Posts

በፕሪሚየር ሊግ ሲዳማ ቡና ሲያሸንፍ ሃዋሳ ከነማ ተሸንፏል

Image
በሰሞኑ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር የሲዳማ ክለቦች ድል እና ሽንፈት ኣስተናግደዋል። መከላከያን የገጠመው ሲዳማ ቡና የ2 ለ0 ድል ሲቀናው ሃዋሳ ከነማ ደግሞ  በመብራት 0ለ2 ሽንፈትን ኣስተናግዷል። ጥቂት ሰለ ኣሽናፊው የሲዳማ ቡና ክለብ ተጫዋቾች ምንጭ፦ የክለቡ ድረ ገጽ

This Is Coffeeland: Sidama

Image
This Is Coffeeland I had never even seen a coffee tree. But during harvest season in Ethiopia – where coffee is everything – I was determined to learn to drink like a local. By David Farley The first thing Azeb wanted to know about me was if I was on Facebook. After that she got to the less important stuff: Where I was from, if I was married, had kids, believed in God — and what was I doing in southern Ethiopia? Azeb, a 25-year-old business student with big glowing eyes and long dark hair, was born and raised not far from where we were having breakfast. We ended up sitting together when we realized we were the only people in the dining room at the Lesiwon Hotel in Yirgacheffe, the namesake town of a region known to coffee cognoscenti for producing some of Ethiopia’s highest-quality coffee beans. As Azeb scooped up pieces of her omelet with torn-off hunks of bread, as is the Ethiopian custom, I stabbed at mine with a fork and told her about my travels thus far in her country. But

ሐሰተኛ ሪፖርቶች አያደናግሩን!

Image
በአሁኑ ጊዜ በተለያዩ መንግሥታዊ ተቋማት አማካይነት የሚወጡ ሪፖርቶችን ለማመን የማይቻልበት ደረጃ ላይ ተደርሷል፡፡ በአኃዝና በመቶኛ ሥሌቶች እየተቀናበሩ የሚቀርቡ በርካታዎቹ ሪፖርቶች በጥንቃቄ ሲታዩ በከፍተኛ ደረጃ መጣረሶች እንዳሉባቸው በቀላሉ እንረዳለን፡፡ ሌላው ቀርቶ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተለጠጡ የሚታቀዱ ኢኮኖሚያዊም ሆኑ ማኅበራዊ ዕቅዶች መነሻቸው የተሳሳቱ ሪፖርቶች ናቸው፡፡ መንግሥት የአምስት ዓመቱን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ይፋ ሲያደርግ ብዙዎች የፈሩት ዕቅዱ ያለመጠን መጋነኑን ነበር፡፡ አሁን ዕቅዱ በዝርዝር ሲታይ ከአምስት ዓመት በኋላ ይደረስበታል የተባለው ግብ በተጨባጭ ተግባራዊ አልሆነም፡፡ በተለይ እየተለጠጡ የሚወጡ ዕቅዶች ተጨባጩን ሁኔታ ስለማያገናዝቡ በመጨረሻ የሚገኘው ውጤት ከተጠበቀው በታች ይሆናል፡፡ ከዚህ ቀደም ለፓርላማ ይቀርቡ የነበሩ የመንግሥታዊ ተቋማት ሪፖርቶች እርስ በርስ የሚጣረሱ ከመሆናቸውም በላይ፣ ያለውን እውነታ በትክክል የሚገልጹ አልነበሩም፡፡ ፓርላማው አስፈጻሚውን የመንግሥት አካል ወጥሮ መያዝ ሲጀምር ግን  እንዲህ ዓይነቶቹ ሪፖርቶች ቀስ በቀስ ፓርላማው ዘንድ መቅረባቸው እየቀነሰ መጥቷል፡፡ ምንም እንኳን አሁንም አስገራሚ ሪፖርቶች እንደሚቀርቡ ቢታወቅም፡፡ በመንግሥት መገናኛ ብዙኃን አማካይነት የሚቀርቡ አንዳንድ ሪፖርቶች ግን የሕዝቡን የማወቅ መብት የሚጋፉ ከመሆናቸውም በላይ፣ የተቋማቱን ዝርክርክነት የሚያጋልጡ ናቸው፡፡ ለምሳሌ በአንድ ወረዳ አንድ ጤና ጣቢያ እንደነበር ይነገርና ተጨማሪ አንድ ጤና ጣቢያ ሲገነባ የወረዳው የጤና አገልግሎት ሽፋን መቶ በመቶ አደገ ይባላል፡፡ አንድ ትምህርት ቤት ላይ ሌላ ትምህርት ቤት ሲጨመር ስታትስቲክሱ በዚህ ሁኔታ ተባዝቶ ይቀርባል፡፡ በፌደራል መንግሥት

