Posts

ችግር ለሚፈጥሩ ቡና ላኪዎች የሥነ ምግባር ደንብ ተዘጋጀ

Image
ችግር የሚፈጥሩ የቡና ነጋዴዎች አደብ እንዲገዙ ያደርጋል የተባለ የሥነ ምግባር ደንብ ተዘጋጀ፡፡ ደንቡን ያዘጋጀው የኢትዮጵያ ኮፊ ኤክስፖርተርስ አሶሴሽን ሲሆን፣ ማኅበሩ በዚህ ሳምንት በጠራው ጠቅላላ ጉባዔ ደንቡን ያፀድቀዋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ምንጮች ገልጸዋል፡፡  የተዘጋጀው የሥነ ምግባር ደንብ በተለይ ከውጭ አገር ገዥዎች ጋር የገቡትን የቡና ሽያጭ ስምምነት ውል የማያከብሩ ነጋዴዎች በአገሪቱ ቀጣይ የቡና ግብይት ላይ ሳንካ የሚፈጥሩ የቡና ኤክስፖርተሮችን ከጨዋታ ውጭ እንዲሆኑ ማድረግ የሚያስችል ዕርምጃ ለመውሰድ ከማስቻሉም በተጨማሪ፣ የሥነ ምግባር ችግር አለባቸው ተብለው የተፈረጁ ኤክስፖርተሮችን ጥቁር መዝገብ ውስጥ ያሳፍራል ተብሏል፡፡ የኢትዮጵያ ቡና ላኪዎች ማኅበር ከሌሎች አገሮች የቡና ላኪ ማኅበራት፣ በአፍሪካና በዓለም አቀፍ ደረጃ ከተቋቋሙ የቡና ማኅበራት ጋር ግንኙነት ያለው በመሆኑ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ጥቁር መዝገብ ውስጥ የገባ የቡና ኤክስፖርተር እነዚህ ተቋማት በሙሉ እንዲያውቁት ይደረጋል ተብሏል፡፡  ይህም አጥፊ ከተባለው ኤክስፖርተር ጋር ቀጣይ ግብይት ማድረግ አደጋ እንደሚመጣ ጠቋሚ በመሆኑ የተፈረጀው ላኪ ችግር ውስጥ ይወድቃል ተብሏል፡፡ ማኅበሩ ጥቁር መዝገብ ውስጥ ያሰፈረው ቡና ላኪ በመንግሥት በኩልም ምርመራ ተካሂዶበት ለቅጣት እንደሚዳረግም ተገልጿል፡፡ በማኅበሩ የተዘጋጀው የሥነ ምግባር ደንብ የንግድ ሚኒስቴር፣ ግብርና ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ምርት ገበያን ጨምሮ የተለያዩ የሚመለከታቸው አካላት አስተያየት እንዲሰጡበት ተደርጎ፣ የሰጧቸው አስተያየቶችም ተካተው የመጨረሻው ረቂቅ ተዘጋጅቷል፡፡  ነገር ግን የሥነ ምግባር ደንቡን በጥርጣሬ የሚመለከቱ ኤክስፖርተሮችም አሉ፡፡ እነዚህ ኤክስፖርተሮች እንደሚሉት፣ በሥነ ምግባር ደንቡ

