Posts

በሲዳማ ለምነሱት የክልል ኣስተዳደር ጨምሮ ለሌሎች የመልካምኣስተዳደር እና የሰብኣዊ መብት ጥያቄዎችን ለማፈን መንግስት የምወስደውን የኃይል እርምጃ እንድያቆም የሲዳማ መብት ተከራካሪዎች ድምጻቸውን ማሰማት ኣለባቸው ተባለ፤የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው

Image
ፎቶ  ኢንተርኔት  ሰሞኑን ከሬውተርስ የተገኘው ዜና እንደሚያመለክተው የኣሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በዋናነት ዲሞክራሲና ሰብአዊ መብትን ማሳደግ በሚቻልበት አቅጣጫ ላይ ከሀገ ሪ ቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ይ መክራ ሉ ተብሎ ይጠበቃል ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያን ጉብኚት ኣስመልክቶ ሪፖርተራችን ሚሊዮን ማቲያስ ያናገራቸው ስማቸው እንድገለጽ ያልፈለጉ የሲዳማ ፖለቲካ ተንታኞች የሆኑት ምሁራን እንደተናገሩት፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ቆይታቸው በኣገሪቱ ባለው የሰብኣዊ መብት ኣያያዝ ላይ የምመክሩ በመሆኑ በዚህ ኣጋጣም በሲዳማ ያለውን የስብኣዊ መብት ረገጣ የማጋለጥ ስራ መስራት ኣለበት ብለዋል። ኣክለውም መንግስት በሲዳማ በተለያዩ ጊዚያት የሰብኣዊ መብት ረገጣ መፈጸሙን ኣስታውሰው፤ መንግስት በሲዳማ የምፈጽመውን የሰብኣዊ መብት ተባብሶ መቀጠሉን ኣመልክተዋል። ለኣብነትም በዚህ ወር ውስጥ በሃዋሳ ከተማ የኣላሙራ እና ታቦር ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ የሲዳማ ተማሪዎች ከሲዳማ ኣፎ ጋር በተያያዘ ላነሱት የመብት ጥያቄ መንግስት የኃይል ምላሽ መስጠቱን ኣብራርተዋል። በሲዳማ ለምነሱት የክልል ኣስተዳደር ጥያቄን ጨምሮ ለሌሎች የመልካምኣስተዳደር እና የሰብኣዊ መብት ጥያቄዎች መንግስት በሰላማዊ መንገድ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ የኃይል እርምጃ መውሰድ መምረጡን እንድያቆም ብሎም ዞኑ የምፈጽመውን የዲሞክራሲ እና ሰብኣዊ መብት ረገጣ ለማስቆም የምታገሉ ህዝባዊ ድርጅቶች ይህንን ኣጋጣሚ በመጠቀም ድምጻቸውን ማሰማት ኣለባቸው በማለት እኝኑ ምሁራን መክረዋል። ኬሪ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማሪያም ደሳለኝ እና ከኢፌድሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴድሮስ አድሃኖም ጋር የሚገናኙ ሲሆን በቀጠናው

ሩጥ ሃዋሳ

Image
ፎቶ @  http://www.photorun.net/index.php?content=photodisplay&id=1065&event=Gebrselassie_Hawasa_Resort ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት፦  ኃይሌ ሪዞርት ሃዋሳ

ኢህአዴግ ራሱ ጥያቄ አውጥቶ፣ ራሱ ተፈትኖ፣ ራሱ ያርማል!

