ሰንሻይን ሦስተኛውን የማሪዮት ሪዞርት ሆቴል በሐዋሳ ሊገነባ ነው
ሰንሻይን ኢንቨስትመንት ግሩፕ ከማሪዮት ኢንተርናሽናል ጋር በፍራንቻይዝ ስምምነት ሦስተኛውን የማሪዮት ሪዞርት ሆቴል ሐዋሳ ከተማ ውስጥ ሊገነባ ነው፡፡ ምንጭ፦ ethiopianreporter.com አዲስ አበባ ውስጥ በተመሳሳይ መንገድ እየተገነቡ ካሉት ሁለት ባለአምስት ኮከብ ሆቴሎች ውስጥ አንደኛውን ከስድስት ወራት በኋላ እንደሚያስመርቅ ተገለጸ፡፡ በሰንሻይን ኢንቨስትመንት ግሩፕ ሥር ከሚገኙ ኩባንያዎች መካከል አንዱ የሆነው በሰንሻይን ቢዝነስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ሦስተኛውን ማሪዮት ሪዞርት ሆቴል ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ይጠይቃል ተብሏል፡፡ ለሐዋሳ ማሪዮት ሪዞርት ሆቴል የመሠረት ድንጋይ ባለፈው እሑድ ሰኔ 1 ቀን 2006 ዓ.ም. የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደሴ ዳልኬና የሐዋሳ ከንቲባ አቶ ዮናስ ዮሴፍ በተገኙበት ተቀምጧል፡፡ የሐዋሳው ማሪዮት ሪዞርት ሆቴል ስዊት ቪላዎች፣ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ሕንፃዎችና ለሌሎች አገልግሎቶች የሚውሉ ግንባታዎችንም ያካተተ ነው፡፡ የሰንሻይን ኢንቨስትመንት ግሩፕ ፕሬዚዳንት አቶ ሳሙኤል ታፈሰ እንደገለጹት፣ ማርዮት ሪዞርት ሆቴልን በሐዋሳ ለመገንባት የወሰኑት ሐዋሳ ከተማ እያሳየች ካለው ዕድገትና በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት ከተማዋ ልታሳይ የምትችውን የኢንቨስትመንት ዕድሎች ከግምት በማስገባት ነው፡፡ አቶ ሳሙኤል ሐዋሳን ለምን እንደመረጡ በሰጡት ተጨማሪ ማብራሪያ፣ ሐዋሳ ከሌሎች ከተሞች በተሻለ እያደገችና በተደጋጋሚ ምርጥ ከተማ በመባል ተሸላሚ መሆኑዋ አንዱ ምክንያት ነው፡፡ እንዲሁም የከተማዋ ኢንቨስትመንት ዕድገትና በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት ውስጥ ከተማዋን የሚያቋርጠው የፈጣን መንገድ ግንባታ የሚጠናቀቅ መሆኑም ሌላው ምክንያት ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በሐዋሳ ሐይቅ