Posts

ስለከሸፈው “መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ” ጥራዝ አንዳንድ ነጥቦች

በተስፋዬ ንዋይ  መነሻ የአገራችንን የአጭር ጊዜ ታሪክ በጥልቀት ለሚመለከት ታዛቢ እጅግ በጣም የሚያሰቅቅና አፍ የሚያሲዘን ጉዳይ የተወሰኑ የዕውቀት ገመዶች የጥፋት ብርሃን ማስተላለፊያ በመሆናቸው ነው፡፡ በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ በተጨባጭ እውነት ላይ የተመሠረተ ሚዛናዊ ትንታኔ በበቂ ሁኔታ የተሰጠ አይመስለኝም፡፡ ይህ መሠረታዊ ሀቅ ንቅንቅ ወደማይል አለትነት የደረሰ ይመስላል፡፡ ይህን ችግር ከመሠረቱ የሚፈጥረው ደግሞ “የኢትዮጵያ ታሪክ” ተብሎ በጽሑፍም ሆነ በቃል የሚተረተረው ሐሳብ እውነታን መሠረት ያላደረገ መሆኑ ብቻ ሳይሆን፣ ለፖለቲካ፣ ግብዓትና ዓላማ ተብሎ የቀረበ ወይም እየቀረበ ያለ መሆኑ ነው፡፡ ይህ መምታታት አገሪቷን አንድ አስማሚ የሆነ ታሪክ የሌላት የሚያስመስላት ብቻ ሳይሆን የግልን የፖለቲካ ዓላማ ማካሄጃ መድረክ እንዲሆን ዕድል ፈጥሯል፡፡  የአገራችን የታሪክ ሒደትና ውጤት ላይ በእውነት (Authentic) ላይ የተመሠረተ የታሪክ ዕድገት በአገሪቷ ተመዝግቦ  ያለመኖሩ አንድ ችግር ሆኖ፣ እነዚህ በእውነት ላይ ያልተመሠረቱ ታሪኮችን ከእውነት በላይ አድርጎ በመውሰድ ምሁራዊ ትንታኔዎችን በእነሱ ላይ መስጠት ሌላው አበሳጭ ጉዳይ ነው፡፡ ይህንን እንድል ያደረገኝ በቅርቡ በገበያ ላይ ውሎ የተሰራጨውን  “መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ” የሚል ጥራዝ አንብቤ ከጨረስኩኝ በኋላ ነው፡፡ ይህ ጥራዝ የተጻፈው መስፍን ወልደማርያም በሚባሉ ግለሰብ (እኚህ ግለሰብ ፕሮፌሰር የሚል ማዕረግ የደረቡ ቢሆንም በመጽሐፉ ላይ ስላወለቁት እኔም ትቼዋለሁ) ሲሆን፣ በዚህ አጭር በማይባል ጥራዝ ጸሐፊው ያሉዋቸውን አስተሳሰቦችና ከአስተሳሰቦቹ ጀርባ ያሉትን መነሻዎች በሚገባን ቋንቋ አቅርበዋል፡፡ በዚህ ጥራዝ የታጨቁት ሐሳቦች ዘርፈ ብዙ ቢሆኑም፣ በዚህች አ

የተንከባለሉ የማንነት ጥያቄዎች

ኅዳር 29 ቀን 1987 ዓ.ም. የፀደቀው የኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት ዛሬ ሥራ ላይ ከዋለ 19ኛ ዓመቱ ነው፡፡ ሕገ መንግሥቱን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ የተለያዩ ተግዳሮቶች ቢገጥሙም በአገሪቱ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓትን ለመምራት የሚያስችል ሰነድ ስለመሆኑ ብዙዎች ይስማማሉ፡፡ የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት እንደ ሌሎች ሕገ መንግሥቶች በሕዝቦች መካከል የተገባ ቃል ኪዳን አይደለም፡፡ ይልቁንም በብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መካከል የተገባ ቃል ኪዳን ነው፡፡ ራስን በራስ የማስተዳደር እስከ መገንጠል መብት  ለተሰጣቸው ለእነዚህ ቡድኖች ሕገ መንግሥቱ የሉዓላዊነታቸው መገለጫ ነው፡፡    ከአንድነት ባልተናነሰ ሁኔታ ልዩነትና የማንነት ጥያቄ በሕግም ሆነ በተግባር ድጋፍ እንደሚሰጠው ይገመታል፡፡ የሕገ መንግሥቱን የተለያዩ አንቀጾች በማየት የማንነት ጥያቄዎች ሕገ መንግሥታዊ ድጋፍ አላቸው ከማለትም በላይ እነዚህ አንቀጾችና የራስን ዕድል በራስ የመወሰን እስከ መገንጠል መርህን በማንገብ ታግሎና አታግሎ በአሸናፊነት ሥልጣን የያዘው፣ በሕገ መንግሥት ማርቀቅ ሒደቱም ወሳኝ ሚና ያለው ገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ ለተግባራዊነቱ ታማኝና ቁርጠኛ ነው የሚል ግምትም በብዙዎች ዘንድ ሥር የሰደደ ነበር፡፡  ይሁንና በተግባር ኢሕአዴግ የመገንጠልን፣ ክልል የመሆንና የማንነት ጥያቄዎችን በተለያዩ ጊዜያት ላነሱ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የሰጠው ምላሽ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የሕገ መንግሥቱ ዋነኛ መሠረት የሆነው መርህ በሥራ ላይ ያለውን የመንግሥት ቅርፅ እንዲለውጥ በሚያስችል ሁኔታ እንዲተገበር ፍላጎት እንደሌለው ሪፖርተር ያነጋገራቸው የሕግና የፖለቲካ ሳይንስ ምሁራን ይገልጻሉ፡፡  በቅርቡ ለህትመት የበቃው ‹‹የራያ ሕዝብ የማንነት ጥያቄና የማዕከላዊ መንግሥታት ምላሽ ከአፄ ዮሐንስ

