Posts

Speech Recognition System: Speaker Dependent Recognizer for Sidama Language

Image
by  Abdella Kemal Mohammed   (Author) Speech recognition systems have been applicable in wide areas as various speech recognition methodologies, techniques and tools have been developed and implemented to generate a natural and intelligible speech. In this regard, this work attempts the possibility of developing a prototype speech recognition system for Sidama language using Hidden Marcov Model. The study has conducted extensive study on the language features, the components, speech recognition tools; the techniques used in speech recognition design, and identified those component that are dependent on the characteristics of language. Finally this work has showed a working prototype speech recognizer for the language, tested the performance of the system and compared its accuracy, and recommended measures for similar researches and projects. This work, therefore, will be useful to researchers, Speech application developers, Educators and other individuals or institutions working on

የቡና ንግድ ቀይ መብራት በርቶበታል

Image
ሚኒስትሮች ተሰብስበዋል፡፡ የሚኒስትሮቹ ጠቅላይ አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ስብሰባውን ይመራሉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ሚኒስትሮችና ከዚያ በታች በተዋረድ የሥልጣን ዕርከን ላይ የሚገኙ 37 ሹማምንት ለስብሰባው ሲጠበቁ 25ቱ ተገኝተዋል፡፡ በሦስት ሚኒስቴሮች የኤክስፖርት አፈጻጸም ላይ በብሔራዊ ኤክስፖርት አስተባባሪውና የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ ሚኒስትር በአቶ አርከበ ዕቁባይ (የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ይዘዋል) ጠሪነት ለአምስት ሰዓት የዘለቀ ስብሰባ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት ተካሂዷል፡፡ ስብሰባው ከጥቂት ወራት በፊት የተካሄደ ነው፡፡ ከመነጋገሪያ ነጥቦቹ አንዱ የሆነው የንግድ ሚኒስቴር የኤክስፖርት አፈጻጸም ነበር፡፡ ከዚህም ውስጥ ቡና ላይ ትኩረት አድርጎ፣ ሌሎች የግብርና ምርቶችንም ተመልክቷል፡፡ ‹‹በንግድ ሚኒስቴር ክትትል የሚደረግባቸው የግብርና ምርቶች የኤክስፖርት ዕቅድ አፈጻጸም በተያዘው ዕቅድ መሠረት ለማሳካት የተከተልነው የአሠራር ሥርዓትና የማኔጅመንት አመራር ለውጥ ያላመጣው በምን ምክንያትን እንደሆነ አጽንኦት ተሰጥቶት ቢታይ፤›› የሚል መነሻ ያሰፈረው የመወያያ አጀንዳ፣ ከዚህ ቀደም በኤክስፖርት ብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴው በኩል የተሰጡ ማሳሰቢያዎችና የሥራ መመርያዎች ብዙም ለውጥ እንዳላመጡ ይገልጻል፡፡  ከቀረቡት ዝርዝር ነጥቦች መካከል ለአብነት መጥቀስ ቢያስፈልግ፣ ከዚህ ቀደም ኮሚቴው የኢትጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን፣ የንግድ ሚኒስቴር፣ የግብርና ሚኒስቴርና የፀጥታ አካላት በጋራ ተቀናጅተው በተለይ የቡና ኤክስፖርት ዕቅድ አፈጻጸምን ለማቀላጠፍ ይቻል ዘንድ፣ ቡና በብዛት ወደ ምርት ገበያ እንዲገባ በማድረግ የአቅርቦት መጠኑ እንዲጨምር የሚል መመርያ ሰጥቶ እንደነበር ያስታውሳል፡፡ ሆኖም ግን የተለየ ለውጥ አለመምጣቱን

በግብርና ምርቶች ላይ እሴት ጨምሮ መላክ የሚያስችል የተቀናጀ የግብርና ኢንዱሰትሪ ፓርኮች ሊመሰረቱ ነው

Image
 በግብርና ምርቶች ላይ እሴት ጨምሮ መላክ የሚያስችል "የተቀናጁ የግብርና ኢንዱሰትሪ ፓርኮች" ለመመስረት የሚያስችል ጥናት በማካሄድ ላይ እንደሆነ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለፀ። ሚኒስትር ዲኤታው ዶክተር መብራቱ መለስ የግብርና ምርቶችን እሴት ጨምሮ ወደ ውጭ ገበያ ማቅረብ እንደሚያስፈልግና ለዚህም እሴት ጨምረው መላክ የሚያስችሉ ኩባንያዎች ማቋቋም መሰረታዊ ነገር መሆኑን ተናግረዋል። ሚኒስትሩ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደተናገሩት ፓርኮቹ የግብርና ምርት በብዛት የሚገኝባቸው ቦታዎችን በጥናት በመለየት የሚከናወኑ ናቸው ። የግብርና ምርቶችን እሴት ጨምሮ ለአለም ገበያ ባለማቅረብ የተነሳ አገሪቱ ከፍተኛ የሆነ የውጭ ምንዛሬ እያጣች ነው ያሉት ሚኒስትሩ በቀጣይ ግን ፓርኮችን ገንብቶ ኢንዱስትሪዎች በማቋቋም  ከፍተቱን ለሞምላት እንደሚጥሩ ተናግረዋል። የሚቋቋሙት ኢንዱሰትሪዎች የገበሬውን የግብርና ምርት በስፋት መጠቀም መቻላቸው አርሶ አደሩ ዘላቂና አስተማማኝ የሆነ የገቢ ምንጭ እንዲኖረው እንደሚያደርግና የአርሶ አደሩን ህይወት መቀየር እንደሚችሉ አስረድተዋል። በሚቋቋሙት ኢንዱስትሪዎችም ከፍተኛ የስራ እድልና የኢንተርፕራይዞች መፈጠር እንደሚያስፋፋ ጨምረው ተናግረዋል። ሚኒሰትሩ እንደተናገሩት "የተቀናጁ የግብርና ኢንዱሰትሪ ፓርኮች"  በስኳር ማምረቻ አካባቢዎች፣ የፍራፍሬና የአትከልት ምርት በስፋት በሚኖርባቸው፣ የሰሊጥ እንዲሁም የቡና ምርቶች በሚበዙባቸው ቦታዎች ላይ ይጀመራሉ። በሚቀጥለው የበጀት አመት በሚጠናቀቀው የእድገትና የትራንስፎርሜሺን እቅድ ላይ መጀመር እንዲቻል የጥናት ስራው በመፋጠን ላይ ይገኛል ያሉት ሚኒሰትሩ በሚቀጥለው የእቅድ ዘመን ግን በስፋት በመላው አገሪቱ እንደሚተገበሩ አረጋግጠዋል።

