Posts

ሲአን በሀዋሳ ጽ/ቤቱ ግንቦት 16/1994 ዓ/ም በሎቄ የተጨፈጨፉ ንጹሓን የሲዳማ ልጆች 12ኛ ዓመት የመታሰቢያ ቀን በተለያዩ ዝግጅቾች አክብሮ ውለዋል

Image
ምንጭ፦  Selamu Bulado ሲአን በሀዋሳ ጽ/ቤቱ ግንቦት 16/1994 ዓ/ም በሎቄ የተጨፈጨፉ ንጹሓን የሲዳማ ልጆች 12ኛ ዓመት የመታሰቢያ ቀን በተለያዩ ዝግጅቾች አክብሮ ውለዋል!!!! በዕለቱ የተከናወኑ ድርጊቶች፦ 1ኛ) በተሳታፊዎች የህሊና ፀሎት ተደርጓል፤ 2ኛ) የእንኳን ደህና መጣችሁ እና የመክፈቻ ንግግር በዶ/ር አየለ አሊቶ ተደርጓል፤ 3ኛ) አጠቃላይ ባሁኑ ጊዜ በኢት/ያ ዘጎች ላይ በገዢው ፓርቲ እየተፈፀሙ ያሉ ኢ-ሰብዓዊና ኢ-ዴሞክራሲያ ድርጊቶች ላይ በዕለቱ እንግዳ አቶ ደጉ ደነቦ (ደቡብ የመድረክ ተወካይ) ገለጻ ተደርጓል፤ 4) የግንቦት 16/1994 ዓ/ም የሎቄ ጭፍጨፋ በማስመልከት በአቶ ለገሰ ዋንሳሞ ዋቃዮ በስፋት ገለጻ ተደርጓል፤ 5)የሲአን ትግል አመሠራረት እና ታሪካዊ አመጣጥ ላይ የቀድመው የሲአን መስራች ታጋይና ያሁኑ አመራር በአቶ አርጋታ ጉንሳ (አዱርማን) አጭር ገላጻ ተደርጓል፤ 6)በወቅቱ ሰዎች ስጨፈጨፍ አካል ጉዳተኛ ሆነው በአሁኑ ጊዜ በህይወት ያሉ አንዳንድ ግለሰቦች በገዢው ፓርቲ ላይ ያላቸውን ጥላቻ ለተሳታፊዎች ገልጸዋል፤ 7) በደምሴ ሱካሬ Qaangeemmo'ne በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ግጥም ለተሳታፊዎች ቀርበዋል፤ በመጨረሻም የሲዳማ አርነት ንቅናቄ(ሲአን) ግንቦት 16/1994 ዓ/ም ንጹሓን የሲዳማ ልጆችን በሎቄ ያስጨፈጨፉት ግለሰቦች ለፍርድ የሚቀርቡበት ጊዜ ቅርብ እንደሆነ በአቶ ደሳለኝ መሳ ለተሳታፊዎች ተገልጾ የሻማ ማብራት ስነ-ስርዓት ተካሂዶ ፕሮግራሙ ተጠናቋል።

የኣለታ ላንድ ያስገነባቸውን ሶስት ፋብሪካዎች ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ በተገኙበት ልያስመርቅ መሆኑ ተሰማ

Image
የዜና ምንጭ፡ addisfortune.net Aleta Land Coffee Plc is going to inaugurate its three big factories in the Southern region of Ethiopia, in Hawassa city on Friday, May 24, 2014. According to the statement from Aleta, the inauguration ceremony will be graced by the president of the Federal Democratic Republic of Ethiopia Mulatu Teshome (PhD), the president of Hawassa and other invited ministers and guests. Aleta Land Coffee Plc was established in 2005 with an eight million dollar initial capital. The company is engaged with coffee exporting activities and providing coffee cleaning and warehousing services for other exporters. Currently, Aleta owns eight full-fledged washed-coffee factories in southern Ethiopia, particularly in the Sidamo highland areas.