12 ሺ ቶን ቡና በተጭበርበረ ሰነድ ወደ ውጭ አገር መላኩ ታወቀ

Image
የካቲት ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የስነምግባር እና ጸረ ሙስና ኮሚሽን በቅርቡ በቡና አስተዳደር ላይ የሚታየውን ችግር አስመልክቶ ያወጣውን ሪፖርት ተከትሎ 12 ሺ ቶን ወይም  1 መቶ 20 ሺ  ኩንታል ቡና በተጭበረበረ ሰነድ ወደ ውጭ ተልኮ መሸጡን አመልክቷል። ኮሚሽኑ ቡናው በማን በኩል ተሰርቆ እንደተላከ እያጣራ መሆኑን የዘገበው ሪፖርተር፣ የሽያጩ ገንዘብም ወደ አገር ውስጥ አለመግባቱን ገልጿል። ዛሬ ባለው የአለም የቡና የመሸጫ ዋጋ 120 ሺ ኩንታል ቡና ከ16 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወይም ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያወጣል። ይህን ያክል ገንዘብ በአንድ ጊዜ በተጭበረበረ ሰነድ መዝረፍ የሚቻልባት አገር ሆናለች የሚለው ዘጋቢያችን፣ ድርጊቱ መንግስት አለ ወይ ያሰብላል ሲል ሃሳቡን አሰፍሯል። አቶ መለስ በስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት 10 ሺ ኩንታል ቡና መጥፋቱ ይታወቃል። ስለዚሁ ጉዳይ ጥያቄ የቀረበላቸው አቶ መለስ መንግስታቸው እያጣራ መሆኑን ተናግረው ነበር። ይሁን እንጅ የምርመራው ውጤት ምን ደረጃ ላይ እንደደረሰ የታወቀ ነገር የለም። ዘጋቢያችን እንደሚለው ጸረ ሙስና ኮሚሽን እየመረመርኩ ነው ቢልም፣ የምርመራው ውጤት ታፍኖ ሊቀር የሚችልበት እድሉ ሰፊ ነው። በጉዳዩ ዙሪያ የንግድ ሚኒስቴር ባለስልጣናትን ለማግኘት የተደረገው ሙከራ አልተሳካም። http://ethsat.com/amharic/12-%E1%88%BA-%E1%89%B6%E1%8A%95-%E1%89%A1%E1%8A%93-%E1%89%A0%E1%89%B0%E1%8C%AD%E1%89%A0%E1%88%AD%E1%89%A0%E1%88%A8-%E1%88%B0%E1%8A%90%E1%8B%B5-%E1%8B%88%E1%8B%B0-%E1%8B%8D%E1%8C%AD-%E1%8A%A0%E1%8C%88/

ሃዋሳ ሐይቅ እና ወፎቿ

Image
ኣስደዳሚ እና ብርቅዬ የሐዋሳ ሐይቅ ኣእዋፋት ፎቶ ለማየት እዚህ ይጫኑ

የመላው ደቡብ ክልል ስፖርቶች ውድድር በሲዳማ ዞን አሸናፊነት ተጠናቀቀ

Image
አርባምንጭ የካቲት 23/2006 በደቡብ ክልል በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን የስፖርቱን መስክ ከሌሎች የልማት ፕሮግራሞች ጋር አቀናጅቶ በማስኬድ ውጤታማ ስራ መከናወኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ዳሴ ዳልኬ ገለጹ። ባለፉት 2 ሳምንታት በአርባምንጭ ከተማ ሲካሄድ የቆየው የመላው ደቡብ ክልል የልዩ ልዩ ስፖርቶች ውድድር በሲዳማ ዞን አጠቃላይ አሸናፊነት ትናንት ተጠናቋል። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድርና የስፖርት ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ዳሴ ዳልኬ በስፖርት ውድድሩ ማጠቃለያ ላይ እንደገለጹት የክልሉ መንግስት በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን በስፖርቱ መስክ ባስቀመጣቸው ግቦች መሰረት ስኬታማ ውጤቶች አስመዝግቧል፡፡ በእግር ኳስ በአገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ተተኪ ስፖርተኞች ለማፍራት የሚያስችሉ ተግባራት ተከናውነዋል፡፡ ስፖርት የአምራቹን ኃይል የአካል ብቃት ለማጎልበትና ጤንነቱን ለመጠበቅ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው የገልጹት ርዕስ መስተዳድሩ  የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦችን ባህል ልውውጥ በማሳደግና ገጽታን በመገንባት የክልሉን ብሎም የሀገሪቱን ህዳሴ ለማረጋገጥ እንደሚያግዝም ተናግረዋል፡፡ ዘርፉ ለሁለንተናዊ ልማትና እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያለው በመሆኑ ይበልጥ ለማጠናከር በየደረጃው የሚገኘው አመራር የስፖርት ቤተሰቦችን በማቀናጀት ትኩረት ሰጥቶ እንዲሰራም አሳስበዋል። የክልሉ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ መዝርድን ሁሴን በበኩላቸው ላለፉት 2 ሳምንታት በተለያዩ ድማቅ ስነስርዓቶች ታጅቦ ሲካሄድ የቆየው የመላው ደቡብ ስፖርቶች ውድድር ተተኪ ስፖርተኞችን ለይቶ ለማዘጋጀት ማስቻሉን ገልጸዋል። በውድድሩ ሀዋሳ ከተማን ጨምሮ ከ14 ዞኖችና ከ4