Image
ፓርላማው እንዲሟሟቅ ትኩስ ቡናና ሳቅ ያስፈልጋል!         ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ለፓርላማ ያቀረቡት በፋሲካ ማግስት ነው ማለት ይቻላል- ባለፈው ሐሙስ፡፡ ለዚህም ነው አንዳንድ የምክር ቤቱ አባላት ከሌላው ጊዜ በተለየ እንቅልፍ እንቅልፍ ያላቸው (የበዓል ማግስት እኮ ይጫጫናል!) ለነገሩ … ያንን ሁሉ ሰዓት አዳራሽ ውስጥ መሰብሰብም እኮ እንቅልፍ ያመጣል፡፡ ምናልባት በጣም የባሰበት እኮ ጥያቄውን ለጠ/ሚኒስትሩ ከአቀረበ በኋላ፣ “ለሽ” ሊል ይችላል፡፡ ደግነቱ እኛ እንሰማዋለን (“እኛ” ወካዮቼ ማለቴ ነው!) በነገራችሁ ላይ በበቀደሙ ፓርላማ  እንቅልፍ ያስቸገራቸውን የምክር ቤት አባላት ለመውቀስ አይደለም - የሚመለከተው አካል መፍትሄ እንዲያፈላልግ መተንኮሴ ነው (የግምገማ ተጠሪውን ሳይሆን የሪፍሬሽመንት ክፍሉን!)   ከምሬ ነው--- ለምን አጭር የቡና ሰዓት አይኖርም? (“ኖሮ አያውቅም ወይም አልተለመደም” እንዳትሉኝ!) ለነገሩ ብትሉኝም አልቀበልም፡፡ ይኼውላችሁ---- ድሮ የሌሉ አሁን የተጀመሩ ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ እናም ----- ድሮ የቡና ሰዓት የሌለው ምናልባት ዘመኑ ስለማይጫጫን ይሆናል፡፡ አሁን ግን ይጫጫናል እያልን ነው፤ስለዚህ መፍትሄ የግድ ነው፡፡ በእርግጥ መፍትሄው ትኩስ ቡና ብቻ ነው እያልኩ አይደለም፡፡ ትኩስ ቀልድ ሊሆንም ይችላል፤ ዋናው ነገር ከእንቅልፍና ከድብርት ስሜት ማነቃቃቱ ነው፡፡ ያለዚያ እኮ ጠ/ሚኒስትሩ ከስንት አንዴ ተገኝተው የሚያቀርቡት ሪፖርትና ማብራሪያ ከንቱ ሆነ ማለት ነው! (እንቅልፍ ወስዶት “ገና” እንዳመለጠው ትንሽ ልጅ!)  እናላችሁ --- አባላቱ ሁሉን ነገር በንቃት እንዲከታተሉ ከፈለግን coffee break ቢኖር አይከፋም፡፡ አሊያም ደግሞ አንድ ሁለት ሞቅ ያለ

ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የቡና ኮንፈረንስ እንድታዘጋጅ ተመረጠች

- ውድድሩ አፍሪካና አውሮፓን አፎካክሯል በዓለም አቀፍ የቡና ግብይት ውስጥ ከፍተኛውን ሚና የሚጫወቱት ቡና ገዥ ኩባንያዎችና አምራቾች በአባልነት የታቀፉበት ዓለም አቀፍ የቡና ድርጅት፣ ኢትዮጵያ አራተኛውን ዓለም አቀፍ የቡና ኮንፈረንስ እንድታዘጋጅ መረጠ፡፡ እ.ኤ.አ. በማርች 2016 የሚዘጋጀውን ኮንፈረንስ ለማስተናገድ የመጨረሻው ውድድር ላይ ቀርበው የነበሩት ኢትዮጵያና ጣሊያን ናቸው፡፡ ምርጫው በተካሄደበት  ለንደን ከተማ ተገኝተው የነበሩ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን አባላት እንደገለጹት፣ ውድድሩ ከፍተኛ ፉክክር የነበረበት ቢሆንም ኢትዮጵያ ልታሸንፍ ችላለች፡፡  በመጨረሻው ውድድር ላይ ከድምፅ ሰጪዎች መካከል ግዙፎቹ የአውሮፓ ቡና ገዥ ኩባንያዎች ድምፃቸውን ለጣሊያን ሰጥተው ነበር፡፡ አፍሪካውያንና ሌሎች ቡና አብቃዮች ደግሞ ለኢትዮጵያ ድምፅ በመስጠት ውድድሩ በአፍሪካውያንና በአውሮፓውያን መካከል እንዲሆን አድርገው ነበር ብለዋል፡፡ በተለይ በዓለም አቀፉ ድርጅት ውስጥ ከፍተኛ ድምፅ ካላቸው አገሮች መካከል አንዷ የሆነችው ብራዚል ድምጿን ለኢትዮጵያ በመስጠቷ ለኢትዮጵያ አሸናፊነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል ተብሏል፡፡ ከመጨረሻው ውድድር ቀደም ብሎ ኮንፈረንሱን ለማዘጋጀት ከአፍሪካ ኮትዲቯር፣ ጋቦንና ኬንያ ጥያቄ አቅርበው የነበረ ቢሆንም ሁሉም አገሮች የኢትዮጵያን የተወዳዳሪነት ጥያቄ በመቀበል ድምፃቸውን ሰጥተዋታል፡፡ ኮንፈረንሱ አፍሪካ ውስጥ መካሄዱ ትልቅ ዕድል ነው በማለት ለኢትዮጵያ ዕድሉ እንዲሰጣት አፍሪካውያኑ ድጋፍ እንዳሰባሰቡም በቦታው ከነበሩ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን አባላት ለመረዳት ተችሏል፡፡  ከዓለም የቡና ድርጅት (አይሲኦ) መካከል 50 በመቶዎቹ የቡና ገዥ ኩባንያዎች የሚወከሉባቸው አገሮች ሲሆኑ፣ ቀሪዎቹ ቡና አምራች አገሮች

