Posts

The Indiscriminate Killings of Oromo University Students and Other Civilians by Ethiopian Security Forces is Deplorable!

By United Sidama Parties for Freedom and Justice (USPFJ) May 7, 2014 It has been confirmed that the Ethiopian regime’s security forces have indiscriminately massacred over 50 unarmed Oromo University students who were all peacefully demonstrating against the plan of the regime to uproot Oromo peasants from the outskirts of Finfine/Addis Ababa. The casualties were said to have included children of age 6 and the elderly who were marching against the proposed plan. Over 250 Oromo youth and other civilians were seriously injured during the shootings which is said to be continuing sporadically as we speak. More than 2000 Oromo University students and other members of the Oromo nation were unlawfully detained. There is also allegations of torture of those detained. All Universities throughout Oromia were targeted and being encircled by the regime’s killing squad, the infamous ‘Agi’azi’ special force. The massacre began on 29th of April 2014 when Oromo University students peacefully e

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ እየተገነባ ያለው ዘመናዊ ስታዲየም ዩኒቨርሲቲውን የሚያስተዋውቅና የማህበረሰብ አገልግሎትን የሚያጠናክር ማዕከል መሆኑ ተገለጸ

Image
Photo from H.University website: Edited by Worancha Information Network በሀዋሳ ዪኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ፤ በአንድ ጣሪያ ስር ሁሉን-አቀፍ አገልግሎት ሊሰጥ በሚችል መልኩ እየተገነባ ያለው ስታዲየም፤ ተማሪዎች  በዙሪያው   ባሉ መዝናኛ ማዕከላት ተጠቅመው የሚዝናኑበትና ትምህርታቸውንም  ሊያጠኑ  የሚችሉበት ማዕከል መሆኑን የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ዴቭሎኘመንት ምክትል ኘሬዚዳንት ኘ/ር ንጋቱ ረጋሳ ገለፁ፡፡   የስታዲየሙ መገንባት ዩኒቨርሲቲው ከሁለት ዓመታት ወዲህ ለስፖርቱ ዕድገት የሰጠው ትኩረት ማሳያ ነው ያሉት ኘ/ር ንጋቱ፤ በከተማው የሚደረጉ ትላልቅ ዝግጅቶችን በማስተናገድ ረገድ ምቹ አማራጭ ሊሆን እንደሚችልና ጎን ለጎንም ዩኒቨርሲቲው የውስጥ ገቢውን ለማሳደግና የአከባቢውን ማህበረሰብ ለማገልገል የሚያመርታቸውን ምርቶች የሚያቀርብባቸው ሱቆች በስታዲየሙ ዲዛይን ውስጥ መካተታቸው ማዕከሉ ለየት ያለ ኮምኘሌክስ ያደረርገዋል ብለዋል፡፡   በስፖርት ሳይንስ የተካኑ ባለሙያዎችን በማፍራት ለሀገሪቱ ስፖርት እድገት በትጋት እየሰራ ላለው ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ፤ ትልቅ ግብዓት እንደሚሆን የታመነበት ይህ ዘመናዊ የስፖርት ማዘውተሪያ ኮምኘሌክስ፤ ለአከባቢው የስፖርት ቡድኖችም የመወዳደሪያና የልምምድ አማራጭ በመሆን ዩኒቨርሲቲው የማህብረሰብ አገልግሎትን የበለጠ እንደሚያጠናክር የሚጠበቅ ሲሆን፤ እስካሁን ድረስ ለግንባታው 140 ሚሊዮን ብር ወጪ መደረጉን ኘ/ር ንጋቱ አስረድተዋል፡፡ የዩኒቨርሲቲው ግንባታ ኘሮጀክት ጽ/ቤት ሥራ አስክያጅ የሆኑት አቶ ደንበሹ ነኤሬ በበኩላቸው የስታዲየሙን ግንባታ በማስመልከት በሰጡት ገለጻ¿ ዩኒቨርሲቲው በ2002 ዓ.ም የመንግስት ከፍተኛ ዩኒቨርሲቲዎችን ስፖርት ውድድር ለማዘጋጀት አምስት ሺህ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት 2ኛውን የኦፕን ዶር(Open-Door) ቀን አከበረ

