Posts

መድረክ ፓርቲ በአዲስ አበባ የጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደ

Image
ምንጭ፦ ሬዲዮ  ፋና  አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 16 ፣ 2006 ( ኤፍ.ቢ.ሲ. ) የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ፓርቲ ዛሬ በአዲስ አበባ የጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደ። የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎች መነሻቸውን ግንፍሌ ወንዝ ድልድይ ቅዱስ ማቲዎስ አንግሊካን ቤተክርስቲያን አድርገው ፥ በህንድ ኤምባሲ በመታጠፍ አቧሬ አደባባይን ፣ አድዋ ድልድይን በማቋረጥ ማጠቃለያቸውን የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 በተለምዶ ታቦት ማደሪያ እየተባለ በሚጠራው ሜዳ ላይ አድርገዋል። ሰልፈኞቹ ኢህአዴግ ለሰላማዊ ድርድር በሩን ክፍት ያድርግ ፤ በአንድነት ኢትዮጵያን እንገነባለን ፤ የፕሬስ ነፃነት ይከበር ፤ የታሰሩ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች ይፈቱ ፤ መልካም አስተዳደር እውን ይሁን እና የውሃ ፣ መብራትና ስልክ አገልግሎቶች ይስተካከሉ የሚሉ መፈክሮችን አሰምተዋል። በሰልፉ ማጠቃለያ ላይ የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጎይቶም ፀጋዬ እና ዋና ፀሃፊው አቶ ገብሩ ገብረማሪያም ንግግር ያደረጉ ሲሆን ፥ ፓርቲው ባዘጋጃቸው ወቅታዊ ጥያቄዎች ላይ  ኢህአዴግ  ምላሽ እንዲሰጥ ጠይቀዋል። በአዲስ አበባና ፊንፊኔ ዙሪያ የተዘጋጀው የጋራ ማስተር ፕላን ህዝባዊ ውይይት ተደርጎበት በህዝቡ መልካም ፈቃድ ተግባራዊ ሊደረግ ይገባልም ብለዋል።

ክብር ለሎቄ ሰማዕታት!

Image

ጥሬ ቡና ለውጭ ገበያ ማቅረብ እያሽቆለቆለ ነው

Image
- በውጭው ዓለም ከቡና ገለባ ምግብ ሊዘጋጅ ነው ከጥቂት ዓመታት በፊት ከቡና ኤክስፖርት ይገኝ የነበረው ገቢ አንድ ቢሊዮን ዶላርን ለመጠጋት የሚዳዳው ነበር፡፡ ከአራት ዓመት በፊት ከ840 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ከቡና ብቻ ተገኝቶ ነበር፡፡ በዚህ ዓመት ዘጠኝ ወራት ውስጥ መላክ የተቻለው ቡናና የተገኘው የውጭ ምንዛሪ ገቢ መጠን በጣም አነስተኛ ነው፡፡ 67 ሺሕ ቶን ቡና ለውጭ ገበያ ቀረበና ከ222 ሚሊዮን ዶላር ብዙም ፈቅ ያላለ ገቢ ተመዘገበ፡፡  የቡና ሽያጭ ለማሽቆልቆሉ የሚሰጡ በርካታ ምክንያቶች ይጠቅሳሉ፡፡ የዓለም የቡና ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ እየወረደ መምጣቱ ዋናው ምክንያት ተደርጐ ቢቆይም፣ በአገር ውስጥ የቡና ፍጆታ እየጨመረ መምጣት፣ ‹‹የጀበና ቡና›› መሸጫዎች መብዛት፣ ሌሎች ተወዳዳሪ አገሮች ከኢትዮጵያ የተሻለ የቡና መጠን ለውጭ ገበያ ማቅረባቸውና ሌሎችም ይጠቀሳሉ፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሽቆለቆለ የመጣው የቡና ኤክስፖርት ገበያ ከሚጠበቀው በታች ገቢ እያስገኘ ቢሆንም ከግብርና ምርቶች አሁንም በቀዳሚነት ገቢ እያገኘ ደረጃውን ይዟል፡፡  ኢትዮጵያ ለውጭ ገበያ የምታቀርበው ጥሬ ቡና መጠን እያንገዳገዳት ቢሆንም፣ ከቀድሞ የስታር ባክስ ባልደረባና የሥራ ፈጠራ ባለቤት በኩል የተሰማው አስገራሚ የቡና ዜና አነጋግሯል፡፡ ዜናው ኢትዮጵያውያን የተቀባበሉት ሲሆን ከማኅበራዊ ድረ ገፆች፣ በቲዊተር ገጻቸው ከተቀባበሉት መካከል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህርና በበርካታ ተቋማት ተሳትፎ ያላቸው ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ በርሄ ናቸው፡፡ ቡናን በምግብ መልክ በማዘጋጀት፣ ዱቄቱን ሲያሻዎ ዳቦ፣ ኩኪስ ወይም ሌላ ዓይነት ኬክ እንዲሠሩበት ወይም ግራኖላ፣ ቼኮሌትና ካራሜል የተባሉትን ዓይነት ኬኮች ለማዘጋጀት የቡና ገለፈት ተመራጭ መሆኑ ቢፈለሰፍም፣ ይህም ኢት