የኮሪያ መንግሥት ለሞጆ-ሐዋሳ የፍጥነት መንገድ የፈቀደው ብድር ለፓርላማ ቀረበ

ከሞጆ-ሐዋሳ የመጀመሪያ ዙር የፍጥነት መንገድ ግንባታ የኮሪያ መንግሥት ኤግዚም ባንክ የፈቀደው 100 ሚሊዮን ዶላር ብድር ለፓርላማ ቀረበ፡፡ የሞጆ-ሐዋሳ መንገድ 201 ኪሎ ሜትር ርዝመት ሲኖረው፣ ግንባታው በሁለት ዙር ተከፍሎ የሚገነባ ነው፡፡ የጀመሪያው ዙር ግንባታ ከሞጆ-ዝዋይ በራሱ በሁለት ተከፍሎ የሚገነባ መሆኑን የብድር ማፅደቂያ አዋጁ አባሪ ሰነድ ያብራራል፡፡ የመጀመርያው ዙር የመጀመርያ ምዕራፍ ከሞጆ-መቂ ሲሆን፣ ለዚህ ግንባታ ማስፈጸሚያ የሚውል 128 ሚሊዮን 460 ሺሕ ዶላር በዚህ ዓመት ከአፍሪካ ልማት ባንክ መገኘቱን ሰነዱ ያብራራል፡፡ ለቀሪው የመቂ-ዝዋይ መንገድ ግንባታ ደግሞ የኮሪያ ኤክስፖርት ኢምፖርት (ኤግዚም) ባንክ 100 ሚሊዮን ዶላር መፈረሙን የአዋጁ አባሪ ይገልጻል፡፡ ከሞጆ-ሐዋሳ ድረስ የሚገነባው የፍጥነት መንገድ በአንድ ጊዜ አራት ተሽከርካሪዎችን እንዲያስተናግድ ይፈለጋል፡፡ አጠቃላይ ወጪውም 349 ሚሊዮን 480 ሺሕ ዶላር መሆኑን ሰነዱ ይገልጻል፡፡  ከኮሪያ መንግሥት የተገኘው 100 ሚሊዮን ዶላር የ15 ዓመት የችሮታ ጊዜን ጨምሮ በ40 ዓመት ጊዜ ውስጥ ተከፍሎ የሚጠናቀቅ ነው፡፡ ለፕሮጀክቱ ትግበራ ባንኩ በሚፈጽመው ክፍያ ላይ 0.1 በመቶ የአገልግሎት ክፍያ ከብድሩ ገንዘብ ላይ ተቀንሶ እንደሚከፈል፣ ጥቅም ላይ ባልዋለውና ባልተከፈለው የብድር ገንዘብ ላይ ደግሞ 0.01 በመቶ ወለድ እንደሚታሰብበት ረቂቅ ማፅደቂያ አዋጁ ይገልጻል፡፡ የብድር ስምምነቱ እስከዛሬ ከነበሩት የብድር ዓይነቶች ጋር ሲነፃፀር የ55 ዓመት መሆኑ፣ የአገልግሎት ክፍያውና ወለዱ በጣም ዝቅተኛ መሆኑ የፓርላማው አባላትን አስደንቋል፡፡ ‹‹የኮሪያ ኤግዚም ባንክ ብድር ሳይሆን ስጦታ ነው የሰጠው፤›› ሲሉ የምክር ቤቱ ዶ/ር አድሃና ኃይሌ አድንቀውታ

የኢትዮጵያ ሴቶች እግር ኳስ ፕሪሚየር ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ነገ በሀዋሳ ከተማ ይጀመራል

Image
የሲዳማ ቡና የሴቶች ብድን ከሰኔ 8 እስከ ሰኔ 22 ቀን 2006 ዓ.ም በሚካሄደው በዚህ ጨዋታ ተወዳዳሪ ክለቦች፣ የውድድር ባለሙያዎች ደጋፊዎችና ሌሎች እንግዶች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። የኢትዮጵያ ዜና ኣገልግሎት እንደዘጋበው፤ ለፍጻሜ ውድድር በወጣው ደንብ መሰረት ሀዋሳ ከነማና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የየምደቡ አሸናፊ በመሆናቸው የምድብ አንድና ሁለት አባትነት ደረጃ ሲያገኙ የቀሩት ክለቦች ግን በደረጃቸው መሰረት ድልድል ይደረግላቸዋል። ከ2ኛ እስከ 4ኛ ደረጃ ባለው የምድብ ተራ ቁጥር ያሉት ደግሞ በዕጣ የሚወሰኑ ይሆናል። ከየምደቡ አንደኛና ሁለተኛ የሚወጡት ቡድኖች ለጥሎ ማለፍ ውደድር የሚያልፉ ሲሆን ተሸናፊዎች ለሶስተኛ ደረጃ፣ አሸናፊዎች ደግሞ ለዋንጫ ፍልሚያ የሚያደርጉ ይሆናል። ቀደም ሲል ባስመዘገቡት ውጤት መሰረት ከማዕከላዊ ሰሜን ዞን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ደደቢት፣ ቅዱስ ጊዮርጊስና ዳሽን ቢራ ሲገኙ ከደቡብ ምስራቅ ዞን ደግሞ ሀዋሳ ከነማ፣ ሲዳማ ቡና፣ አርባ ምንጭና ድሬድዋ ከተማ ለፍፃሜ ውድድር ያለፉ ናቸው። ሀዋሳ ጨዋታውን ለማካሄድ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጓንና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽንም ውድድሩ የተሳካና ያማረ እንዲሆን አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማደረጉን ገልጿል። ፈዴሬሽኑ ለሸናፊዎቹ የዋንጫና የሜዳሊያ ሽልማት እንዲሁም ለኮከብ ተጫዋቾች፣ ለአሰልጣኞችና ለዳኞች የማበረታቻ ሽልማት እንደሚያደርግ ማሰታወቁን ኢዜኣ ዘግቧል።

