ገዥው ፓርቲ በከተማ ኣስተዳደር ስም በሲዳማ የፈጸመውን ኣይነት የመሬት ወረራ በኣሮሚያ ልዩ ዞኖች መድገም ኣልቻለም
ገዥው ፓርቲ በከተማ ኣስተዳደር ስም በሲዳማ ዞን ሃዋሳ ዙሪያ ወረዳ ውስጥ ይገኙ የነበሩትን የገጠር ቀበሌዎችን በሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር ስር በማጠቃለል በልማት ስም የኣርሶ ኣደሮች ይዞታ የሆነውን መሬት በመንጠቅ በልዝ ለባለጋብቶች ለማከፋፈል እና ኣርሶ ኣደሮችን መሬት ኣልባ ለማድረግ በኦሮሚያ ክልል ያደረገው ጥረት ኣለመሳካቱ ሰሞኑን ተሰምቷል። ዝርዝር ዜና የሪፖርተር ጋዜጣ ነው። የኦሮሚያ ልዩ ዞኖችን በሚያጠቃልለው ማስተር ፕላን ላይ መግባባት አልተቻለም - በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ማስተር ፕላኑን ተቃወሙ -ከአዲስ አበባ አዳማ በአዲሱ መንገድ ግራና ቀኝ መሬት መሸጥ ቁጥጥር ሊደረግበት ነው አዲስ አበባ ከተማና በዙሪያዋ የሚገኙትን አምስት ልዩ የአሮሚያ ዞን ከተሞች ሰበታ፣ ቡራዩ፣ ሱሉልታ፣ ለገጣፎና ገላን አጠቃሎ በተሠራው ማስተር ፕላን ላይ መግባባት ባለመቻሉ ግምገማዊ ውይይት በማድረግ የመግባቢያ ፊርማ ለማድረግ የተጀመረው ስብሰባ ሳይጠናቀቅ መቋረጡን ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡ መጋቢት 19 ቀን 2006 ዓ.ም. የልዩ ዞኑና የአዲስ አበባ ከተማ ተወካዮች በማስተር ፕላኑ አስተዳደራዊ ጉዳዮች ላይ ለመወያየት የተሰበሰቡ ቢሆንም፣ በተሠራው ማስተር ፕላን ላይ አንድ ዓይነት አቋም ሊይዙ አለመቻላቸው ታውቋል፡፡ ከአንዳንድ ተሳታፊዎች መግባባቱን ወደኋላ ሊመልሱ የሚችሉ ጥያቄዎችና አስተያየቶች በመነሳታቸው፣ በዕለቱ ይካሄዳል ተብሎ በነበረው የጋራ ውይይት ላይ ልዩነት መፈጠሩን ምንጮች አስረድተዋል፡፡ በአዳማ በተደረገው ውይይት በልዩ ዞኖቹ በኩል የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አብዱልአዚዝ መሐመድና አዲስ አበባን በመወከል ከንቲባ ድሪባ ኩማ በጋራ ውይይቱን የመሩት ቢሆንም፣ በውይይቱ የተሳተፉ የተለያዩ ቢ