Posts

Forget the BRICs; Meet the PINEs

Image
While many emerging markets are taking a beating, a fantastic growth story in the developing world is widening and drawing in new countries Emerging markets are taking a beating these days, most of all the famous BRIC economies ­— Brazil, Russia, India and China. These four once seemed poised to dominate a post-American world. Not anymore. Brazil and India are posting growth rates that are only a fraction of what they were a couple of years ago. Russia’s prospects, already hampered by an overbearing state, are unlikely to improve as its aggressive moves into Ukraine could force Europe and the U.S. to impose economic sanctions. Even mighty China, while still notching admirable growth, must confront rising debt and a distorted financial system. The supremacy of the emerging world suddenly seems very far off. MORE China Exports Boom Suggests Economic Recovery Global Investors Got High on Emerging Markets: Now for the Comedown Here's An Updated Tally Of All The People Who Ha

Fichchee- The New Year of Sidama- The Sidama people celebrate the festival en mass in their sacred place called Gudumale which is located on the beautiful city of Hawassa

Image
http://commons.wikimedia.org/wiki/File:Fichchee-_The_New_Year_of_Sidama-_The_Sidama_people_celebrate_the_festival_en_mass_in_their_sacred_place_called_Gudumale_which_is_located_on_the_beautiful_city_of_Hawassa-_2013-12-18_17-37.jpg

ሆሬ _የሲዳማ ብሄረሰብ ልጃገረዶች የዘፈን ውዝዋዜ በጋዜጠኛ ቦጋሌ ጥላሁን

Image
በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ዉስጥ ከሚገኙ አስራ ሶስት ዞኖች መካከል እጅግ በርካታ የሆነ የህዝብ ቁጥር ያለዉ የሲዳማ ዞን ነዉ። በያዝነዉ አመት በተደረገ የጥናት መረጃ የሲዳማ ዞን 3.2 ሚሊዮን ህዝብ መያዙ ተነግሮአል። የለቱ የባህል ጥንቅራችን የሲዳማ ብሄረሰብ ባህላዊ ገጽታዎችን ይቃኛል። በደቡብ ኢትዮጽያ በይርጋለም ከተማ ነዋሪ የሆነዉ ጋዜጠኛ ቦጋለ ጥላሁን የረጅም ግዜ አድማጫችን ብቻ ሳይሆን ተሳታፊም ነዉ። በኢትዮጽያ የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦችን አቅፎ በሚገኘዉ በደቡብ ዞን አጓጓጊ የሆኑ የተፈጥሮ መስቦችን አሉት የሚለን ጋዜጠኛ ቦጋለ ከአዲስ አበባ 320 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘዉ በይርጋለም ከተማ ነዋሪ ሲሆን ስለ ሲዳማ ብሄረሰብ ባህል በተለይም ሆሪ ተብሎ ስለሚታወቀዉ ያላገቡ የሲዳማ ልጃገረዶች የዘፈን ዉዝዋዜ፤ ስለ ቋንቋዉ፣ ስለ ሰርግ፣ እንዲሁም ሌሎች የባህል ገጽታዎች ያጫዉተናል። በሌላ በኩል በሲዳማ ዞን ባህልና እስፖርት ማዕከል ድምጻዊ የሆነችዉ ትብለጽ ተከስተ በሲዳማ ቋንቋ በምታዜመዉ ዘመናዊ ሙዚቃዋ በአካባቢዉ ተወዳጅነትን ማትረፍዋ ነገርላታል። የሲዳማ ዞን የተፈጥሮ መስቦች ያሉበት በቱሪስቶች የሚወደድ ድንቅ የተፈጥሮ ጸጋ ያለዉም አካባቢ ነዉ መረሃ ግብሩን ያድምጡ የሲዳማ ዞን የተፈጥሮ መስቦች

