Posts

የሲዳማ ተረቶችን ያዳምጡ

Image
የብሪትሽ ካውንስል ኣዘጋጅነት ከሲዳማ ዞን ተሰባሰበው ሃዋሳ ከተማ በተለያዩ ግለሰቦች የቀረቡ ተረቶች የሲዳማ የሳር ቤት የሲዳማ ተረት በይሳሃቅ ኣልዳዳ (ሃዋሳ)

ታላቁ የኢትዮጵያ ሩጫ በመጪው እሁድ በሐዋሳ ከተማ ይካሄዳል

Image
ፎቶ  @  http://www.photorun.net/index.php?content=photodisplay&id=1065&event=Gebrselassie_Hawasa_Resort አዲስ አበባ ሚያዝያ 29/2006 አምስተኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ  ''የጨቅላ ህጻናትን ህይወት እንታደግ''  በሚል መሪ ቃል በመጪው እሁድ በሃዋሳ ይካሄዳል። የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጽህፈት ቤት የማርኬቲንግና የገቢ ማሰባሰቢያ አስተባባሪ አቶ መርዕድ ዮሴፍ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ውድድሩ ከ10ሺ በላይ ሰዎችን ያሳትፋል፡፡ ጽህፈት ቤቱ ከ'ሁሉም' ዘመቻ ጋር በመተባበር በሚያዘጋጀው ሩጫ በህጻናት፣ በጤና ቡድኖችና በአትሌቶች መካከል የሰባት ኪሎ ሜትርና የግማሽ ማራቶን የሩጫ ውድድር ይደረጋል፡፡ አቶ መርዕድ እንዳሉት በሰባት ኪሎ ሜትሩ ውድድር ከ10ሺ በላይ የጤና ቡድኖችና 750 ህጻናት ይሳተፉበታል። በሩጫው 120 የክለብ አትሌቶች ሲሳተፉ ከአንድ እስከ ሶስት ለሚወጡ አትሌቶች የ14፣ የሰባትና የአራት ሺህ ብር ሽልማት ይበረከታል፡፡

allAfrica.com: Ethiopia Most Successful in Africa At Cutting Maternal Deaths - NGO (Page 1 of 2)

Image
allAfrica.com: Ethiopia Most Successful in Africa At Cutting Maternal Deaths - NGO (Page 1 of 2)

Scholars at Risk ‘Gravely Concerned’ About University Lecturers Arrested in Ethiopia

Image
Scholars at Risk ‘Gravely Concerned’ About University Lecturers Arrested in Ethiopia

የሕዝብ ተሳትፎ በተግባር ይረጋገጥ!

Image
ሪፖርተር ጋዜጣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ከፍተኛ ኮሚሽነር ሚያዝያ 28 ቀን 2006 ዓ.ም. በስዊዘርላንድ ዋና ከተማ ጄኔቭ ባዘጋጀው ወቅታዊ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ግምገማ ላይ ኢትዮጵያ እየተገመገመች ነበር፡፡ በዚሀ ግምገማ ላይ ሦስት አገሮች ማለትም ናሚቢያ፣ ካዛክስታንና ቼክ ሪፐብሊክ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝን በተመለከተ በአቻ ገምጋሚነት ተሳታፊ ነበሩ፡፡ ይህ በተመድ የተዘጋጀ ግምገማ ለሰብዓዊ መብት አከባበር የሕዝብ በአገር ኢኮኖሚ፣ ፖለቲካና ማኅበራዊ ጉዳዮች ውስጥ በንቃት ተሳታፊ መሆን ዋነኛውና መሠረታዊው መርህ መሆኑን አስቀምጧል፡፡ በዚህ ግምገማ ላይ ኢትዮጵያን ወክለው የተገኙ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትም የአንድ አገር ልማትና ዕድገት የሚረጋገጠው በሕዝብ ያልተገደበ ተሳትፎ ላይ ሲመሠረት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በተለይ በግምገማው ላይ ከተለያዩ አገሮችና ወገኖች የተነሱ መሠረታዊ የሚባሉት ነጥቦች ማለት የምንፈልጋቸውን በይበልጥ ያብራሩልናል፡፡ በተለይ አንኳር ተብለው የተነሱ ጉዳዮችን ስንመረምር የሕዝብ ተሳትፎ አስፈላጊነትን ቁልጭ አድርገው ያስቀምጡልናል፡፡  በግምገማው ላይ ከተነሱ ሐሳቦች መካከል በ2007 ዓ.ም. ሊደረግ የታሰበው ብሔራዊ ምርጫ ነፃ፣ ፍትሐዊና ሁሉንም የሚያሳትፍ መሆን እንዳለበት፣ ኢትዮጵያ የፀረ ሽብርተኝነት አዋጁን በድጋሚ ማጤን እንደሚገባት፣ የጋዜጠኞች፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችና የፖለቲከኞች በዘፈቀደ መታሰርና መጉላላት መቆም እንዳለበት፣ ሕጋዊ አካሄድን የጠበቀ የዳኝነትና የፍትሕ ሥርዓት መኖር አስፈላጊ መሆኑን፣ በበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማኅበራት ላይ የወጣው ሕግ መሻሻል እንደሚኖርበት፣ ኢትዮጵያ ብሔራዊ የሰብዓዊ መብት የድርጊት መርሐ ግብርን ሙሉ ለሙሉ