Deadly Protests in Ethiopia Over Plans to Expand Capital — At Least 17 Killed
Photo: Addis Ababa University Students Urge John Kerry to condemn the police violence against fellow students in Ambo -- a town located in the Oromia region of Ethiopia. (Picture: Twitter.com May 1, 2014 ) - See more at: http://www.tadias.com/05/02/2014/deadly-protests-in-ambo-ethiopia-over-plans-to-expand-capital-17-killed/#sthash.R2GfovTw.dpuf ከአዲስ አበባና የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ማስተር ፕላን ጋር በተገናኘ ተማሪዎች ተቃውሞ አሰሙ ሪፖርተር ጋዜጣ -የኦሮሚያ ክልል የታሰረም ሆነ የተደበደበ ተማሪ የለም አለ በአዲስ አበባና በዙሪያዋ ያሉ የኦሮሚያ ክልል ልዩ ዞንን በአንድ የማስተር ፕላን ማቀናጀት ምክንያት፣ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች በሚገኝ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚማሩ የኦሮሚያ ተማሪዎች ተቃውሞ ማድረጋቸውን ምንጮች ገለጹ፡፡ የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ስለ ተማሪዎቹ ተቃውሞ በግልጽ ያለው ነገር ባይኖርም፣ በፀጥታ ኃይሎች ድብደባና እስራት ተፈጽሞባቸዋል መባሉን ግን አስተባብሏል፡፡ ለአዲስ አበባና ለኦሮሚያ ልዩ ዞኖች የተዘጋጀው የተቀናጀ ማስተር ፕላን ካለፉት ጥቂት ሳምንታት ጀምሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና የኦሮሚያ ክልል አመራሮች ሲወያዩበት መቆየታቸውን፣ ይህንን ተከትሎ ሕገ መንግሥታዊ ጥያቄዎች ማስነሳቱንም ጨምሮ መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ግን የኦሮሞ ተወላጆች ናቸው በተባሉ ተማሪዎች በአገሪቱ በተለያዩ ቦታዎች የሚገኙ በተለይም በጂማ፣ በአምቦ፣ በወለጋና በሀረማያ ዩኒቨርሲ