የፕሬዚዳንቱን ይቅርታ የማድረግ ሥልጣን የሚቀንስ አዋጅ ቀረበ

ሪፖርተር ጋዜጣ 12 March 2014 -   መጋቢት 3, 2006 ዓ.ም. - የፓርላማ አባላት ከሕገ መንግሥቱ ጋር እንዲጣጣም ጠይቀዋል የአገሪቱ ፕሬዚዳንትን ለሕግ ታራሚዎች ይቅርታ የማድረግ ሥልጣን የሚቀንስ አዲስ ‹‹የይቅርታ አሰጣጥና አፈጻጸም ሥነ ሥርዓት›› ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማው ቀረበ፡፡ አንዳንድ የፓርላማው አባላት ረቂቅ አዋጁ ከሕገ መንግሥቱ ጋር ይቃረናል በማለት እንዲስተካከል ጠይቀዋል፡፡ የፕሬዚዳንቱን ሥልጣንና ተግባር የሚዘረዝረው የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 71 (7) ‹‹ፕሬዚዳንቱ በሕግ መሠረት ይቅርታ ያደርጋል›› በማለት ይደነግጋል፡፡ በ1996 ዓ.ም. የወጣው በአሁኑ ወቅት በሥራ ላይ የሚገኘው የይቅርታ ሥነ ሥርዓት አዋጅም በሕገ መንግሥቱ ለፕሬዚዳንቱ የተሰጠውን ይቅርታ የማድረግ ሥልጣን ያጠናክረዋል፡፡ በዚህ አዋጅ መሠረት ፕሬዚዳንቱ የይቅርታ ቦርድ የውሳኔ ሐሳብን መሠረት በማድረግ፣ እንዲሁም በውሳኔ ሐሳቡ ላይ የቀረቡ መረጃዎችን ፕሬዚዳንቱ በራሱ መመዘን ለሕግ ታራሚዎች ይቅርታ እንዲያደርግ ወይም እንዲከለክል ሥልጣን ይሰጠዋል፡፡ የፕሬዚዳንቱን ይቅርታ ያገኘ ታራሚ በሕጉ መሠረት የተጣለበትን ጥሶ የተገኘ ከሆነ በይቅርታ ቦርዱ የውሳኔ ሐሳብ አቅራቢነት ፕሬዚዳንቱ የሰጠውን ይቅርታ የማንሳት መብት በዚሁ በሥራ ላይ ባለው አዋጅ ለፕሬዚዳንቱ ተሰጥቷል፡፡  ባለፈው ማክሰኞ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ግን፣ ‹‹ፕሬዚዳንቱ የይቅርታ ቦርድን የውሳኔ ሐሳብ መሠረት በማድረግ ይቅርታ ይሰጣል፤›› ሲል በረቂቁ ክፍል ሁለት አንቀጽ 4 (1) ላይ አስቀምጧል፡፡ በማከልም ቦርዱ ለፕሬዚዳንቱ የሚልከው የውሳኔ ሐሳብ ይቅርታ የተወሰነላቸውን ታራሚዎች በመተለከተ ብቻ ነው፡፡  በቦርዱ ውሳኔ አቅራቢነት

ሳቅ እንደ አማራጭ ሕክምና?

ኮከቤ የማነ የፊኛ ካንሰር እንዳለበት ያወቀው ከአሥር ዓመታት በፊት ነበር፡፡ ህመሙን ካወቀ በኋላ ከሌሎች የካንሰር ሕመምተኞች ሰምቶ ሕመሜን ቢያስታግስልኝ በማለት ወደ ሳቅ ትምህርት ቤት ይቀላቀላል፡፡ በወቅቱ ሞትን እስከመመኘት ድረስ በበሽታ ይሰቃይ እንደነበር ይናገራል፡፡ ኮከቤ የኬሞቴራፒ ሕክምና ይፈጥርበት የነበረውን ሕመም ለመቋቋምና ስቃዩን ለማስታገስ ከረዱት ዋነኛው ሳቅ እንደሆነ ይገልጻል፡፡   የካንሰር ሕክምናን አብረውት ይከታተሉ ከነበሩት መካከል ብዙዎች ሕይወታቸው ሲያልፍ ተመልክቷል፡፡ በአካል የሚያውቃቸው ሲያልፉ ከማየቱም በላይ ሕይወቱ አደጋ ላይ በወደቀበት ወቅት ራሱን መሳቅ አስተምሯል፡፡ ኮከቤ ወደኋላ በትዝታ እየቆዘመ ‹‹ዕድለኛ ነኝ›› ይላል፡፡  ዛሬ የ45 ዓመት ጐልማሳ ነው፤ ባለትዳርና የልጆች አባትም ነው፡፡ በቤተ መንግሥት ውስጥ የሜዳ ቴኒስ አጫዋች የሆነው ኮከቤ ‹‹የእኔ ደስተኛ መሆን ለቤተሰቦቼም ተርፏል፤ ማታ ቤት እስክገባ ይቸኩላሉ፡፡ ምንም ችግር ቢኖር በሳቅ እናሳልፈዋለን፤›› ይላል፡፡ ደስተኛ መሆኑን የሚገልጸው ኮከቤ ልጆቹ እሱን በማየት ሲስቁ ማየት ያስደስተዋል፡፡  በዓለም የድንቅ ነገሮች መዝገብ ላይ ለሦስት ሰዓት ከስድስት ደቂቃ ያለማቋረጥ በመሳቅ ሪከርድ የጨበጠና ‹‹የዓለም የሳቅ ንጉሥ›› የሚል መጠሪያ ያገኘው በላቸው ግርማ፣ ኮከቤን ለመሰሉና ሌሎች የሳቅ ትምህርት ቤት ካቋቋመ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ በእነዚህ ዓመታት ወደ ትምህርት በመሔድ ስለ ሳቅ፣ አሳሳቅንና በሌሎች ተያያዥ ትምህርቶች ለአንድ ወር ሠልጥነው የወጡ ተማሪዎች አሉ፡፡ በአፍሪካ ባሉ አገሮች ጅማሮዎች ቢኖሩም በኢትዮጵያ የሚገኘው ትምህርት ቤት የቆየና ግንባር ቀደም እንደሆነ የተለያዩ ዘገባዎች ያመለክታሉ፡፡  በላቸው ስለሳቅ ትምህርት ቤት ሲና