የዲያስፖራውን ሙሉ መረጃ አጠናቅሮ መያዝ የሚያስችል አሰራር መዘርጋት ይገባል-ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
አዲስ አበባ ሰኔ 23/2006 ዲያስፖራው በአገሩ የልማት እንቅስቃሴ ላይ በስፋት እንዲሳተፍና በሚኖርበት አገር ሁሉ መብቱን ማስከበር እንዲችል የዲያስፖራውን ሙሉ መረጃ አጠናቅሮ መያዝ የሚያስችል አሰራር መዘርጋት እንዳለበት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከአለም አቀፍ የስደተኞች ተቋም ጋር በመተባበር ከ20 በላይ ከሚሆኑ ኤምባሲዎች ለተውጣጡ የኢትዮጵያ አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች "ዲያስፖራውን ማወቅ" በሚል ርዕስ በአዲስ አበባ ስልጠና እየሰጠ ነው። በዚሁ ወቅት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ደዋኖ ከድር እንደተናገሩት የዲያስፖራውን ሙሉ መረጃ በማወቅ በአገሩ ልማት ላይ በስፋት እንዲሳተፍ ማድረግ ይገባል። ከአሁን በፊት የነበረው አሰራር የዲያስፖራውን መገኛ ቦታ ብቻ በማወቅ ላይ የተመሰረተ እንደነበር ጠቁመዋል፡፡ አቶ ደዋኖ እንዳሉት ዲያስፖራውን ከአገሩ ልማት ጋር ማቆራኘት እንዲቻል የአሁኑ ስልጠና ጥሩ ተሞክሮ ያላቸው አገሮችን ልምድ ያካተተ እንዲሆን ተደርጓል። ለአሁኑ ስልጠና እንዲሳተፉ የተጋበዙ ዲፕሎማቶች ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በስፋት ከሚገኙበት አገራት እንደመሆኑ መጠን ስልጠናውን ጨርሰው ወደመጡባቸው አካባቢዎች ሲመለሱ ዲያስፖራውን በማስተሳሰሩ ረገድ ብዙ ስራ ይጠብቃቸዋል ብለዋል። የአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት ተልዕኮ የኢትዮጵያ ኃላፊ ሚስተር ጆሲያህ ኦጊና እንዳሉት ድርጅቱ የምሁራንን ፍልሰት ለመግታትና የስደተኞችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከመንግስት ጎን ይሰለፋል። ከውጭ ለሚመለሱ ኢትዮጵያውያንም አጫጭር ስልጠናዎችን በመስጠት በዘላቂነት ራሳቸውን እንዲችሉ በማገዝና ጊዜያዊ የቁሳቁስ አቅርቦት በማድረግ ድጋፍ እንደሚያደርግም ገልፀዋል። ዲያስፖራው ለአገሩ ልማት