Posts

የሲዳማ ኣርነት ንቅናቄ (ሲኣን) በሃዋሳ ከተማ ታላቅ ህዝባዊ ጉባኤ መጥራቱ ተሰማ

Image
ንቅናቄው በቅርቡ ከተቀላቀለው ብሔራዊ ድርጅት ከመድረክ ጋር በጋራ በመሆን በመጪው መጋቢት 20 ታላቅ ህዝባዊ ሰብሰባ በሃዋሳ ከተማ በሲዳማ ባህል ኣደራሽ ኣዘጋጅቷል። በተመሳሳይ ዜና ባለፈው ቅዳሜ በመድረክ ኣዘጋጅነት በተካሄደው ህዝባዊ ሰብሰባ ላይ የሲዳማ ኣርነት ንቅናቄ በ 15 ተወካዮች የተሳተፈ ሲሆን፤ ተወካዮቹ በሲዳማ የባህል ኣልባሳት ኣምረው ዘንጠው ወደ ጉባኤው ኣዳራሽ በገቡበት ወቅት ቤቱ በታላቅ ጭብጭባ ደማቅ ኣቀባበል እንዳደረገላቸው ሪፖርተራችን ጥቻ ወራና ከሃዋሳ ዘግቧል።

Africa Looks To Colombia For Tips On Sustainable Coffee

Image
Producers from Rwanda, Burundi and Ethiopia have visited the Colombian estates of producers to discover the social, environmental and aesthetic benefits of growing shade coffee. BOGOTA  — Which is better,  Colombian  or  African coffee ? Whatever your preference, both regions are major world producers and have begun to work together to produce coffee that offers much more than enticing flavors and aroma. This idea exchange began when producers in  Rwanda  and  Burundi  explored how they could focus on quality but also on environmental care and long-term sustainability. They wanted to generate additional revenues via tourism and improve the welfare of coffee workers at the same time.  “The two countries begin to identify these elements as important practices for sustainable landscape management, with numerous environmental and social benefits,” says Paola Agostini, the World Bank’s Africa Regional Coordinator. So it made sense that they wanted to visit South America, where

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ከኃላፊነታቸው ለቀቁ፤ በሲዳማ ቡና ገበያ ላይ ተጽኖ ይኖረው ይሁን?

Image
ዘመናዊ የግብይት ሥርዓት ለመዘርጋት ምሳሌ ይሆናል የተባለውን የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በዋና ሥራ አስፈጻሚነት ሲመሩ የቆዩትን ዶ/ር እሌኒ ገብረ መድኅንን ተክተው ሲሠሩ የቆዩት አቶ አንተነህ አሰፋ ከኃላፊነታቸው ለቀቁ፡፡ ምንጮች እንደጠቆሙት አቶ አንተነህ ከኃላፊነት የለቀቁት አሜሪካ ሆነው ባመለከቱት የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤ ሲሆን፣ የምርት ገበያው ቦርድ ጥያቄያቸውን ተቀብሎ አፅድቆታል፡፡  በቀድሞው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ አዲሱ ለገሰ ሊቀመንበርነት የሚመራው የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ቦርድ የሥራ መልቀቂያውን ተቀብሎ ውሳኔ የሰጠው፣ ሐሙስ መጋቢት 4 ቀን 2006 ዓ.ም. መሆኑን የተገኘው መረጃ ያስረዳል፡፡   አቶ አንተነህ ሥራቸውን ለመልቀቅ ውሳኔ ላይ ያደረሳቸው የጤና ችግር መሆኑን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ በልብ ሕመም ምክንያት በአገር ውስጥ በሕክምና ላይ እንደነበሩና አነስተኛ ቀዶ ጥገና ተደርጐላቸው እንደነበር ታውቋል፡፡ በዚህ ምክንያት ለከፍተኛ ሕክምና አሜሪካ የሄዱት አቶ አንተነህ፣ ሕክምናውን እዚያው በቅርብ እንዲከታተሉ በመወሰኑ ሥራቸውን ለመልቀቅ እንደተገደዱ እየተነገረ ነው፡፡ ወደ አሜሪካም ሲጓዙ ቤተሰቦቻቸውን ይዘው እንደሆነም ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡  በሥራ ገበታቸው ላይ ሳይገኙ ከሁለት ወራት በላይ የቆዩት አቶ አንተነህ፣ ይመለሳሉ ተብሎ በሚጠበቅበት ጊዜ የሥራ መልቀቂያ መላካቸው ያልተጠበቀ ነው ተብሏል፡፡  አቶ አንተነህ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን ሙሉ የምርት ገበያውን ኃላፊነት ተረክበው መምራት ከመጀመራቸው ቀደም ብሎ፣ ከነሐሴ 24 ቀን 2004 ዓ.ም. እስከ መስከረም 20 ቀን 2005 ዓ.ም. ድረስ ዕጩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተብለው ከዶ/ር እሌኒ ጋር በጋራ ሲሠሩ እንደነበር ይታወሳል፡፡ መስከረም