ዋና ኦዲተር ለብክነት የተጋለጡ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ሒሳቦችን አጋለጠ

Image
- ከ1.5 ቢሊዮን ብር በላይ ያልተሰበሰበ ሒሳብ አለ -785 ሚሊዮን ብር ሕጋዊ ያልሆነ ወጪ ታይቷል -ከ2.3 ቢሊዮን ብር በላይ ያልተሠራበት በጀት ተገኝቷል የፌደራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ላለፉት በርካታ ዓመታት ለፓርላማ ሲያቀርበው እንደቆየው ሁሉ፣ ለብክነት የተጋለጠ በቢሊዮኖች የሚቆጠር የመንግሥት ሀብት መኖሩን ባለፈው ሚያዝያ 14 ቀን 2006 ዓ.ም. ለፓርላማው ይፋ አድርጓል፡፡ ተመሳሳይ ሪፖርቶችን ሲሰማ የቆየው ፓርላማው ፈጣን ዕርምጃ ከመውሰድ ይልቅ የአንድ ዓመት ገደብን መስጠት መርጧል፡፡ በዝቅተኛ የደመወዝ ክፍያ ምክንያት ሠራተኞችን ለማቆየት መቸገራቸውን የገለጹት የፌደራሉ ዋና ኦዲተር አቶ ገመቹ ዱቢሶ፣ ችግሩን ለመቅረፍ ራሳቸው ጭምር በቡድን መሪነት በተሳተፉበት የ130 የፌደራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶችን የ2005 ዓ.ም. በጀት ኦዲት በማድረግ፣ እንዲሁም በኦዲት ሰርቪስ ኮርፖሬሽን የስምንት መሥሪያ ቤቶችን ኦዲት በማሠራት፣ በአጠቃላይ የ138 መሥሪያ ቤቶችን ኦዲት በመተንተን የኦዲት ግኝቱን ለፓርላማ አቅርበዋል፡፡ ከቀረበው የፋይናንስ ሕጋዊነትን የተመለከተ የኦዲት ሪፖርት ውስጥ አንድ ቢሊዮን 527 ሚሊዮን ብር ተሰብሳቢ ሒሳብ መኖሩን፣ ሕጋዊ ሥርዓቱን በልተከተለ መንገድ የተለያዩ የመንግሥት ድርጅቶች 785 ሚሊዮን ብር ወጪ ማድረጋቸውን፣ የተፈቀደው በጀት በትክክል ሥራ ላይ መዋሉን ለማረጋገጥ በተደረገ ኦዲት ደግሞ 2.3 ቢሊዮን ብር ያልተሠራበት በጀት መገኘቱን ይፋ አድርገዋል፡፡ ውዝፍ ተሰብሳቢ ሒሳብ ሕጉ በሚፈቅደው መሠረት በወቅቱ ካልተወራረደ ወይም ካልተሰበሰበ በቆየ ቁጥር የመሰብሰብና ወደ ሀብትነት የመለወጥ ዕድሉ አሳሳቢ መሆኑን የገለጹት ዋና ኦዲተሩ፣ ኦዲት ከተደረጉት መሥሪያ ቤቶች 77 በሚሆኑት ላይ 877.1