ያላረፈው አየር ማረፊያ እንዳያፋጀን!
ከማህበራዊ መረብ የተገኘ በ ደሳለኝ መሳ በኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ ክልሎች መካከል የመሰረተ ልማትና የልማት ልዩነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋ መምጣቱን የተለያዩ ፀሐፊዎችና ባለሙያዎችም ጭምር ይስማሙበታል፡፡ መንግሰት በየጊዜ ፍትሐዊ የሀብት ክፍፍል በክልሎች መካከል አረጋግጫለው ብሎ ቢከራከርም በተጨባጭ ከሚታየው ነገር አንፃር የኢህአዴግ ክርክር ውሃ የሚቋጥር አልሆነም፡፡ በዚህ መጣጥፍ ልያነሳ የፈለኩት መንግስት ለአየር ማረፊያ ግንባታን ለማስፋፋት ካለው ፍላጎትና ተግባር አንፃር የፍትሐዊነት ጉድለት እንዳለው ከማሳየትም አልፎ አሁን በሲዳማ እየተሞከረው ያለው ነገር ከጥቅሙ ጉዳቱ ሊያመዝን እንደምችል ለማመላከት ነው፡፡ ማንም ሰው ለመገንዘብ እንደምችለው ( አልገነዝብም ካሉት ውጭ ) ሐዋሳ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሳች ካለችው የጎብኚዎች ሳቢቷና ከአካባቢም ከሚገኘው የኢኮኖሚ ወሳኝነቷ አንጻር አየር ማረፍያ አስፈላጊ ብቻ ሳይሆን አንገብጋቢ ጉዳይ ነው፡፡ ነገር ግን ይህ ነገር እስከ አሁን ድረስ ተፈፃሚ አልሆነም፤ ሀዋሳና አካባቢውም እድለኛ መሆን አልቻለም፡፡ ሀዋሳና አካባቢዋ አንድ አየር ማረፍያ እንኳን ሳይኖራት የተለያዩ ከልሎች ከአንድ በላይ አየር ማረፊያ ተከፋፍለዋል፡፡ ለምሳሌ የትግራይን ክልልን ብናይ በቅርቡ ዓለም አቀፍ በረራ ማስተናገድ ከጀመረው የመቐለ “አሉላ አባነጋ” አየር ማረፍያ በተጨማሪ በሌሎች አራት ከተሞች የሀገር ውስጥ በረራ የሚያስተዳግዱ አየር ማረፊያዎች ተገንብቶላቸዋል፡፡ በአማራ ክልልም በቅርቡ ወደ ጎሮቤት ሀገር በረራ ማስተናገድ የጀመረውን የባህር ዳሩን ጨምሮ በጎንደርና በወሎ የሀገር ውስጥ በረራ የሚያስተናግዱ አየር ማረፊያዎች አላቸው፡፡ ከባህር ዳር እሰከ ጎንደር ያለው ርቀት 225 ኪ . ሜ ሲሆን በዚህ ርቀት ሁለት አየር ማረፊያ አላት የአ