የሃዋሳ ከተማ የወደፊት እጣፋንታ ከወዲሁ ለመገመት እንዲያስችሎት
... በአገሪቱ ያልተማከለና የተመጣጠነ የከተሞች ዕድገትን ለማረጋገጥ ዘጠኝ የከተማ ዕድገት መሰላሎችና ዞኖች በአዲስ አበባ፣ በመቐለ፣ በባህር ዳር፣ በነቀምቴ፣ በወልዲያ/ኰምቦልቻ፣ በጅማ፣ በድሬዳዋ፣ በሐዋሳና በጐዴ እንደሚፈጠሩና የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ልዩ ዞን ስኬት ለእነዚህ ስምንት ከተሞች እንደ መልካም ተሞክሮም እንደሚያገለግል መረጃው ያመለክታል፡፡... የሃዋሳ ከተማ የወደፊት እጣፋንታ ከወዲሁ ለመገመት እንዲያስችሎት የሚከተለውን ጽሑፍ ያንቡ፦ የተቀናጀው ማስተር ፕላን በልማትና በፖለቲካዊ ጥያቄዎች መካከል ባለፈው ሳምንት ግንቦት 30 ቀን 2006 ዓ.ም. የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፌዴራሊዝም ጥናት ማዕከልና የደቡብ አፍሪካው ዌስተርን ኬፕ ዩኒቨርሲቲ በመተባበር ያዘጋጁት ሴሚናር በከተሞች አስተዳደር ላይ ያተኮረ ነበር፡፡ የሴሚናሩ ተሳታፊዎች ከምሁራን፣ ከመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ ከኦሮሚያ፣ ከአዲስ አበባና ከፌዴራል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ ከፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት፣ ከተለያዩ የጥናትና ምርምር ተቋማት ተወካዮች፣ ከፌዴራሊዝም ተማሪዎችና ከሌሎች የሚመለከታቸው አካላት የተውጣጡ ነበሩ፡፡ ከላይ የተገለጸው ሴሚናር ከመካሄዱ ከሁለት ቀናት በፊት የአዲስ አበባና በአዲስ አበባ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ማስተር ፕላን ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ለውጭ ሚዲያዎችና በእንግሊዝኛ ቋንቋ ለሚሠሩ ሚዲያዎች በማስተር ፕላኑ የዝግጅት ሒደት ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጠ ሲሆን፣ በጽሕፈት ቤቱ ዳይሬክተር በአቶ ማቴዎስ አስፋው የተመራው ቡድን አዲስ አበባንና ኦሮሚያን የወከሉ ኃላፊዎችን አካቶ ለተለያዩ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ሞክሯል፡፡ በሁለቱ ቀናት ዝግጅቶች ትኩረት የሳበው አጀንዳ የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ክልል ግንኙነት ነው፡