Posts

‹‹በጣም የጎላ የብር ምንዛሪ ቅነሳ የምናደርግበት ምክንያት የለም›› አቶ ሬድዋን ሁሴን

Image
መንግሥት በጣም የጎላ የብር ምንዛሪ ቅነሳ የሚያደርግበት ምክንያት እንደሌለ፣ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ሚኒስትር አቶ ሬድዋን ሁሴን አስታወቁ፡፡  ሚኒስትሩ ባለፈው ሰኞ ከቀትር በኋላ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ የዓለም ባንክ የብር የመግዛት አቅም እንዲቀንስ የሰጠውን ምክረ ሐሳብ አስመልክቶ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ ነው ይህንን የተናገሩት፡፡  የዓለም ባንክ እ.ኤ.አ. ጁላይ 22 ቀን 2014 የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ካቀረባቸው የመፍትሔ ሐሳቦች መካከል የብር የመግዛት አቅምን በመቀነስ፣ የአገሪቱን የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ማጎልበትና የውጭ ምንዛሪ ገቢን ማሳደግ እንደሚቻል መምከሩ ተዘግቧል፡፡  ይህንን ምክረ ሐሳብ ተንተርሶ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት ሚኒስትሩ፣ ‹‹የቀረቡ አማራጮች በሙሉ አይተገበሩም፣ መንግሥት አጠቃላይ አማራጮችን ግንዛቤ ውስጥ አስገብቶና ትርፍና ወጪውን አገናዝቦ በአጠቃላይ ለኢኮኖሚው ይጠቅማል የሚለውን ዕርምጃ ነው የሚወስደው፤›› ብለዋል፡፡  መንግሥት በ2002 ዓ.ም. የብር የመግዛት አቅምን በአሥር በመቶ፣ በ2003 ዓ.ም. ደግሞ 20 በመቶ በመቀነስ ወደ ዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ትግበራ መግባቱን አስታውሰዋል፡፡  ‹‹ይህ የተደረገው በተረጋጋ የማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታ ውስጥ በመሆን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድን ለመተግበር በማቀድ ነው፤›› ብለዋል፡፡ መንግሥት የብር የመግዛት አቅምን ዝቅ እንዲል ከማድረጉ በፊት ስፋት ያለው የማክሮ ኢኮኖሚ ትንተና እንደሚያደርግ የገለጹት ሚኒስትሩ፣ ‹‹አሁን ባለው ሁኔታ በጣም የጎላ የምንዛሪ ቅነሳ የምናደርግበት ምክንያት የለም፡፡ ተለቅ ያለ ቅነሳ አሁን ትክክለኛ ነው ተብሎ አይታሰብም፤››

Two Tales, or One?: On Ethiopia’s Federalism and South Africa’s Apartheid

Image
By Tsegaye R Ararssa* 1.     Introduction What is the story of the Ethiopian federal experiment? What stories does it tell? And what stories can be told about it? Feeding from and into the ever polarized and polarizing ‘debate’ on Ethiopia’s politics, Dr Taye Negussie recently argued that the Ethiopian federal arrangement is synonymous with apartheid’s ‘racial federation’. In a similar vein, Dr Asfawossen Asrate also remarked that “ethnic federalism amounts to nothing but apartheid.” [i]  In this piece, I seek to explore the tales the Ethiopian federal experiment tells (and masks) with a view to shedding light on whether, by juxtaposing the two systems, there emerges a tale of two federations or two tales of two differently unjust governance systems. In what follows, I will first offer a sketchy ‘description’ of the federation in context. I will then discuss what to look for in a federal system as its fundamental features. I do this in order to determine whether the tale

No Case of Ebola Virus in Ethiopia

Image
The Ethiopian Government has dispelled rumours of alleged cases of the Ebola in the country. An East Africa correspondent reports that information that Ebola may have been brought into the country by two Chinese who travelled to Nigeria went viral in Addis Ababa last week. Ahmed Amano, the Director, Communication, at the Ethiopian Ministry of Health, told the media in Addis Ababa that the two Chinese national tested negative to the Ebola virus. The Chinese were treated for malaria after being admitted at the Korean hospital in Addis Ababa, he said. Amano said the Ethiopian Government had taken measures to prevent the spread of the virus, including screening of passengers from West Africa on arrival at Bole international airport in Addis Ababa. “The airport is already checking passengers who are coming from West Africa countries with cases of Ebola.” The media recalls that the Ethiopian Government has established a National Committee on Ebola, headed by the Prime Minister, Hailemaria