የመንግስት መገናኛ ብዙሃን የሲኣን/ መድረክ ሰላማዊ ሰልፍ ተሳታፊዎችን ቁጥር ኣሳንሰው ዘገቡ

Image
ከሰላማዊ ሰልፈኞቹ መካከል የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን በዛሬው እለት በሃዋሳ ከተማ የተካሄደውን የሲኣን/ መድረክ ሰላማዊ ሰልፍ ተሳታፊዎችን ቁጥር በእጅጉ ኣሳንሰው መዘገባቸው ተሰማ። በወቅታዊው የኣገሪቱ የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ድምጻቸውን ለማሰማት ወደ ኣደባባይ በርካታ ቁጥር ያለው ህዝብ የተመመ ሲሆን፤ በሰላማዊ ሰልፉ ላይ በሺዎች የምቆጠሩ ሰዎች መገኘታቸውን ከሲኣን የተገኘው መረጃ ያመክታል። ሆኖም የመንግስት መገናኛ ብዙሃን  ይህንን ብዛት የለውን ሰላማዊ ሰልፈኛን ቁጥር በማሳነሰ የሰላማዊ ሰልፈኛውን ቁጥር ወደ 200 ኣውርደው መዘገባቸው ታውቋል። ከመገናኛ ብዙሃኑ ዘጋባ መካከል የሚከተለውን ለኣብነት ኣቅርበነዋል፦  መድረክ በሀዋሳ ከተማ የተቃውሞ ሰልፍ አካሄደ ሀዋሳ ሰኔ 07/2006 የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ዛሬ በሀዋሳ ከተማ የተቃውሞ ሰልፍ አካሄደ፡፡ መድረክ በዚሁ ሰልፍ ላይ የተለያዩ የተቃውሞ መፈክሮችን አሰምቷል፡፡ የመድረክ ዋና ጸሐፊ አቶ ገብሩ ገብረማርያም በሰልፉ ላይ እንዳሉት ኢህአዴግ የህግ የበላይነትን በማክበርና በማረጋገጥ ነጻ ፍትሐዊ ዴሞክራሲያዊና ታዓማኒነት ያለው ገለልተኛ የምርጫ አስተዳደር እውን እንዲሆን ማድረግ አለበት፡፡ ዜጎች ያለ ፖለቲካዊ ወገንተኝነት ከሀገራቸው ልማትና እድገት ውጤቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ እንጠይቃለን ብለዋል። መድረክ የሀገሪቱን ወቅታዊና መሰረታዊ ችግሮች መፍቻ አቅጣጫ ነው ያለውን ማንፌስቶ በህዝቡ ድጋፍ ስራ ላይ እንዲውል ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ገልጿል፡፡ በሰልፉ ላይ የተሳተፉት ሰዎች  ከ200 በላይ እንደሚገመቱ በስፍራው የነበሩ የአይን እማኞች ገልጸዋል፡፡ ሰልፉም በሰላም መጠናቀቁን ጸጥታ አንዳንድ የጸጥታ አስከባሪዎች ተናግረዋል፡፡

ሲኣን/ መድረክ የጠራው ታላቅ ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ በሃዋሳ ከተማ ተካሄደ

Image
ዛሬ ከቀኑ ሶስት ሰዓት ላይ ከወልደኣማኑኤል ዱባሌ ሐውልት የተሰባሰበው ሰላማዊ ሰልፈኛ በኣቶቴ እንድሁም በየሙሉ ወንጌል በተክርስቲያን በኩል ኣድርጎ ወደ መናሃሪያ በመትመም መጨረሻውን ከሃዋሳ መስቀል ኣደባባይ ኣድርጓል። ሪፖተራችን ጥቻ ወራና እንደዘጋበው በሰላማዊ ሰልፉ ላይ በሺዎች የምቆጠሩ ሰዎች የተገኙ ሲሆን የፖለቲካ እና የህሊና እስረኞች ይፈቱ፤ በልማት ስም ህዝብን ማንገላታት ይቁም፤ የኣገራችን የፖለቲካ ችግሮች በድርድር እንጂ በኃይል ኣይፈቱም የምሉ መፎክሮችን ኣስምተዋል። በሰልፉ ላይ ተጋባዥ እንግዶችን እና የመድረክ /   ሲኣን ከፍተኛ ኣመራሮች ተገኝተው ለህዝብ የተለያዩ መልዕክቶችን ያስተላለፉ ሲሆን፤ ሰላማዊ ሰልፉ በፍጽም ሰላማዊ መሆነ ሁኔታ ያለምንም ችግር መጠናቀቁን ሪፖርተራችን ጥቻ ወራና ከሃዋሳ ዘግቧል።