Image
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እና የደቡብ ብ/ብ/ህ/ክ/መ ንግድ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ በጋር በመሆን ሁለተኛውን የኦፕን ዶር ቀን በደመቀ ሁኔታ ሚያዝያ 14/2006 ዓ.ም አከበሩ፡፡ "የዩኒቨርሲቲ ኢንዱስትሪ ትስስር ለህዳሴያችን" በሚል መሪ ቃል በተከበረው በዓል ላይ የፕሬዚዳንት ጽ/ቤትን በመወከል ዶ/ር ፍቅሬ ደሳለኝ የመክፈቻ ንግግር አድረገዋል፡፡ እሳቸው እንዳሉት ኦፕን ዶር በሀገራችን ብዙም ያተለመደ ነገር ግን የተለያዩ የምርምርና የቴክሎጂ ውጤቶችን የምናስተዋውቅበት ዘርፈ ብዙ ጠቃሜታዎች አሉት ብለዋል፡፡ ዶ/ር ፍቅሬ አክለውም ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በቴክኖሎጂው ዘርፍ እምርታና ለውጥ ለማምጣት ዩኒቨርሲቲው ከአውሮፓ ከካናዳ እና አሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ተባብሮ እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡ ዶ/ር ሞልቶት ዘውዴ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር በበኩላቸው እንዳተናገሩት መድረኩ በዩኒቨርሲቲውና እና በኢንስዲስትሪው መካከል ከፍተኛ ትስስር የሚፈጠርበትና ኢንስቲትዩቱ የሚሰራቸውን ስራዎች የምናስተዋውቅበት ነው ብለዋል፡፡ ዶ/ር ሞልቶት አክለው ይህ ቀን እንዲከበር በገንዘብና በተለያዩ ቁሳቁሶች ዩኒቨርሲቲውን የደገፈው የክልሉ ንግድ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮን አመስግነዋል፡፡ ለግማሽ ቀን በዩኒቨርሲቲው የስልጠና ማዕከል በተካሄደው መድረክ በኢንስቲትዩቱ ስር የሚገኙ የትምርት ክፍሎችና ት/ት ቤቶች እያከናወኗቸው ያሉትን ተግባርና እንቅስቃሴ አስተዋውቀዋል፡፡ በመቀጠልም የዩኒቨርሲቲ ኢንዱስትሪ ትስስርን ለማጠናከር የሚያስችል የመወያያ ሰነድ በዶ/ር ሞልቶት ዘውዴ ቀርቧል፡፡ ውይይቱንም የደቡብ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ ምክትል ርዕሰ መስተዳደርና የክልሉ ንግድ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ ኃላፊ የሆኑት

ስለ ሃዋሣ እና ዣ – ን – ዣ – ድ … ባ – ር

Image
ስለ ሃዋሣ እና ዣ – ን – ዣ – ድ … ባ – ር እግር ጥሎኝ… ውበትና ተፈጥሮን አድሎኝ… በፍቅርና በሃሴት ተፍነክነክ ብሎኝ… ደልቶኝ… ሞቆኝ… ምችት፣ ምችትችት ብሎኝ… የሐዋሳ ሰማይ ስር ከርሜ ነበር :: ሐዋሳ ፍቅር እንደሆነች ባየኋት ልክ የምታስደስተኝ… በኖርኩባት ልክ የምትናፍቀኝ… በሸሸኋት ልክ የምታስጨንቀኝ… መሽቶ በነጋ ቁጥር ነገን የምታስመኘኝ የስስት ከተማዬ ናት :: አይደለም አሁን እንዲህ በአስፋልትና በውስጥ ለውስጥ የኮብል ስቶን ንጣፍ አሸብርቃ ይቅርና አቧራ እየለበስን፣ በጠራራ ፀሃይ እየተጠበስን፣ የሞላልን ቀን በጋሪ፣ ያልሞላልን ቀን በኮቴ አሸዋውን በሲሊፐራችን እየዛቅን ስናዘግም እንኳ ለፍቅሯ ጥግ አልነበረኝም… ያን ደማቅ ሰማያዊ የታቦር ሃይስኩል ዩኒፎርም ራሳችን ላይ ጣል እንዳደረግን ጀላቲ እየመጠጥን… አሊያም ሸንኮራ እየጋጥን… ሲደላንም የማዘር ቤትን የ 60 ሳንቲም አምባሻ እየጎመጥን… በላዩ ውሃችንን አንዳንዴም ʿ ሴሏችንን ʾ እየጨለጥን ጎዳናውን ስንሸከሽከው እንኳ ለፍቅሯ ልክ አልነበረኝም… እንዲህ እንደዛሬው በባጃጅ ሽር በሚባልበት ወቅት ይቅርና የጡረታ ዘመኗ ባለፈባት ድክሞ ሳይክል SOS ን አልፌ ጥቁር ዉሃ ድረስ ስንተፋተፍ እንኳ ለፍቅሯ የሚያህላት አልነበረኝም !… ዛሬም የሰላምና የደስታ ጥጌ ሐዋሳ ናት !… ሐዋሳ ሰላም… ሐዋሳ ፍቅር !… እናም የሲዳማን የቆጮ ምግቦችና የወተት አይነቶች እያጣጣምኩ፣ የቶኪቻውን ( የዮሐንስ በቀለን ) ጫምባላላ እየዘፈንኩ ሐዋሳ ከርሜ ነበር… ምንም እንኳ በዛ ያሉ የጭፈራ ዘፈኖች ቢኖሩም ጫምባላላን ግን እጅግ እወደዋለሁ… ከባህል አንፃር ደህና ትርጉም ስላለው ይሆን ?!… ነሸጥ ስለሚያደርገኝ ይሆን ?!… እንጃ ብቻ !… “ አይዴ ጫምባላላ” … “አይዴ ጫምባላላ” … ማ