Posts

Ethiopia arrive in Brazil for two week tour

Image
Ethiopia's Walia Ibex arrived safely in Brazil for a two week preparation tour ahead of the 2015 Africa Cup of Nations qualifiers where they are grouped with Malawi, Mali and Algeria. The East Africans will play five friendly matches with local sides that include AC Anapolina Club Do Remo at the Arena Baenao Gama, Brasiliense at the Boca do Jacare stadium and the last friendly will be against Itubiara at the 30,000 seater JK stadium. While in Brazil, the national team will stay at Hotel San Peter and will be training at one of the training centers that was used by the Brazilian national team during the World Cup. Coach Mariano Barreto, his assistant Daniel Tsehai, team doctor Dr. Terefe Tafa, Physio Behailu Abera have landed in Brazil. Jemal Tassew, Sesay Bancha, Ephrem Ashamo, Mesud Mohammed, Shemeles Tegegn, Andaregachew Yelake, Thok James, Abebaw Butako, Behanu Bogale, Mintesinot Adane, Akilu Ayanaw and Dawa Hottesa are some of the players already in Brazil. Player

የሃዋሳ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ጉባኤ በጀትና ደንቦችን በማፅደቅ ተጠናቀቀ

ሀዋሳ ሐምሌ 27/2006 የሃዋሳ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ በጀትና ሁለት ደንቦችን በማፅደቅ ትናንት ማምሻውን ተጠናቀቀ፡፡ ምክር ቤቱ በትናንትናው ውሎ የሃዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የ2006 በጀት አመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት በማድረግ በሙሉ ድምፅ አጽድቋል፡፡ በተለይ በከተማ ቀልጣፋና ውጤታማ የፍትህ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ ከመደበኛ ፍርድ ቤቶች በተጨማሪ አዳዲስ ምድቦችንና ተዘዋዋሪ ችሎሎቶች በመክፈት የተከናወኑ ስራዎች አበረታች በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ምክር ቤቱ አሳስቧል፡፡ ምክር ቤቱ በ2007 በጀት አመት ለመደበኛና ለካፒታል ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት አጽድቋል፡፡ በጀቱ የሚሸፈነው ከመንግስት ግምጃ ቤት፣ ከከተማ ገቢ እንዲሁም ከማዘጋጃ ቤት አገልግሎት ፣ ከጤናና ትምህርት ተቋማት ገቢ መሆኑም ተመልክቷል፡፡ በከተማው የሚከናወኑ የመልካም እስተዳደር፣ የልማትና ዴሚክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ስራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል የተመደበው በጀት ካለፈው በጀት አመት ጋር ሲነጻጸር  ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ ብልጫ ያለው ነው፡፡ የምክር ቤቱ ጉባኤ በተጨማሪም የሃዋሳ ሀይቅን እንዲሁም ተራራማና ረግረጋማ መሬት አያያዝና አጠቃቀምን ለመወሰን የወጣውንና  የስብሰባና ሰላማዊ ሰልፍ ስነ ሰርዓት ረቂቅ ደንቦች ላይ ከተወያየ በኋላ በሙሉ ድምፅ በማፅደቅ ትናንት ማምሻውን ተጠናቋል፡፡ Source: ENA ________________________________________________________ We welcome comments that advance the story through relevant opinion and data. If you see a comment tha

ብሮድካስት ባለሥልጣን ደቡብ ክልል የራሱን የቴሌቪዥን ሥርጭት እንዲጀምር ፈቃድ አልሰጠሁም አለ

Image
ዜናው የ http://www.ethiopianreporter.com ነው - ከ180 ሚሊዮን ብር በላይ ወጥቶበታል  -ብሮድካስት ባለሥልጣን ፈቃድ አልሰጠሁም አለ ከ2004 ዓ.ም. ጀምሮ በመቋቋም ሒደት ላይ የነበረው የደቡብ ክልል ቲቪ ከ180 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ሥራውን አጠናቆ ነሐሴ 17 ቀን 2006 ዓ.ም. ከተመረቀ በኋላ፣ በቀን የአሥር ሰዓት ሥርጭት እንደሚጀምር ተገለጸ፡፡  የደቡብ ክልል ሬድዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዮሐንስ ቱሬ ለሪፖርተር እንደገለጹት ከሆነ፣ በኢቲቪ በቀን ለአንድ ሰዓት ይተላለፍ የነበረው የክልሉ መንግሥት የቲቪ ፕሮግራም በክልሉ የሚኖሩትን በርካታ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቋንቋ፣ ባህል፣ ማኅበራዊ ኑሮ፣ ፖለቲካዊ ሥርዓት፣ የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀምና የመሳሰሉትን ጉዳዮች በላቀ ሁኔታ ለመግለጽ በቂ እንዳልሆነ በመታመኑ፣ ጣቢያውን የማቋቋም ሥራው በፕሮፖዛል መልክ በ2004 ዓ.ም. ከተሠራ በኋላ በ2005 ዓ.ም. የክልሉ መንግሥት አፅድቆት ነው የማቋቋሙ ሒደት የተጀመረው፡፡  በማቋቋም ሒደቱ ስቱዲዮ በመገንባት፣ የመሣሪያዎች ግዥ በመፈጸምና ሠራተኞችን በመቅጠር ያለፉትን ሁለት ዓመታት እንዳለፉ የጠቆሙት አቶ ዮሐንስ፣ ጣቢያውን ሙሉ በሙሉ ሥራ ለማስጀመር ከሚያስፈልጉ ሠራተኞች መካከል 70 በመቶ የሚሆኑ 110 ሠራተኞችን መቀጠራቸውን አመልክተዋል፡፡  ክልላዊና አገራዊ ጉዳዮችን በማንሳት ከዚህ በፊት ለሕዝብ እይታ ያልቀረቡ ርዕሰ ጉዳዮችን በማቅረብ የክልሉ ነዋሪዎችን ለማስተማርና ለማዝናናት ጣቢያው ቁልፍ መሆኑን አቶ ዮሐንስ አስረድተው፣ በመረጃ ነፃነት ሕጉ አማካይነት የክልሉ ነዋሪዎችና ሌሎች ተመልካቾች ወቅታዊ መረጃ እንዲያገኙ ለማድረግ ጣቢያው እንደሚ

