Posts

የኤድስ ስርጭትን እኤአ እስከ 2030 ማቆም እንደሚቻል ተመድ ገለጸ

ሐምሌ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኤድስ ኤጀንሲ እንደገለጸው ኢትዮጵያና ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ በብዙ አገሮች የኤደስ ወረርሽኝ ስርጭት እየቀነ ሲሆን ፣ ስርጭቱንም ከ14 አመታት በሁዋላ  ማቆም እንደሚቻል ገልጿል። አሁንም በርካታ ዜጎች መድሃኒት አጥተው በመሰቃየት ላይ መሆናቸውን ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን ገልጿል። በዚህ አመት በአለም ደረጃ 2 ሚሊዮን 300 ሺ ሰዎች ብቻ በኤች አይ ቪ ቫይረስ ተይዘዋል። በአጠቃላይ በአለም ላይ 35 ሚሊዮን የሚሆን ህዝብ በቫይረሱ ተይዟል። ምንጭ፦ ኢሳት

የቡና ምርትና ግብይት የሚቆጣጠር መንግሥታዊ ተቋም ሊቋቋም ነው

Image
- አዲስ የቡና ስትራቴጂ እየተቀረፀ ነው ቡናን ከምርት ጀምሮ እስከ መጨረሻው ድረስ ያለውን የግብይት ሒደት የሚቆጣጠር፣ በቡና ላይ የሚሠሩ የተለያዩ መሥሪያ ቤቶችን በአንድ ላይ ጠቅልሎ የሚሠራ አዲስ መንግሥታዊ ተቋም ሊቋቋም ነው፡፡  ከቡና ምርትና ግብይት ሒደት ጋር ተያይዞ አለ የሚባለውን ችግር ለመቅረፍ ያስችላል የተባለውን አዲሱን መንግሥታዊ ተቋም ለመፍጠር የሚያስችለው ጥናት ተጠናቅቆ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀርቧል፡፡ የተቋሙ አስፈላጊነት ላይ ውሳኔ ከደረሰ በኋላ ካለፈው ዓመት ጀምሮ የተለያዩ ዝግጅቶች ሲካሄዱ መቆየታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ከንግዱ ኅብረተሰብ ጋር ባደረጉት ውይይት፣ በቡና ምርትና ግብይት ዙሪያ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ  ቡናን የሚቆጣጠር መንግሥታዊ ተቋም እንዲቋቋም መወሰኑን መግለጻቸው ይታወሳል፡፡ እንደ ምንጮች ከሆነ እስከዛሬ የነበረውን የቡና ግብይት ሙሉ ለሙሉ የሚለውጥና አዲስ አሠራርን ይፈጥራል የተባለው ይህ ተቋም በሚቀጥለው ዓመት ወደ ሥራ ይገባል፡፡ ተቋሙን ለመፍጠር የተደረገው ጥናት ተጠናቆ ለመንግሥት ከመቅረቡ በፊት የሌሎች የቡና አምራች አገሮች ልምድ እንዲወሰድ መደረጉም ተገልጿል፡፡ በተለይ በቡና ላይ የሚታየውን ረዥም የግብይት ሰንሰለት በመስበር ቀልጣፋ የግብይት ሥርዓት እንዲፈጠር በማድረግ በአገር ውስጥ የቡና ዋጋ እንዳያሻቅብ ለማድረግ ቁጥጥር ያደርጋል፡፡ የኮንትሮባንድ ንግድንም ለመቆጣጠር የሚያስችል አሠራር የሚኖረው ሲሆን፣ የቡና ምርታማነትም እንዲያድግ የሚያስችል አሠራር እንደሚከተልም ተጠቁሟል፡፡ ከዚህ ተቋም መቋቋም ጎን ለጎን አዲስ የቡና ስትራቴጂ በመዘጋጀት ላይ ነው፡፡ ስትራቴጂው በሚቀጥሉት አሥር ዓመታት ኢትዮጵያ ከብራዚል ቀጥላ ሁለተኛዋ የ

ደመወዛችን ሃምሳ ጉዳያችን መቶ!