ደቡብ ግሎባል ባንክ ወደ አትራፊነት መግባቱን ገለጸ

Image
- የኮር ባንኪንግ ቴክኖሎጂ ግዥ ፈጸመ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በኢትዮጵያ በባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ ለመሰማራት ይጠየቅ የነበረውን የተከፈለ 100 ሚሊዮን ብር ወደ 500 ሚሊዮን ብር ከማሳደጉ በፊት 15ኛው የግል ባንክ በመሆን የአገሪቱን የባንክ ኢንዱስትሪ የተቀላቀለው ደቡብ ግሎባል ባንክ 19 ወራት አስቆጥሯል፡፡ ከሌሎች የግል ባንኮች በተለየ በአንድ የአክሲዮን ሽያጭ ፕሮግራም በሚሊዮን የሚቆጠር አክሲዮን በመሸጥ በ138.9 ሚሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታል በማሰባሰብ ወደ ሥራ የገባ ባንክ ነው፡፡ በ5481 ባለአክሲዮኖች የተመሠረተው ይህ ባንክ ወደ ሥራ ከገባ በኋላ በመጀመርያው የሥራ ዓመት (10 ወራት) አትራፊ መሆን ባይችልም በአሁኑ ወቅት ግን ወደአትራፊነት እየገባ መሆኑን ባንኩ አስታውቋል፡፡ የባንኩን የ19 ወራት የሥራ እንቅስቃሴ በተመለከተ በተሰጠ መግለጫ ላይ እንደተመለከተው፣ ባንኩ መጋቢት 2006 ዓ.ም. 14.5 ሚሊዮን ብር አትርፏል፡፡ የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ ወርቁ ለማ እንደገለጹት፣ በመጀመርያው ዓመት ላይ ተመዝግቦ የነበረው ኪሳራ አሁን መለወጡንና በየወሩ እያተረፈ መጓዝ ጀምሯል፡፡ በመጀመርያው የሥራ ዘመንም ትርፍ ይገኛል ተብሎ ባይጠበቅም ደቡብ ግሎባል ባንክ ግን በአጭር ጊዜ ወደ ትርፍ መግባት ከመቻሉም በላይ አሁን እያስመዘገበ ያለው ትርፍ በ2006 በጀት መዝጊያ ጥሩ ትርፍ የሚያገኝ መሆኑን ያሳያልም ብለዋል፡፡ በመጋቢት 2006 ዓ.ም. ያስመዘገበው የትርፍ መጠንም አምና ከነበረው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 223 በመቶ ብልጫ ያለው ነው፡፡  ባንኩ ትርፍ ማስመዝገብ ከመጀመሩ ባሻገር በዋና ዋና የባንክ አገልግሎቱ እያደገ መምጣቱን የፕሬዚዳንቱ ገለጻ ያስረዳል፡፡ የባንኩ የሥራ እንቅስቃሴ በለውጥ ጎዳና ላይ ስለመሆኑም ዋና

ገዥው ፓርቲ በከተማ ኣስተዳደር ስም በሲዳማ የፈጸመውን ኣይነት የመሬት ወረራ በኣሮሚያ ልዩ ዞኖች መድገም ኣልቻለም

Image
ገዥው ፓርቲ በከተማ ኣስተዳደር ስም በሲዳማ ዞን ሃዋሳ ዙሪያ ወረዳ ውስጥ ይገኙ የነበሩትን የገጠር ቀበሌዎችን በሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር ስር በማጠቃለል በልማት ስም የኣርሶ ኣደሮች ይዞታ የሆነውን መሬት በመንጠቅ በልዝ ለባለጋብቶች ለማከፋፈል እና ኣርሶ ኣደሮችን መሬት ኣልባ ለማድረግ በኦሮሚያ ክልል ያደረገው ጥረት ኣለመሳካቱ ሰሞኑን ተሰምቷል። ዝርዝር ዜና የሪፖርተር ጋዜጣ ነው።   የኦሮሚያ ልዩ ዞኖችን በሚያጠቃልለው ማስተር ፕላን ላይ መግባባት አልተቻለም - በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ማስተር ፕላኑን ተቃወሙ -ከአዲስ አበባ አዳማ በአዲሱ መንገድ ግራና ቀኝ መሬት መሸጥ ቁጥጥር ሊደረግበት ነው አዲስ አበባ ከተማና በዙሪያዋ የሚገኙትን አምስት ልዩ የአሮሚያ ዞን ከተሞች  ሰበታ፣ ቡራዩ፣ ሱሉልታ፣ ለገጣፎና ገላን አጠቃሎ በተሠራው ማስተር ፕላን ላይ መግባባት ባለመቻሉ ግምገማዊ ውይይት በማድረግ የመግባቢያ ፊርማ ለማድረግ የተጀመረው ስብሰባ ሳይጠናቀቅ መቋረጡን ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡ መጋቢት 19 ቀን 2006 ዓ.ም. የልዩ ዞኑና የአዲስ አበባ ከተማ ተወካዮች በማስተር ፕላኑ አስተዳደራዊ ጉዳዮች ላይ ለመወያየት የተሰበሰቡ ቢሆንም፣ በተሠራው ማስተር ፕላን ላይ አንድ ዓይነት አቋም ሊይዙ አለመቻላቸው ታውቋል፡፡ ከአንዳንድ ተሳታፊዎች መግባባቱን ወደኋላ ሊመልሱ የሚችሉ ጥያቄዎችና አስተያየቶች በመነሳታቸው፣ በዕለቱ ይካሄዳል ተብሎ በነበረው የጋራ ውይይት ላይ ልዩነት መፈጠሩን ምንጮች አስረድተዋል፡፡ በአዳማ በተደረገው ውይይት በልዩ ዞኖቹ በኩል የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አብዱልአዚዝ መሐመድና አዲስ አበባን በመወከል ከንቲባ ድሪባ ኩማ በጋራ ውይይቱን የመሩት ቢሆንም፣ በውይይቱ የተሳተፉ የተለያዩ ቢ