በሃዋሳ ከተማ ለኣምስተኛ ጊዜ የተካሄደው Everyone ታላቁ ሩጫ ውጤት ደርሶናል
" የጨቅላ ህፃናትን ህይወት እንታደግ " በሚል መሪ ቃል የእናቶችን ሞት ለመታደግ ታስቦ የተዘጋጀው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በሃዋሳ መ ካሄ ዱ ይታወሳል ። ውድድሩ በግማሽ ማራቶን፣ በሰባት ኪሎ ሜትርና በህፃናት ውድድር በአንድ ነጥብ ሁለት ኪሎ ሜትር ተካሂዷል። ትናንት በተካሄደው ሩጫ አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ፣ አርቲስት ሰለሞን ቦጋለ፣ አርቲስት ግሩም ኤርሚያስ እና ሌሎችም ታዋቂ ሰዎች ተገኝተዋል። በወንዶች ግማሽ ማራቶን ጤናው በለጠ አንደኛ ሲሆን ርቀቱን ለማጠናቀቅ 1 ሰዓት ከ 3 ደቂቃ ከ 23 ሰከንድ ወስዶበታል። ሀብታሙ ካሳሁን 1 ሰዓት ከ 3 ደቂቃ ከ 45 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በሁለተኝነት አጠናቋል። ሀብታሙ ካሳሁን ውድድሩን ለማጠናቀቅ በግማሽ ማራቶን ሶስተኛ የሆነው የፍቃዱ ግርማ ሲሆን ከሀብታሙ በ 10 ሴኮንድ ዘግይቶ ገብቷል። በሴቶቹ የግማሽ ማራቶን የሩጫ ውድድር የውብዳር ተሾመ ውድድሯን በአንደኝነት ስታጠናቅቅ የወሰደባት ሰዓትም 1 ሰዓት ከ 15 ደቂቃ ከ 43 ሴኮንድ ነው። እምሻው ንጉሴ በሁለት ሴኮንድ በየውብዳር ተቀድማ ሁለተኛ ሆና ውድድሯን አጠናቃለች። በሴቶች ግማሽ ማራቶን ሶሰተኛ የሆነችው ኑሪት ሽመልስ ስትሆን የወሰደባት ሰዓትም 1 ሰዓት ከ 16 ደቂቃ ከ 15 ሴኮንድ ወስዶባታል። በሀዋሳ ከተማ ታላቁ ሩጫ ሲካሄድ ዘንድሮ ለአምስተኛ ጊዜ ነው። በዚህ ውድድር አሸናፊዋች በአጠቃላይ 64 ሺህ ሁለት መቶ ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። በሴትም በወንድም አንደኛ ሆነው ውድድራቸውን ለጨረሱ 14 ሺህ ብር ሽልማት ሲያገኙ ሁለተኛ ሆነው የጨረሱ 7 ሺህ ብር ተሸልመዋል፡፡ ሶስተኛ የወጡት ደግሞ 4 ሺህ ብር ተሸልመዋል።