ማንን እንስማ፦ ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን መቻሏን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ገለጹ፤ የዓለም ምግብ ድርጅት ፋኦ በበኩሉ በኣገሪቷ ከ2 ሚሊዮን በላይ ህዝብ የምግብ እርዳታ ያስፈልገዋል ይላል
የዜናው ምንጭ፦ www.ena.gov.et አዲስ አበባ ግንቦት 20/2006 ኢትዮጵያ በሁለት አሥርት ዓመታት ውስጥ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ በአገር አቀፍ ደረጃ በምግብ ራሷን መቻሏን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም በአዲስ አበባ ስታዲዬም በተከበረው 23ኛው የግንቦት 20 የድል በዓል የማጠቃለያ ሥነ-ሥርዓት ላይ እንደተናገሩት ባለፉት 20 ዓመታት በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትናን የሚያረጋግጡ ፕሮግራሞች ተግባራዊ በመሆናቸው ስኬታማ ውጤት ተመዝግቧል። ከሦስት ዓመታት በፊት የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ አገሮች ባለፉት ስድስት አሥርታት ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በድርቅ ክፉኛ ተመተው እንደነበር አስታውሰው፣ ኢትዮጵያ በዚህ ወቅት ያለአንዳች መሰናክል ችግሩን ማለፏን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ከ23 ዓመታት አገሪቱ ከነበረችበት ከፍተኛ ተመጽዋችነት በመውጣት ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ በዓመት ከ250 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ማምረቷንም አቶ ኃይለማርያም ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት አርሶ አደሩ ከፍተኛ ገቢ ወደሚያስገኙ ምርቶች መሸጋገሩንና በቀጣይም ጠንካራ አገር በቀል ባለሃብቶችን በማፍራት የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪውን ለማሳደግ ጥረት ይደረጋል። ለሁለት አስርት ዓመታት በተካሄደው እልህ አስጨራሽ ትግልም አገሪቱ በዓለም ኅብረተሰብ ዘንድ ትታወቅበት ከነበረው ረሃብና ጉስቁልና በመውጣት ከኦክስፎርድ የእንግሊዝኛ መዝገበ-ቃላትም የረሃብተኝነት ምሳሌ መሆኗ እንዲፋቅ መደረጉን ተናግረዋል።ይህም ለኢትዮጵያውያን ታላቅ እመርታ መሆኑን ጠቅሰዋል። በቀጣይም ኢትዮጵያ ከሚፈለገው ምርታማነትና የብልፅግና ደረጃ ለመድረስና ግሎባላይዜሽን የደቀነውን የውድድር ፈተና በብቃት ለማለፍ ዜጎች ከመንግስት