ሁለት የሃዋሳ ከተማ ተጫዋቾችን የያዘው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከቱርክ አቻው ጋር የወዳጅነት ግጥሚያ እንዲያደርግ መታቀዱን ተሰማ

Image
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከቱርክ አቻው ጋር የወዳጅነት ግጥሚያ እንዲያደርግ መታቀዱን አሰልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ አስታወቁ። አሰልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ በዛሬው እለት ስለቡድኑ አጠቃላይ እንቅስቃሴ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው ይህን ያሉት። አሰልጣኙ መግለጫ ከሰጡባቸው ዋነኛ ሀሳቦች መካከል ፥ የመረጧቸው 38 ተጨዋቾች የዝግጅት ሂደት ምን ይመስላል የሚለው ይጠቀሳል። በተጨማሪም ዋነኛ አላማቸው በ2015 በሞሮኮው የአፍሪካ ዋንጫ መሳተፍ እንደሆነ በመግለፅ፥ አልጄሪያን ከመግጠማቸው በፊትም የወዳጅነት ጨዋታ ወደ ቱርክ አቅንተው ለመጫወት እንደታሰበ አስረድተዋል። አብዛኛውን ተጨዋቾች በደንብ ስለሚያውቋቸው ም/አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ እና ዳንኤል  ፀሀዬን እኔው እራሴ ምክትሎቼ አድርጌ መርጫቸዋለው ብለዋል በመግለጫቸው ላይ። ከ20 አመት በታች የሚገኙ ተጨዋቾች የሚሳተፉበት  ክለቦች ሊግ በአገር ውስጥ ሊኖር እንደሚገባ እና  ተተኪዎችን ለማፍራት ከ14  ፣ 17 እና ከ20 አመት በታች ተጨዋቾች ላይ መሰራት እንደሚኖርበትም ነው የገለፁት። ዜናው የፋና ነው

በስነ ምግባር የታነጸ ዜጋ በመፍጠር ፆታዊ ጥቃትን ለመከላከል የሃይማኖት ተቋማት መከሩ

Image
በስነ ምግባር የታነጸ ዜጋ በመፍጠር ፆታዊ ጥቃትን ለመከላከል በሃይማኖት ተቋማት ሚና ላይ የተዘጋጀ ክልል አቀፍ የሃይማኖት ተቋም የሁለት ቀን የምክክር ጉባኤ የአቋም መግለጫ በማውጣት ትናንት ማምሻውን ተጠናቋል፡፡ ከተሳታፊዎቹ መከካል የደቡብ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሰብሳቢ የሲዳማ፣ የቡርጂና ጌድኦ ሀገር ስብከት ስራ አስኪያጅ ሊቀ ጉባኤ አባ ሀብተማርያም ገብረመስቀል እንደተናገሩት ያለስነ ምግባር የሚካሄድ ማንኛውም ስራ ሂደቱ አስቸጋሪ ውጤቱም አስከፊ በመሆኑ በስነ ምግባር የተገነባ ዜጋ ለመፍጠር ከሃይማኖት ተቋም አባቶች ብዙ ይጠበቃል፡፡ የአከባቢን ስነ ምህዳር በመጠበቅ ለሰው ልጆች ምቹና ተስማሚ የመኖሪያ ስፍራ ለመፍጠር፣ልማትን ከሙስና ማጽዳት፣ ስራን ከስህተትና ከጉዳት ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ሁሉ የሃይማኖት አባቶችና ተከታዮቻቸው የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ሊያደርጉ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡ ጉባኤው በስነ ምግባር የታነፁ ዜጎችን ለማፍራትና በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ፆታዊ ጥቃት እንዲሁም ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለማስወገድ ሁሉም የሃይማኖት ተቋማት ሚና ምን መሆን እንዳለበት ግልፅ አቅጣጫ ያሳየ ነው ብለዋል፡፡ የደቡብ ክልል የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዜዳንትና የሃይማኖት ተቋማት ምክትል ሰብሳቢ ሀጂ ሚፍታህ ሰኢድ በመከባበርና በሰላም አብሮ በመኖር የሚያምኑ፣በልማትና ዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ሂደት ሀገራዊ ሃላፊነት መሸከም የሚችሉ ዜጎችን የማፍራት ጉዳይ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል፡፡ ጠንካራ የስራ ባህል ያላቸው፣ በራሳቸው የሚተማመኑና ከማንኛውም ጥገኛ ልማድ ነፃ የሆኑ ፣ ኃላቀር አስተሳሰቦችን በመዋጋት እውቀትን የመሻት ዝንባሌ የተላበሱ ወጣቶችን ለማፍራት ከሃይማኖት ተቋማት ብዙ የሚጠበቅ በመሆኑ ጠንክረው