የፕሬዚዳንቱን ይቅርታ የማድረግ ሥልጣን የሚቀንስ አዋጅ ቀረበ
ሪፖርተር ጋዜጣ 12 March 2014 - መጋቢት 3, 2006 ዓ.ም. - የፓርላማ አባላት ከሕገ መንግሥቱ ጋር እንዲጣጣም ጠይቀዋል የአገሪቱ ፕሬዚዳንትን ለሕግ ታራሚዎች ይቅርታ የማድረግ ሥልጣን የሚቀንስ አዲስ ‹‹የይቅርታ አሰጣጥና አፈጻጸም ሥነ ሥርዓት›› ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማው ቀረበ፡፡ አንዳንድ የፓርላማው አባላት ረቂቅ አዋጁ ከሕገ መንግሥቱ ጋር ይቃረናል በማለት እንዲስተካከል ጠይቀዋል፡፡ የፕሬዚዳንቱን ሥልጣንና ተግባር የሚዘረዝረው የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 71 (7) ‹‹ፕሬዚዳንቱ በሕግ መሠረት ይቅርታ ያደርጋል›› በማለት ይደነግጋል፡፡ በ1996 ዓ.ም. የወጣው በአሁኑ ወቅት በሥራ ላይ የሚገኘው የይቅርታ ሥነ ሥርዓት አዋጅም በሕገ መንግሥቱ ለፕሬዚዳንቱ የተሰጠውን ይቅርታ የማድረግ ሥልጣን ያጠናክረዋል፡፡ በዚህ አዋጅ መሠረት ፕሬዚዳንቱ የይቅርታ ቦርድ የውሳኔ ሐሳብን መሠረት በማድረግ፣ እንዲሁም በውሳኔ ሐሳቡ ላይ የቀረቡ መረጃዎችን ፕሬዚዳንቱ በራሱ መመዘን ለሕግ ታራሚዎች ይቅርታ እንዲያደርግ ወይም እንዲከለክል ሥልጣን ይሰጠዋል፡፡ የፕሬዚዳንቱን ይቅርታ ያገኘ ታራሚ በሕጉ መሠረት የተጣለበትን ጥሶ የተገኘ ከሆነ በይቅርታ ቦርዱ የውሳኔ ሐሳብ አቅራቢነት ፕሬዚዳንቱ የሰጠውን ይቅርታ የማንሳት መብት በዚሁ በሥራ ላይ ባለው አዋጅ ለፕሬዚዳንቱ ተሰጥቷል፡፡ ባለፈው ማክሰኞ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ግን፣ ‹‹ፕሬዚዳንቱ የይቅርታ ቦርድን የውሳኔ ሐሳብ መሠረት በማድረግ ይቅርታ ይሰጣል፤›› ሲል በረቂቁ ክፍል ሁለት አንቀጽ 4 (1) ላይ አስቀምጧል፡፡ በማከልም ቦርዱ ለፕሬዚዳንቱ የሚልከው የውሳኔ ሐሳብ ይቅርታ የተወሰነላቸውን ታራሚዎች በመተለከተ ብቻ ነው፡፡ በቦርዱ ውሳኔ አቅራቢነት