የአፍሪካ መሪዎች በአሜሪካ

Image
ፎቶ ከ ሪፖርተር ጋዜጣ ቻይና በአፍሪካ ውስጥ ያላት ንግድና ኢንቨስትመንት ለአሜሪካ ራስ ምታት እንደሆነ ይነገራል፡፡ አሜሪካ በአፍሪካ ለምታደርገው ዕርዳታም ሆነ ኢንቨስትመንት ከሰብዓዊ መብት አጠባበቅ ጀምሮ ቅድመ ሁኔታ ታስቀምጣለች፡፡ ኩባንያዎቿም በአፍሪካ ኢንቨስት ከማድረጋቸው በፊት ስለ ደኅንነት፣ ፀጥታና ሰላም ብሎም በአገሪቱ ስላለው የሠራተኛ አያያዝ መብት በቅድሚያ መወያየት ይፈልጋሉ፡፡  ቻይና ደግሞ በምትሠራባቸው አገሮች የውስጥ ጉዳይ እጇን አታስገባም፣ አትጠይቅም፡፡ ትኩረቷ ያለው ኢንቨስትመንቷ ላይ ነው፡፡ በዚህም ከአፍሪካ መሪዎች ጋር ተመቻችታለች፡፡ በንግድና ኢንቨስትመንት እንዲሁም በኮንስትራክሽን ዘርፍ በአፍሪካ መሠረቷን ጥላለች፣ ተጠናክራለች፡፡ የአፍሪካ መሪዎችንና የንግድ ማኅረሰብ አባላትን ሲያሻት በተናጠል፣ ሲያሻት በቡድን እያወያየች በተለያዩ ኢንቨስትመንቶች በጋራና በተናጠል ትሠራለች፡፡ ብድር ለመስጠትም የምትሰጠውን አገር የውስጥ ጉዳይ ከቅድመ ሁኔታ ወይም ከመደራደሪያ ውስጥ አታስገባውም፡፡  በመሆኑም በአፍሪካ ውስጥ ከአሜሪካ በበለጠ ሰፊ ድርሻ ይዛ ትሠራለች፡፡ ቻይና ለአፍሪካ የምትልከውም ሆነ ከፍሪካ ወደ አገሯ የምታስገባው አሜሪካ ከአፍሪካ ጋር ካላት ሲነፃፀር የአንበሳውን ድርሻ ይይዛል፡፡ በመሆኑም አሜሪካ በቻይና እጅ ከገባው የአፍሪካ ኢንቨስትመንት መቋደስና በአፍሪካ ውስጥም መኖሯን ማሳወቅ ትፈልጋለች፡፡ በመሆኑም አሜሪካ ከዚህ በፊት አድርጋ የማታውቀውን የአሜሪካና የአፍሪካ መሪዎች ጉባዔ እያካሄደች ነው፡፡ የአፍሪካ መሪዎች ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ስብሰባ ተቀምጠዋል፡፡ ባለፈው ሰኞ በተጀመረውና ረቡዕ በሚያበቃው የአሜሪካና የአፍሪካ መሪዎች

በዚህ ኣመት በሲዳማ ዞን 21 ኣዲስ የተሽከርካሪ ስምሪት መስመሪ መከፈቱ ተሰማ

Image
በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በሲዳማ ዞን ኣዳዲስ የተሽከርካሪ ስምርት መስመር መከፈቱን የክልሉ ትራንስፖርት ቢሮ  ገለጸ። የቢሮውን ኃላፊ አቶ ላጫ ጋሩማ ጠቅሶ ኢዜአ እንደዘጋበው፤ በዞኑ 21 ኣዲስ የሰምሪት መስመር ከፍቷል። አዲስ በተከፈቱ የስምሪት መስመሮች ቋሚ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎችን በመመደብና ታሪፍ በማውጣት የትራንስፖርት አገልግሎት ሳይቆራረጥ እንዲቀጥል መደረጉንና በዚህም አርሶ አደሩ ምርቱን ገበያ ለማቅረብና በእግር ረዥም መንገድ ከመጓዝ እንዳላቀቀው እኙሁ ኃላፊ ተናግረዋል። በሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ የዶሬ ባፈና ነዋሪ አርሶ አደር ብርሀኑ ባጢሶና አርሶ አደር ይፍሩ ይማም ቀደም ሲል ከሀዋሳ እስከ ወረዳ ከተማ  ካልሆነ ወደ ገጠር ቀበሌ ለመጓዝ የፈረስ ጋሪና የጭነት መኪና ይጠቀሙ እንደነበር አስታውሰው አሁን በሳምንቱ አብዛኛው ቀናት መለስተኛ አውቶብሶች በበመደባቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል። የዜና ምንጩ ኢዜኣ ነው