መድረክ ፓርቲ በአዲስ አበባ የጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደ

Image
ምንጭ፦ ሬዲዮ  ፋና  አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 16 ፣ 2006 ( ኤፍ.ቢ.ሲ. ) የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ፓርቲ ዛሬ በአዲስ አበባ የጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደ። የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎች መነሻቸውን ግንፍሌ ወንዝ ድልድይ ቅዱስ ማቲዎስ አንግሊካን ቤተክርስቲያን አድርገው ፥ በህንድ ኤምባሲ በመታጠፍ አቧሬ አደባባይን ፣ አድዋ ድልድይን በማቋረጥ ማጠቃለያቸውን የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 በተለምዶ ታቦት ማደሪያ እየተባለ በሚጠራው ሜዳ ላይ አድርገዋል። ሰልፈኞቹ ኢህአዴግ ለሰላማዊ ድርድር በሩን ክፍት ያድርግ ፤ በአንድነት ኢትዮጵያን እንገነባለን ፤ የፕሬስ ነፃነት ይከበር ፤ የታሰሩ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች ይፈቱ ፤ መልካም አስተዳደር እውን ይሁን እና የውሃ ፣ መብራትና ስልክ አገልግሎቶች ይስተካከሉ የሚሉ መፈክሮችን አሰምተዋል። በሰልፉ ማጠቃለያ ላይ የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጎይቶም ፀጋዬ እና ዋና ፀሃፊው አቶ ገብሩ ገብረማሪያም ንግግር ያደረጉ ሲሆን ፥ ፓርቲው ባዘጋጃቸው ወቅታዊ ጥያቄዎች ላይ  ኢህአዴግ  ምላሽ እንዲሰጥ ጠይቀዋል። በአዲስ አበባና ፊንፊኔ ዙሪያ የተዘጋጀው የጋራ ማስተር ፕላን ህዝባዊ ውይይት ተደርጎበት በህዝቡ መልካም ፈቃድ ተግባራዊ ሊደረግ ይገባልም ብለዋል።

ክብር ለሎቄ ሰማዕታት!

Image

ጥሬ ቡና ለውጭ ገበያ ማቅረብ እያሽቆለቆለ ነው

Image
- በውጭው ዓለም ከቡና ገለባ ምግብ ሊዘጋጅ ነው ከጥቂት ዓመታት በፊት ከቡና ኤክስፖርት ይገኝ የነበረው ገቢ አንድ ቢሊዮን ዶላርን ለመጠጋት የሚዳዳው ነበር፡፡ ከአራት ዓመት በፊት ከ840 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ከቡና ብቻ ተገኝቶ ነበር፡፡ በዚህ ዓመት ዘጠኝ ወራት ውስጥ መላክ የተቻለው ቡናና የተገኘው የውጭ ምንዛሪ ገቢ መጠን በጣም አነስተኛ ነው፡፡ 67 ሺሕ ቶን ቡና ለውጭ ገበያ ቀረበና ከ222 ሚሊዮን ዶላር ብዙም ፈቅ ያላለ ገቢ ተመዘገበ፡፡  የቡና ሽያጭ ለማሽቆልቆሉ የሚሰጡ በርካታ ምክንያቶች ይጠቅሳሉ፡፡ የዓለም የቡና ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ እየወረደ መምጣቱ ዋናው ምክንያት ተደርጐ ቢቆይም፣ በአገር ውስጥ የቡና ፍጆታ እየጨመረ መምጣት፣ ‹‹የጀበና ቡና›› መሸጫዎች መብዛት፣ ሌሎች ተወዳዳሪ አገሮች ከኢትዮጵያ የተሻለ የቡና መጠን ለውጭ ገበያ ማቅረባቸውና ሌሎችም ይጠቀሳሉ፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሽቆለቆለ የመጣው የቡና ኤክስፖርት ገበያ ከሚጠበቀው በታች ገቢ እያስገኘ ቢሆንም ከግብርና ምርቶች አሁንም በቀዳሚነት ገቢ እያገኘ ደረጃውን ይዟል፡፡  ኢትዮጵያ ለውጭ ገበያ የምታቀርበው ጥሬ ቡና መጠን እያንገዳገዳት ቢሆንም፣ ከቀድሞ የስታር ባክስ ባልደረባና የሥራ ፈጠራ ባለቤት በኩል የተሰማው አስገራሚ የቡና ዜና አነጋግሯል፡፡ ዜናው ኢትዮጵያውያን የተቀባበሉት ሲሆን ከማኅበራዊ ድረ ገፆች፣ በቲዊተር ገጻቸው ከተቀባበሉት መካከል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህርና በበርካታ ተቋማት ተሳትፎ ያላቸው ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ በርሄ ናቸው፡፡ ቡናን በምግብ መልክ በማዘጋጀት፣ ዱቄቱን ሲያሻዎ ዳቦ፣ ኩኪስ ወይም ሌላ ዓይነት ኬክ እንዲሠሩበት ወይም ግራኖላ፣ ቼኮሌትና ካራሜል የተባሉትን ዓይነት ኬኮች ለማዘጋጀት የቡና ገለፈት ተመራጭ መሆኑ ቢፈለሰፍም፣ ይህም ኢት