በኣለማችን ላይ “ሲዳማ” የምትለውን ቃል በኢንተርኔት ላይ ሰርች የሚያደርጉ ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን የጎግል መረጃ ኣመለከተ።
ጎግል በኣለም ደረጃ “ሲዳማ” በምል ቃል ስለ ሲዳማ ጎግል የምያደርጉ ሰዎች ቁጥር ካለፉት ኣስር ኣመታት ጀምሮ እያደገ መምጣቱን የገለጸ ሲሆን፤ በተለይ እንደ ፈረንጆቹ ዘመን ኣቆጣጠር በ 2013 ከፍተኛ ቁጥር ያለው የኢንተርኔት ተጠቃሚ ሲዳማን መፈለጉ ታውቋል። እንደጎግል መረጃ በተለይ እኣኣ ከ 2007 በፊት ሲዳማ ብዙም ጎግል የተደረገ ቃል ባይሆንም፤ በ 2008 ኣጋማሽ ላይ በርካታ ሰዎች “ሲዳማ”ን ጎግል ማድረጋቸው ተመልክቷል። ቀጥሎም በ 2009 መጀመረያ ላይ የሲዳማ ጎልጋዮች ቁጥር የወረደ ሲሆን በተመሳሳይ ኣመት መጨረሻ ላይ እንደገና ኣድጓል። ከ 2010 ጀምሮ የጎልጋዮች ቁጥር ኣንዴ ስያድግ ሌላ ግዜ ሲወርድ ቆይቶ በበላፈው ኣመት መጀመሪያ ላይ በታሪኩ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ መጨመሩ ታውቋል። ነገር ግን ከ 2013 ኣጋማሽ ጀምሮ ይቁጥር በመውረድ ላይ ይገኛል። ጎግል እንዳመለከተው “ሲዳማ” የምትለውን ቃል የምጎለጉሉ ሰዎች ትራፊክ በኣብዛኛው የምፈጠረው ከሰሜን ኣሜሪካ ሲሆን፤ ኢትዮጵያ እና ሰሜን ኣውሮፓ ኣገራት እንድሁ የትራፊክ ምንጮች ናቸው። የሲዳማ ጎልጋዮች ቁጥር መጨመር እና መውረድ ከሲዳማ ዞን የፖለቲካ ሁኔታ ጋር የተያያዘ መሆኑን የወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ ትንተና ያመለከተ ሲሆን፤ ለዚህም ማሳያ በሲዳማ ዞን ውስጥ የፖለቲካ ትኩሳት የነበረባቸው ኣመታት ማለትም በ 2006 እና 2013 የተፈጠረውን ትራፊክ ማየት ይቻላል።