Posts

የኢትዮጵያ ሴቶች እግር ኳስ ፕሪሚየር ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ነገ በሀዋሳ ከተማ ይጀመራል

Image
የሲዳማ ቡና የሴቶች ብድን ከሰኔ 8 እስከ ሰኔ 22 ቀን 2006 ዓ.ም በሚካሄደው በዚህ ጨዋታ ተወዳዳሪ ክለቦች፣ የውድድር ባለሙያዎች ደጋፊዎችና ሌሎች እንግዶች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። የኢትዮጵያ ዜና ኣገልግሎት እንደዘጋበው፤ ለፍጻሜ ውድድር በወጣው ደንብ መሰረት ሀዋሳ ከነማና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የየምደቡ አሸናፊ በመሆናቸው የምድብ አንድና ሁለት አባትነት ደረጃ ሲያገኙ የቀሩት ክለቦች ግን በደረጃቸው መሰረት ድልድል ይደረግላቸዋል። ከ2ኛ እስከ 4ኛ ደረጃ ባለው የምድብ ተራ ቁጥር ያሉት ደግሞ በዕጣ የሚወሰኑ ይሆናል። ከየምደቡ አንደኛና ሁለተኛ የሚወጡት ቡድኖች ለጥሎ ማለፍ ውደድር የሚያልፉ ሲሆን ተሸናፊዎች ለሶስተኛ ደረጃ፣ አሸናፊዎች ደግሞ ለዋንጫ ፍልሚያ የሚያደርጉ ይሆናል። ቀደም ሲል ባስመዘገቡት ውጤት መሰረት ከማዕከላዊ ሰሜን ዞን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ደደቢት፣ ቅዱስ ጊዮርጊስና ዳሽን ቢራ ሲገኙ ከደቡብ ምስራቅ ዞን ደግሞ ሀዋሳ ከነማ፣ ሲዳማ ቡና፣ አርባ ምንጭና ድሬድዋ ከተማ ለፍፃሜ ውድድር ያለፉ ናቸው። ሀዋሳ ጨዋታውን ለማካሄድ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጓንና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽንም ውድድሩ የተሳካና ያማረ እንዲሆን አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማደረጉን ገልጿል። ፈዴሬሽኑ ለሸናፊዎቹ የዋንጫና የሜዳሊያ ሽልማት እንዲሁም ለኮከብ ተጫዋቾች፣ ለአሰልጣኞችና ለዳኞች የማበረታቻ ሽልማት እንደሚያደርግ ማሰታወቁን ኢዜኣ ዘግቧል።

የመንግስት መገናኛ ብዙሃን የሲኣን/ መድረክ ሰላማዊ ሰልፍ ተሳታፊዎችን ቁጥር ኣሳንሰው ዘገቡ

Image
ከሰላማዊ ሰልፈኞቹ መካከል የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን በዛሬው እለት በሃዋሳ ከተማ የተካሄደውን የሲኣን/ መድረክ ሰላማዊ ሰልፍ ተሳታፊዎችን ቁጥር በእጅጉ ኣሳንሰው መዘገባቸው ተሰማ። በወቅታዊው የኣገሪቱ የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ድምጻቸውን ለማሰማት ወደ ኣደባባይ በርካታ ቁጥር ያለው ህዝብ የተመመ ሲሆን፤ በሰላማዊ ሰልፉ ላይ በሺዎች የምቆጠሩ ሰዎች መገኘታቸውን ከሲኣን የተገኘው መረጃ ያመክታል። ሆኖም የመንግስት መገናኛ ብዙሃን  ይህንን ብዛት የለውን ሰላማዊ ሰልፈኛን ቁጥር በማሳነሰ የሰላማዊ ሰልፈኛውን ቁጥር ወደ 200 ኣውርደው መዘገባቸው ታውቋል። ከመገናኛ ብዙሃኑ ዘጋባ መካከል የሚከተለውን ለኣብነት ኣቅርበነዋል፦  መድረክ በሀዋሳ ከተማ የተቃውሞ ሰልፍ አካሄደ ሀዋሳ ሰኔ 07/2006 የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ዛሬ በሀዋሳ ከተማ የተቃውሞ ሰልፍ አካሄደ፡፡ መድረክ በዚሁ ሰልፍ ላይ የተለያዩ የተቃውሞ መፈክሮችን አሰምቷል፡፡ የመድረክ ዋና ጸሐፊ አቶ ገብሩ ገብረማርያም በሰልፉ ላይ እንዳሉት ኢህአዴግ የህግ የበላይነትን በማክበርና በማረጋገጥ ነጻ ፍትሐዊ ዴሞክራሲያዊና ታዓማኒነት ያለው ገለልተኛ የምርጫ አስተዳደር እውን እንዲሆን ማድረግ አለበት፡፡ ዜጎች ያለ ፖለቲካዊ ወገንተኝነት ከሀገራቸው ልማትና እድገት ውጤቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ እንጠይቃለን ብለዋል። መድረክ የሀገሪቱን ወቅታዊና መሰረታዊ ችግሮች መፍቻ አቅጣጫ ነው ያለውን ማንፌስቶ በህዝቡ ድጋፍ ስራ ላይ እንዲውል ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ገልጿል፡፡ በሰልፉ ላይ የተሳተፉት ሰዎች  ከ200 በላይ እንደሚገመቱ በስፍራው የነበሩ የአይን እማኞች ገልጸዋል፡፡ ሰልፉም በሰላም መጠናቀቁን ጸጥታ አንዳንድ የጸጥታ አስከባሪዎች ተናግረዋል፡፡

ሲኣን/ መድረክ የጠራው ታላቅ ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ በሃዋሳ ከተማ ተካሄደ