የኢትዮጵያ መንግስት እና የብድር ኣባዜው

Ethiopia’s Growing Debt Appetite and Eurobond The Ethiopian government has significantly increased its borrowing in recent years. Debt-to- GDP ratio has reached an all time high of 35 percent and continues to grow. Lately, the country has also been shifting slowly from concessional loans to market based loans. The Ethiopian Ministry of Finance & Economic Development (MOFED) data shows that, since the beginning of the 2008 world financial crisis through 2013, Ethiopia’s external debt has grown by 156 percent from USD 4.35 billion to USD 11.17 billion. The total public outstanding debt was at USD 16.11 billion, excluding domestic lending to State Owned Enterprises. During the same period, IMF was estimating Ethiopia’s GDP at Birr 877.5 Billion (USD 46 billion). At the moment, Ethiopia has a government guaranteed soft loan program with a rate below 2 percent, a grace period of up to 10 years, and longer duration loans with multilateral development banks, The World Bank loans m

በሃዋሳ ከተማ ሀሰተኛ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማስረጃ ኣቅራቢዎች ቁጥር ለምን ጨመረ?

Image
Photo@http://elmartyhawassa.blogspot.com/2012/06/home.html በሃዋሳ ከተማ እና በሌሎች የደቡብ ኣከባቢዎች የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማስረጃ ኣጭበርባሪዎች መበራከታቸው ተሰማ፤ ሲዳማን ጨምሮ በደቡብ ክልል በግማሽ ኣመት ውስጥ የሙያ ማረጋገጫ ፈተና ከወሰዱት 19 ሺ 862 ሙያተኞች መካከል ግማሾቹ ወድቀዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይ ከቴክኒክ እና ሙያ ተቋማት ስልጥነው የምወጡ ሙያቸኞች የሙያ ማረጋገጫ ፈተና እንድወስዱ መገደዳቸውን ተከትሎ የሙያ ማረጋገጫውን ፈተና ውጤት የሚያጭበረብሩ ሙያተኞች ቁጥር መበራከቱ እየተነገረ ነው። የወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ ሰሞኑን ከሃዋሳ እንደዘጋበው፤ ሲዳማን ጨምሮ በደቡብ ክልል ባለፉት ስድስት ወራት 19 ሺ 862 ሙያተኞች የብቃት ማረጋገጫ ፈተና የወሰዱ ሲሆኑ ፈተናውን ያለፉት ግማሾቹ ብቻ ናቸው ። የወኢኔት ሪፖርተሮች ያናገሯቸው እና ስማቸው እንድጠቀስ ያልፈለጉ በደቡብ ክልል የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ማዕከል የምሰጠውን ፈተና የወሰዱ ተፈታኞች እንደተናገሩ፤ በማዕከሉ የምሰጠው የሙያ ብቃት ምዘና ከባድ መሆኑን በየተቋማቱ ያለውን የሙያ ትምህርት ጥራት ከግምት ውስጥ ያላስገባ ነው። እንደኣስተያየት ስጪዎቱ ከሆነ፤ መንግስት በምዘና ፈተና ላይ ብቻ ትኩረት ከመሰጠት ወደየሙያ ተቋማቱ የምገቡ ሰልጣኞች በኣግባቡ የምገባውን ትምህርት እና የሙያ ክሎት እንድይዙ የሚያደርግ የትምህርት ስርዓት መዘርጋት ኣለበት ብለዋል። ኣክለውም በየየሙያ ተቋማቱ ያለው የትምህርት ስርዓት ጥራት የሌለው መሆኑን ገልጸው፤ የሙያ ማረጋገጫ ከምወስዱት ከግማሽ በላይ የምሆኑት ምዘናውን ማለፈ ኣለመቻል ለትምህርቱ ጥራት ማነስ ማሳያ ነው ብለዋል ። እንደ ሪፖርተሮቻችን ዘገባ ከሆ