እነሆ ከመገናኛ ወደ ሲኤምሲ ልንጓዝ ነው። አጀማመራችን በፀጥታ የተጠነሰሰ ነው። የዛሬዎቹ ተሳፋሪዎች ትንፋሽ ያላቸው አይመስሉም። በውጥረት የታፈነው ጎዳና መንገደኛውን መተንፈሻ የነሳው ይመስላል። ጩኸት ኑሮው የሆነው ወያላ ዕድሜው በለቅሶ ተጀምሮ በጩኸት በሚገባደድ ሕዝብ መሀል ያለ ዕረፍት ይጣራል። እንደ ንጋት ጎርናና ድምፁ ሁሉ ጎርበጥባጣ ኑሮው ይለሰልስለት ይመስል እሪ ሲል አይታክትም። ጥሪ በማይፈልገው የትግል ጎዳናችን ላይ ግን የወያላው ልፋት መና የቀረ ይመስላል። ከወዲያ ወዲህ ሲሯሯጥ ከቆየ በኋላ አካባቢውን የሚቀያይረው ሕዝብ ፍልሰቱ መቼም የሚቆም አይመስልም። ሰው የሚደርስበትን ቦታ እያሰበ ስለአዋዋሉ፣ ስለኑሮው፣ ስለቤተሰቡ፣ ስለሥራው እያውጠነጠነ ባላሰበው በሚገኝበት በዚህ ጊዜ፣ የህልማችንና የሩጫችን ውጤት በአብዛኛው አንገት ያስደፋል። ሲዘሉ መሰበር የመንገዱ ህልውና መሠረት ቢሆንም ቅሉ በዚህ በአገራችን የአረማመድ ዘዬ ሳንዘል በተቀመጥንበት የተሰበርን ጥቂት አይደለንም። የዚህ ጎዳና ትርክት ብዙ ነው።  ማጠቃለያ ሐሳብ ይሰጠው ሲባል ግን ቃሏ አንዲት ናት። እሷም ‘ተግዳሮት’ ትባላለች። መውጣትና መውረድ አክርማና ስንደዶ ሆነው ያልቀየሱት ጎዳና በእርግጥ በየትም አገር ታሪክ አይኖርም። ነፃ ብሎ መንገድ፣ እንደ ጨርቅ የሚጠቀለል አልጋ ባልጋ ጎዳና ለሰው ልጅ አይገባውም የተባለ የተፈጥሮ ሕግ ሳይሆን አይቀርም። በዚህ ግጭቱ፣ ተንኮሉ፣ ተግዳሮቱና ሸሩ በማያልቅ የሰው ልጅ ሕይወት ሁሉም እንደራሱ አረማመድ እየተጓዘ እንደ ሕዝብ ደግሞ በጋራ መጓጓዣ እንዝርቱ ይፈትላል። በፈተለው ልክ ሁሉም የድርሻውን ሕይወት እየሸመነና እየለበሰ፣ ለታሪክና ለታዛቢ በሩን ይከፍታል። መንገድ ሁሉን ይዳኛል። የፍትሕ ያለህ ባዩ ወዮታ ግን እያደር በርትቷል። መቼም

የደመወዝ ማስተካከያ ዝርዝር ይዘት በቅርቡ ይፋ ይሆናል ተባለ፤ የደሞወዝ ጭማሪውን ተከትሎ ሃዋሳን ጨምሮ በኣንዳንድ የሲዳማ ከተሞች በሸቀጦች ላይ የዋጋ ጭማሪ ታይቷል

Image
ለመንግስት ሠራተኛው የተደረገው የደመወዝ ማስተካከያ ዝርዝር ይዘት በመጪዎቹ ሁለት ሣምንታት ይፋ እንደምሆን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል። መገናኛ ብዙሃኑ የመንግስት ከፍተኛ የሰራ ሃላፊን ጠቅሰው እንደዘጋቡት፤ መንግስት የሲቪል ሠራተኛውን ኑሮ ለማሻሻል ከወሰዳቸው እርምጃዎች መካከል የደመወዝ ማስተካከያ በዋነኝነት ተጠቃሽ መሆኑን ነው።  በአሁኑ ወቅት የደመወዝ ማስተካከያው ዝርዝር ሥራ በመከናወን ላይ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፤ በመጪዎቹ ሁለት ሳምንታት ውስጥ ይፋ እንደሚሆን ገልጸዋል። አስፈላጊ ሥራዎች ከተጠናቀቁ የተደረገው የደመወዝ ማስተካከያ ከሐምሌ ወር 2006 ዓ . ም ጀምሮ ለሠራተኛው የሚከፈል መሆኑን ታውቋል ። በተመሳሳይም የመንግስት ሠራተኛውን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ እየተገነቡ ካሉት የጋራ መኖሪያ ቤቶች የ 20 በመቶ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ እንደሚገኝ የመንግስት መገናኛ ብዙሃኑ አመልክተዋል። ኣክለውም የሠራተኛውን የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍም በፌዴራል ደረጃ ለዚሁ አገልግሎት የሚውሉ ተሽከርካሪዎች እየተመረቱ መሆኑንና በቅርቡ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩ አስረድተዋል። አንዳንድ ነጋዴዎች የደመወዝ ማስተካከያውን ተከትሎ በመሰረታዊ ሸቀጦች ላይ የዋጋ ጭማሪ እንዳያደርጉ መንግስት የተለያዩ የቁጥጥር ሥራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል ብለዋል። በሌላ በኩል መሰረታዊ የሚባሉ ሸቀጦችን በ " አለ በጅምላ " ድርጅት በኩል በማቅረብ ኅብረተሰቡ ሸቀጦችን ፍትሃዊ በሆነ ዋጋ እንዲያገኝ የሚያስችል አሰራር መዘርጋቱን ጠቅሰዋል። የደመወዝ ማስተካከያው ኢኮኖሚው ተረጋግቶ መቀጠል በሚችልበትና የኑሮ ውድነትን በማያባብስ መልኩ ተጠንቶ ተግባራዊ የሚደረግ እንደሆነም ተ ገልጸዋል። ባለፈው ሰኔ 16 ቀ

High court ruling says UK should respect human rights in Ethiopia

LONDON, July 15 (RIA Novosti) – The UK High Court’s Monday ruling allowing to review the UK aid agency’s compliance with its own human rights policies in Ethiopia signals the need for the British government and other donors to uphold their commitments, Human Rights Watch (HRW) said in a press release. In its July 14 ruling, the High Court said that allegations that the UK Department for International Development (DFID) has failed to adequately assess evidence of human rights violations in the African country deserve a full judicial review. “The UK High Court ruling is just a first step, but it should be a wake-up call for the government and other donors that they need rigorous monitoring to make sure their development programs are upholding their commitments to human rights,” Leslie Lefkow, HRW deputy Africa director, said. The primary human rights violations took place within the “villagization” program, a compulsory resettlement of people into designated villages, which was carried