በውጪ የሚገኙ ተጫዋቾች ነሐሴ 18 ብሔራዊ ቡድኑን ይቀላቀላሉ

Image
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሚቀጥለው ዓመት ለሚከናወነው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጳጉሜ 2 ቀን 2006 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ስታዲየም የአልጄሪያ አቻውን ያስተናግዳል፡፡ በአፍሪካ ለተለያዩ አገሮች ክለቦች በመጫወት ላይ የሚገኙ የቡድኑ ወሳኝ ተጫዋቾች ነሐሴ 18 አዲስ አበባ ገብተው ዝግጅት እንደሚጀምሩ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡  ፖርቱጋላዊው የዋሊያዎቹ አሠልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ ከአገር ውስጥ ክለቦች የመረጧቸውን ተጫዋቾች ይዘው በብራዚል ከተለያዩ ክለቦች ጋር የወዳጅነት ጨዋታ በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ ለግብፅ፣ ለደቡብ አፍሪካና ለሱዳን ክለቦች የሚጫወቱት ሳላዲን ሰይድ፣ ኡመድ ኡክሪ፣ ጌታነህ ከበደና አዲስ ሕንፃ ፌዴሬሽኑ ከክለቦቻቸው ጋር ባደረገው ግንኙነት መሠረት በሚቀጥለው ሳምንት ብሔራዊ ቡድኑን እንደሚቀላቀሉ ይጠበቃል፡፡  በብራዚል ከተለያዩ ክለቦች ጋር የአቋም መለኪያው ጨዋታ እያደረገ የሚገኘው ብሐራዊ ቡድኑ እስከ ነሐሴ 17 ቀን ድረስ እንደሚቆይ ታውቋል፡፡ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ምንም እንኳ ያለው ነገር ባይኖርም፣ በስዊድን የሚጫወተው የሱፍ ሳላህ ዋሊያዎቹን እንዲቀላቀል አሠልጣኙ መጠየቃቸው ዘገባዎች አመልክተዋል፡፡  ምንጭ፦ ሪፖርተርጋዜጣ

የኢቦላ ምልክት ለሚታይባቸው መታከሚያ የተለየ ሆስፒታል ተዘጋጀ

Image
- ወረርሽኙ በረራ የሚያስቆምበት ደረጃ አልደረሰም ተብሏል የኢቦላ ምልክት የሚታይባቸው ሰዎች የሚታከሙበት የተለየ ሆስፒታል በአዲስ አበባ ከተማ ተዘጋጀ፡፡ በኮተቤ ገብርኤል አካባቢ የሚገኘውና 95 በመቶ ያህል የተደራጀው ሆስፒታል ለጊዜው 10 አልጋዎች ሲኖሩት በቀጣይ 50 ይደርሳሉ ተብሏል፡፡ በምዕራብ አፍሪካ የተከሰተውንና ከአንድ ሺሕ በላይ ሰዎች የገደለውን የኢቦላ ወረርሽኝ ተከትሎ፣ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ያለውን ዝግጁነት አስመልክቶ ነሐሴ 8 ቀን 2006 ዓ.ም. በሰጠው መግለጫ፣ እስካሁን ድረስ ኢትዮጵያ የኢቦላ ተጠቂ ያላስመዘገበች ቢሆንም በማንኛውም ሰዓት ግን ወረርሽኙ ሊገባ ይችላል ብሏል፡፡ የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶ/ር ከሰተብርሃን አድማሱ እንደተናገሩት፣ የኢቦላን ምልክት የሚያሟላ ጉዳይ እስካሁን ወደ ኢትዮጵያ አልገባም፡፡ ኢቦላን የሚመስል ምልክትና ከምዕራብ አፍሪካ ወደዚህ የተጓጓዘ ታካሚ ሲኖር በአስቸኳይ ሪፖርት እንዲደረግ የአሠራር ሥርዓት መዘርጋቱ ተገልጿል፡፡ ከናይጄሪያ የመጡ ሁለት ቻይናውያን በኮሪያ ሆስፒታል ተኝተው ሲታከሙ በተደረገ ምርመራ ታካሚዎቹ ወባ እንደያዛቸው ታውቋል፡፡ ሆኖም ኢቦላ በማንኛውም ጊዜ ሊገባ ይችላል ተብሎ ስለሚጠበቅ፣ ኢትዮጵያ ወረርሽኙን ለመከላከል የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት እያጠናቀቀች መሆኑን ሚኒስትሩ አስታውቀዋል፡፡  ከቅድመ ዝግጅቶቹ መካከል አዲስ የተለየ ጠቅላላ ሆስፒታል ማቋቋም አንዱ ሲሆን፣ ይህም ተዘጋጅቶ የጤና ባለሙያዎች እንደተመደቡለትም ተገልጿል፡፡  ወረርሽኙ ወደ ምዕራብ አፍሪካ ከሚደረጉ የአየር በረራዎች ጋር ተያይዞ የመግባት ዕድሉ ሰፊ በመሆኑ፣ ከናይጄሪያ አራት ከተሞችም ወደ ኢትዮጵያ በረራዎች ስላሉና በቀን በአማካይ 500 የሚደርሱ ተጓዦች እዚህ ስለሚደርሱ ሥጋቶች አሉ፡፡ ከዚህ ጋር