በመላው ዓለም ላይ ያሉ ሲዳማውያን 12ኛ ዓመት የሎቄ ሰማዕታት ቀን በማሰብ ላይ ናቸው

Image
የዛሬ 12 ኣመት ግንቦት 16  ህገመንግስታዊ መብቶቻቸውን በሰላማዊ መንገድ በጠየቁ ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ በጠቅላይ ሚኒስትር ኣቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ይመራ የነበረው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ጸጥታ ኃይል በፈጸመው የጅምላ ጭፍጨፋ የተሰውትን የሎቄ ሰላማዊ ሰልፈኞች ቀን በተለይ በሃዋሳ እና በሎንዶን ከተማ በተለያዩ  ዝግጅቶች በመታሰብ ላይ መሆኑ ታውቋል። የወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ ያሰባሰባቸው መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፤ ቀኑ በመላዋ ሲዳማ በተለይ በሃዋሳ፤ ቱላ፤ሞሮቾ፤ሌኩ፤ ይርጋኣለም፤ ኣለታ ጩኮ፤ ኣለታ ወንዶ፤ ዲላ እና ወንዶ ወሻ በተለያየ ደረጃ በመከበር ላይ ነው። ከከተሞቹ የወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፤ የከተሞቹ ነዋሪዎች በቡድን እና በግለሰብ ደረጃ ቀኑን እያሰቡ ይገኛሉ።  በሎንዶን ከተማ እና በሲዳማ ከተሞች የነበረውን ኣከባበር ዝርዝር መረጃ እንደደረሰን የምናቀርብ መሆናችንን ለመግለጽ እንወዳሃለን።

ግንቦት 16 የሲዳማ ህዝብ ሰማእታት ቀን 12ኛ ዓመት በልዩ ሁኔታ እየታሰበ ነው፡፡

የጽሁፉ ምንጭ፦  sidamanationalregionalstate By  ለገሰ   ዋንሳሞ   ዋቃዮ , Hawassa, Sidama ግንቦት  16  ቀን  1994  ዓ / ም   የሲዳማ   ህዝብ   ህገ   መንግስታዊ   መብቱን   ለማስከበር   ህግንና   ደንብን   ጠብቆ    በተወካዮቹ   አማካይነት   በቀን  12/09/1994 ዓ / ም   ለሲዳማ   ዞን   አስተዳዳር   በተጻፈ   ደብዳቤ   መብቱን   በሠላማዊ   መንገድ   ለማስከበርና   ያለበትን   ጥያቄ   ለመንግስት   ለማቅረብ   መነሻው   ገባህላዊ   ህዝብ መሰብሰቢያ   ከሆነው   ቱሉ   ቦታ   በማድረግ   በመስቀል   አደባባይ   የሚያበቃ   ሠለማዊ   ሰልፍ   ስለሚያደረግ   የአካባቢው   አስተዳዳር   ለሰልፉ   ጥበቃ እንዲያደርግ   አመልክቶ   ነበር፡፡   ዜጎች   መብታቸውን   በሠላማዊ   መንገድ   መጠይቅ   ይችላሉ   ተብሎ   በህገ   መንግሰቱ   ስለተደነገገ   ድንጋጌው   የሁሉንም   ብሔር   ብሔረሰቦችና   ህዝቦችን በእኩል   ያስከብራል   ብሎ   በሙሉ   እምነት   ተቀብሎ   ሰልፍ   የወጣው   ህዝብ   የሰልፉን   ደህንነት   መጠበቅ   የሚገባው   ከህዝብ   አብራክ   የወጣ   ህዝብንና የሀገርን   ደህንነት   ለመጠበቅ   ቃል   ኪዳን   የገባው   ሠራዊት   በገዛ   ወገኑ   ላይ   በጠራራ   ፀኃይ   የአውቶማቲክ   መሳሪያ   ውርጅብኝ   አወረደ፡፡   የሠላም   ተምሳለት   የሆነውን   ኢትዮጵያ   ባንድራ   በማስቀደም   ቅጠል   የያዘው   ህዝብ   ከልጅ   እስከ   አዛውንት   በደቂቃዎች   ልዩነት   እንደ   ቅጠል   ረገፈ፡፡ የተወሰኑ   አስከረኖች   በአይሱዙ   መኪና   በላይ   ላይ   ተደርቦ   እንደ   ኩ