የደመወዝ ጭማሪው የዋጋ ንረት እንደማያስከትል ግልጽ መደረግ አለበት!
የዋጋ ንረትን በተመለከተ ሰሞኑን ሁለት ተቀራራቢ የሆኑ ክስተቶች ተሰምተዋል፡፡ የመጀመሪያው የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ባለሥልጣን የግንቦት ወር 2006 ዓ.ም. የዋጋ ንረትን በማስመልከት ያወጣው ሪፖርት ሲሆን፣ ሁለተኛው መንግሥት የዋጋ ንረትን በማይቀሰቅስ ሁኔታ ለመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ ጭማሪ ለማድረግ መወሰኑ ነው፡፡ ይህ ውሳኔ ለሠራተኛው ሕዝብ መልካም ብሥራት ነው፡፡ ነገር ግን የተጠና መሆን አለበት፡፡ የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ባለሥልጣን ሪፖርት እንደሚያሳየው በግንቦት ወር የአገሪቱ አጠቃላይ የዋጋ ንረት 8.70 በመቶ በማስመዝገብ፣ በመላ አገሪቱ ባለፉት 15 ወራት የዋጋ ንረቱ በነጠላ አኃዝ እንደቀጠለ ነው፡፡ የዋጋ ንረቱ እ.ኤ.አ. ከማርች 2013 ጀምሮ በነጠላ አኃዝ መቀጠሉን ለመንግሥት እንደ ስኬት እንደሚታይ ሪፖርቱ ያብራራል፡፡ የዋጋ ንረቱ በነጠላ አኃዝ መቀጠሉ አዎንታዊ ገጽታ ነው፡፡ ይሁንና መንግሥት ከሐምሌ ወር ጀምሮ ለመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ እጨምራለሁ ሲል ያቀረበው ታሳቢ ጭማሪው የዋጋ ንረት የማያስከትል መሆኑን ነው፡፡ ጥያቄ የሚነሳውም እዚህ ላይ ነው፡፡ የደመወዝ ጭማሪ ሲደረግ የዋጋ ንረት እንደማይባባስ የሚደረገው ምን ዓይነት ዕርምጃዎችን ወይም መለኪያዎችን በማሰብ ነው? ለመንግሥት ሠራተኞች የሚደረገው የደመወዝ ጭማሪ ኢኮኖሚው ተረጋግቶ መቀጠል በሚችልበት ሁኔታ ተጠንቶ ተግባራዊ እንደሚደረግ መንግሥት መወሰኑ ተገልጿል፡፡ ይህ እንዴት ተግባራዊ ይሆናል የሚለው ጥያቄ ደግሞ መነሳቱ የግድ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም በአገሪቱ ተከስቶ የነበረው አጠቃላይ የዋጋ ንረት እስከ 40 በመቶ ደርሶ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን፣ የኅብረተሰቡን ኑሮ በምን ያህል ደረጃ አመሰቃቅሎት እንደነበርም አይዘነጋም፡፡ የዋጋ ንረቱ አሁን በነጠላ አኃዝ ላይ