሰባ ዓላማ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ የፖለቲካ ፕሮግራሙን ለማስተዋወቅ፣ በአገራዊና ሕዝባዊ መግባባት አስፈላጊነት ላይ ግንዛቤ ለማስጨበጥ፣ እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲዎችን የሥነ ምግባር ደንብን ለማስረዳት እንደነበር በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡  ከዚህ በተጨማሪም መግለጫው፣ ‹‹ፓርቲያችን በያዘው የሕዝባዊ ስብሰባ ፕሮግ