የፊቼን በዓል በዓለም ቅርስነት ለመስመዝገብ ከሚያስፈልጉ ዶክሜንቶች መካከል ኣንዱ የሆነው እና የፊቼን በኣል ኣከባበር የምያሳይ ፊልም እስከኣሁን ድረስ ኣለመሟላቱ ተገለጸ
የወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ ከ ተባበሩት መንግስታት የትምህርት፤ ሳይንስ እና ባህል ማዕከል _ ዩኔስኮ ያሰባሰ ው መረጃ እንደሚያመለክተው፤ የፊቼን በኣል በኣለም ቅርስነት ለመመዝገብ መሟላት ካለባቸው ዶክመንቶች መካከል ኣንዱ የሆነው የ 10 ደቂቃ ፊልም ኣልተሟላም። ዩኔስኮ የማይዳሰሱና የማይጨበጡ ብሎም የመጥፋት ኣደጋ የተጋረጠባቸውን የሲዳማን ኣዲስ ኣመት በኣል ፊቼን የመሳሰሉ ኢንታጀብል ባህሎችን ለመጠበቅ እና ለመከባከብ ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት ቅርሶችን በኣለም ቅርስነት ለመመዝጋብ፦ ባህሉ ኢንታጀብል መሆኑን የምያሳይ ማስረጃ፤ ባህሉ በኣስቸኳል ጥበቃ ካልተደረገለት ልጠፋ እንደሚችል የሚገልጽ መረጃ፤ ባህሉ በኣለም ቅርስነት እንድመዘጋብ መመረጡ እና እንድመዘጋብም ዘንድ የባህሉ ባለቤት የሆነው ህዝብ እንደምፈል የገለጸበት በፊርማ የተደገፈ መረጋገጫ፤ ባህሉ እንድመዘጋብ የመጠያቂያ በጥንቃቄ የተሞላ ፎርም፤ ሰለባህሉ በስፋት የሚያትት ጥናት እና በፎቶናበፊልም የተደገፈ የባህሉን ኣከባበር ስነስርኣት የሚያሳዩ መረጃዎች መቅረብ ኣለባቸው። ኢንታጀብል ቅርሶችን የመመዝጋብ ስራ የሚስራው የዩኔስኮ ኮሚቴ ኣንድን ባህል በኣለም ቅርስነት ለመመዝጋብ የግድ ከላይ የተጠቀሱት ማስረጃዎች እንድሟሉለት ይጠይቃል። ኮሚቴው በየኣመቱ ወደ 50 የሚጠጉ ባህሎችን መርምሮ ለወሳኔ የሚያቀርብ ሲሆን፤ የምርመራው ህዴት ከሁለት ኣመታት በላይ ልወስድ ይችላል። የማስመዝጋቡን ህዴት ለማፋጠን ኮሚቴው በየኣመቱ የማስረጃ ማቅረቢያ ጊዜ ገደብ ያበጄ ሲሆን፤ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ መሰረት ማስረጃዎች ያቀረቡ ባህሎች ብቻ በኮሚቴው የምታዩ የሆናል። የሲዳማ ኣዲስ ኣመት በኣል ፊቼን የተመለከቱ ማስረጃዎች በኣብዘኛው የተማሉ ቢሆን፤ የባህሉን ኣካባበር የሚያሳየ