Image
ዛሬ ከቀኑ ሶስት ሰዓት ላይ ከወልደኣማኑኤል ዱባሌ ሐውልት የተሰባሰበው ሰላማዊ ሰልፈኛ በኣቶቴ እንድሁም በየሙሉ ወንጌል በተክርስቲያን በኩል ኣድርጎ ወደ መናሃሪያ በመትመም መጨረሻውን ከሃዋሳ መስቀል ኣደባባይ ኣድርጓል። ሪፖተራችን ጥቻ ወራና እንደዘጋበው በሰላማዊ ሰልፉ ላይ በሺዎች የምቆጠሩ ሰዎች የተገኙ ሲሆን የፖለቲካ እና የህሊና እስረኞች ይፈቱ፤ በልማት ስም ህዝብን ማንገላታት ይቁም፤ የኣገራችን የፖለቲካ ችግሮች በድርድር እንጂ በኃይል ኣይፈቱም የምሉ መፎክሮችን ኣስምተዋል። በሰልፉ ላይ ተጋባዥ እንግዶችን እና የመድረክ /   ሲኣን ከፍተኛ ኣመራሮች ተገኝተው ለህዝብ የተለያዩ መልዕክቶችን ያስተላለፉ ሲሆን፤ ሰላማዊ ሰልፉ በፍጽም ሰላማዊ መሆነ ሁኔታ ያለምንም ችግር መጠናቀቁን ሪፖርተራችን ጥቻ ወራና ከሃዋሳ ዘግቧል። 

We floated a tender for the construction of the Hawassa and Robe Airports: The Ethiopian Airports Enterprise

Image
Wondeme Teklu, head of the communication affairs office at the Enterprise. Source  addisfortune.net Jinka Airport Given Green Light With Construction Contract The Ethiopian Airports Enterprise is also looking to construct new airports in Hawassa and Robe The Ethiopian Airports Enterprise (EAE) has awarded a 571.7 million Br contract to Afro-Tsion Construction Plc for the construction of the country’s 18th airport at Jinka, 587kms south of Addis Abeba. The Enterprise contracted the project to Afro-Tsion on May 27, 2014, and the contractor was handed over the land, located three kilometres away from Jinka town, on Thursday June 5, 2014. Afro Tsion, a grade one general contractor, was established in 1990 and is engaged in road and bridge construction, infrastructure and real estate development and water works. The contractor has previously worked on the construction of numerous projects, such as Mekele University, Oromia Regional Offices, Gondar University, Assela Mal

ኣሰልጣኝ ባሬቶ ለብሔራዊ ቡድን ሁለት ተጫዋቶችን ከሃዋሳ ከነማ መረጡ

Image
ዜናው የ ኢዜኣ ነው አዲስ አበባ ሰኔ 5/2006 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ በሚቀጥለው ዓመት በሞሮኮ በሚዘጋጀው የአፍሪካ ዋንጫ የሚካፈሉ ተጫዋቾችን መረጡ። አሰልጣኙ ተጫዋቾቹን የመረጡት በውጭ ከሚጫወቱ ኢትዮጵያዊያንና ከሀገር ውስጥ ካሉ ከስምንት የተለያዩ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦችና ከብሄራዊ ሊግ ነው። ከተመረጡት 38 ተጫዋቾች መካከል የቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድን 11 ተጫዋቾችን በማስመረጥ ቀዳሚውን ስፍራ ይዟል። የደደቢት እና የኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለቦች እያንዳንዳቸው ስምንት ተጫዋቾችን፣ ሀዋሳ ከነማ ሁለት፣ እንዲሁም መከላከያ፣ ናሽናል ሲሚንቶ፣ዳሽን ቢራና ሙገር ሲሚንቶ አንድ አንድ ተጫዋቾችን አስመርጠዋል። ከቅዱስ ጊዮርጊስ አሉላ ግርማ፣ አበባው ቡጣቆ፣ ሳላዲን በርጌቾ፣ ቢያድግልኝ ኤልያስ፣ ምንተስኖት አዳነ፣ አንዳርጋቸው ረታ፣ አዳነ ግርማ፣ ምንያህል ተሾመ፣ በሀይሉ አሰፋ/ቱሳ/፣ ዑመድ ኡክሪ እና ፍፁም ገብረማርያም በቡድኑ ተካተዋል። ከደደቢት እግር ኳስ ክለብ  ሲሳይ ባንጫ፣ ታሪኩ ጌትነት፣ ስዩም ተስፋዬ፣ ብርሀኑ ቦጋለ/ፋዲጋ/፣ አክሊሉ አየነው፣ ታደለ መንገሻ፣ ዳዊት ፍቃዱ እና ሽመክት ጉግሳ ተመርጠዋል። ከቡና ስፖርት ክለብ ጀማል ጣሰው፣ ሮቤል ግርማ፣ ቶክ ጀምስ፣ ጋቶች ቻኖም፣ መሱድ መሀመድ፣ ዳዊት እስጢፋኖስ፣ ኤፍሬም አሻሞ እና አስቻለው ግርማ ይገኙበታል ። ከሀዋሳ ከነማ ግርማ በቀለና ታፈሰ ሰለሞን ሲመረጡ ከመከላከያ ሽመልስ ተገኝ፣ ከናሽናል ሲሚንቶ ማታይ ሉል፣ ከሙገር ሲሚንቶ አሰግድ ሽፈራው፣ ከዳሽን ቢራ ደግሞ አስራት መገርሳ ተመርጠዋል። በውጭ አገራት ከሚጫወቱት ኢትዮጵያውያን ተጫዋቾች መካከል ሳላዲን ሰይድ፣ አዲስ ህንጻ፣ ጌታነህ ከበደ፣ ፍቅሩ ተፈራና ሽመልስ በቀለ ይገኙበታል። ለ