ብሮድካስት ባለሥልጣን ደቡብ ክልል የራሱን የቴሌቪዥን ሥርጭት እንዲጀምር ፈቃድ አልሰጠሁም አለ
ዜናው የ http://www.ethiopianreporter.com ነው - ከ180 ሚሊዮን ብር በላይ ወጥቶበታል -ብሮድካስት ባለሥልጣን ፈቃድ አልሰጠሁም አለ ከ2004 ዓ.ም. ጀምሮ በመቋቋም ሒደት ላይ የነበረው የደቡብ ክልል ቲቪ ከ180 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ሥራውን አጠናቆ ነሐሴ 17 ቀን 2006 ዓ.ም. ከተመረቀ በኋላ፣ በቀን የአሥር ሰዓት ሥርጭት እንደሚጀምር ተገለጸ፡፡ የደቡብ ክልል ሬድዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዮሐንስ ቱሬ ለሪፖርተር እንደገለጹት ከሆነ፣ በኢቲቪ በቀን ለአንድ ሰዓት ይተላለፍ የነበረው የክልሉ መንግሥት የቲቪ ፕሮግራም በክልሉ የሚኖሩትን በርካታ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቋንቋ፣ ባህል፣ ማኅበራዊ ኑሮ፣ ፖለቲካዊ ሥርዓት፣ የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀምና የመሳሰሉትን ጉዳዮች በላቀ ሁኔታ ለመግለጽ በቂ እንዳልሆነ በመታመኑ፣ ጣቢያውን የማቋቋም ሥራው በፕሮፖዛል መልክ በ2004 ዓ.ም. ከተሠራ በኋላ በ2005 ዓ.ም. የክልሉ መንግሥት አፅድቆት ነው የማቋቋሙ ሒደት የተጀመረው፡፡ በማቋቋም ሒደቱ ስቱዲዮ በመገንባት፣ የመሣሪያዎች ግዥ በመፈጸምና ሠራተኞችን በመቅጠር ያለፉትን ሁለት ዓመታት እንዳለፉ የጠቆሙት አቶ ዮሐንስ፣ ጣቢያውን ሙሉ በሙሉ ሥራ ለማስጀመር ከሚያስፈልጉ ሠራተኞች መካከል 70 በመቶ የሚሆኑ 110 ሠራተኞችን መቀጠራቸውን አመልክተዋል፡፡ ክልላዊና አገራዊ ጉዳዮችን በማንሳት ከዚህ በፊት ለሕዝብ እይታ ያልቀረቡ ርዕሰ ጉዳዮችን በማቅረብ የክልሉ ነዋሪዎችን ለማስተማርና ለማዝናናት ጣቢያው ቁልፍ መሆኑን አቶ ዮሐንስ አስረድተው፣ በመረጃ ነፃነት ሕጉ አማካይነት የክልሉ ነዋሪዎችና ሌሎች ተመልካቾች ወቅታዊ መረጃ እንዲያገኙ ለማድረግ ጣቢያው እንደሚ